የ 2-3-4 የእንቅልፍዕቅድ

አንዳንድ እናቶች ከህጻኑ የእንቅልፍ ዘይቤ ጋር ለመላማድ የ “2-3-4 የእንቅልፍ ዕቅድ” ይጠቀማሉ:: ለእናቲቱም ለህጻኑም ይህ ዘዴ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ህጻን (ከ 6 እስከ 8 ወር የሆነ ህጻን፣ ወይም በአብዛኛው ህጻኑ ማታውን ሙሉ መተኛት በሚጀምርበት ወቅት) ይህን የ 2-3-4 የእንቅልፍ ዕቅድ የእንቅልፍ ድግግሞሽ ማስለመድ ይቻላል:: ይህ ማለት ግን ለሁሉም ህጻን ይሰራል ማለት አይደለም:: የ 2-3-4 የእንቅልፍ ዕቅድን ከዚህ በታች በ3 አገላለጽ አስቀምጠነዋል፡፡

የ 2-3-4 ስልት እንዴት እንደሚሰራ ተመልከቱ – አገላለጽ አንድ

ህጻኑ በጠዋት በፈለገው ሰዓት ነቃ፡፤ ከነቃ ልክ ከ 2 ሰዓት በኋላ ለአጭር እንቅልፍ ያስተኙት(ለእንቅልፍ ያጋድሙት)::  የዚህ አጭር እንቅልፍ ቆይታውም ከ 1-2 ሰዓት ሊረዝም ይችላል::  ህጻኑ ከነቃ በኋላም ነቅቶ እስከ 3 ሰዓት ይቆያል:: ለሁለተኛው አጭር እንቅልፍ ልክ ከነቃ ከ 3 ሰዓት በኋላ ለሌላ አጭር እንቅልፍ ያስተኙት(ለእንቅልፍ ያጋድሙት)::  በተለምዶ ረዘም ላለ አጭር እንቅልፍ ከ 1.5 – 3 ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ሊተኛ ይችላል:: ህጻኑ ከሁለተኛው የአጭር እንቅልፍ ጊዜ ከነቃ በኋላ ለ 4 ሰዐታት ነቅቶ ይቆያል:: ከዛም ከ 4 ሰዓታት ቆይታ በኋላም ተመልሶ ይተኛል፤ በዚህ ጊዜ የምሽት መኝታ ሰዓት ደረሰ ማለት ነው:::

የ 2-3-4 ስልት እንዴት እንደሚሰራ ተመልከቱ – አገላለጽ ሁለት

ህጻኑ ጠዋት ከእንቅልፍ ከነቃ ከ 2 ሰዓት በኋላ፣ ለአጭር እንቅልፍ ያስተኙት(ለእንቅልፍ ያጋድሙት):: ከአጭሩ እንቅልፉ ከነቃ ከሶስት ሰዓት በኋላ፣ በድጋሚ ለአጭር እንቅልፍ ያስተኙት(ለእንቅልፍ ያጋድሙት):: ከአጭሩ እንቅልፉ ከነቃ ከአራት ሰዓት በኋላ፣ የምሽት መኝታ ሰዓት ደረሰ ማለት ነው::

የ 2-3-4 ስልት እንዴት እንደሚሰራ ተመልከቱ – አገላለጽ ሶስት

  • የመጀመሪያው አጭር እንቅልፍ ጠዋት ከእንቅልፍ መንቃት በኋላ ከ 2 ሰዓት በኋላ መሆን አለበት
  • የሁለተኛው አጭር እንቅልፍ ከመጀመሪያው ማንቀላፋት ንቃት በኋላ ከ3 ሰዓት በኋላ መሆን አለበት

የመኝታ ጊዜ ደግም ከሁለተኛው የእንቅልፍ ጊዜ ንቃት በኋላ ከ4 ሰዓት በኋላ መሆን አለበት ለባቸው፡፡