ማርገዝ አለመቻል (መካንነት)
አንዳንድ ሴቶች ልጅ እንዲኖራቸው ቢፈልጉም ወይ ደጋግሞ ይጨናገፍባቸዋል ወይንም ደግሞ ቅሪት መያዝ አይችሉም:: ይህ ሲሆን Infertility መካንነት ወይም መሃንነት ይባላል፤ ሀሳቡ ጊዜያዊ ማርገዝ ያለመቻልን ለማመላከት ሆኖ ነገር ግን በህክምና እስካልተረጋገጠ ድረስ እራስን እንደ መሀን ማሰብ የለብንም:: ከአመት ሙከራ በኋላ ወይም ከ35 አመት በላይ ለሆነች ሴት ደግሞ ከ 6 ወር በኋላ ቅሪት ካልያዘች ለበለጠ እርዳታ ወደ ዶክተር መሄድ ይመከራል:: የመካንነት ችግር በሴቶችም ላይ ሆነ በወንዶች ላይ የሚከሰት ነው:: ዶክተሮች መውለድ ያልቻሉ ጥንዶችን መውለድ እንዲችሉ ሊረዱ ችለዋል::
በቀጥታ ነፍሰጡር ባለመሆናችሁም ልትገረሙም ሆነ ልትበሳጩ አይገባችሁም:: በአብዛኛው የሚዘገይ ነው፣ ይህም የተለመደ ኖርማል ነው:: አስታውሱ ከ100 ጥንዶች ከ 80-90 የሚሆኑት በመጀመሪያው አመት ነፍሰጡር ይሆናሉ:: ከ100 ጥንዶች 95 የሚሆኑት ደግሞ በ ሁለት አመት ውስጥ ነፍሰጡር ይሆናሉ:: በአንዴው ነፍሰጡር አልሆንሽም ማለት ችግር አለ ወይም ደግሞ ከተለመደው የወጣ ነው ማለት አይደለም:: ከወራት ሙከራ በኋላ እንኳ ነፍሰጡር አለመሆን ሊያስጨንቅ አይገባም – የተለመደ ኖርማል ነው::
የሴቶች መካንነት
ፍሬያማነትን ብዙ ነገሮች ሊጎዱት ይችላሉ:: ከእነዚህም ውስጥ ውጥረት፣ ማጨስ፣ የአባላዘር በሽታዎች፣ እንዲሁም ሌሎች የጤና ችግሮች በዋናነት ይጠቀሳሉ:: ደግሞም፣ ሴት እድሜዋ ሲጨምር፣ ቅሪት የመያዝ እድሏ እየጠበበ ይመጣል::
ነፍሰ ጡር እንዳይሆኑ ሊያግዱ የሚችሉ የተለያዩ ምክንያቶች አሉ:: አንደኛው ምክንያት ሊሆን የሚችለው በየወሩ ፍሬያማነት (እንቁላል) ላይከሰት ይችላል:: በቅርቡ የሆርሞናል የወሊድ መቆጣጠሪያ ተጠቃሚ ከነበሩ፣ ፍሬያማነት ሊዘገይ ወይም ደግሞ ስርዐትን ያልተከተለ ሊሆን ይችላል:: የመርፌ የወሊድ መቆጣጠሪያ ተጠቃሚ ከሆኑ፣ እስከ አመት ድረስ ፍሬያማነት ሊዘገይ ወይም ደግሞ ስርዓትን ያልተከተለ ሊሆን ይችላል::
ከሚደረጉት ህክምናዎች ውስጥም፣ የኑሮ ዘዴን ላይፍ ስታይልን መለወጥ፣ ውጥረትን መቀነስ፣ ሴቶች እንቁላል እንዲያፈሩ የሚያደርጉ መድሀኒቶች መስጠት፣ የመራቢያ አካላት ላይ በሚደረግ የቀዶ ጥገና፣ በመራቢያ ቴክኖሎጂዎች እርዳታ ለምሳሌ እንደ ቪትሮ ፈርትላይዜሽን ወዘተ ይጠቀሳሉ፡፡
