በመጀመሪያወቹ ወራቶች የጨቅላው ብቸኛ ፍላጎቱን ማሟያ የመግባቢያ መንገድ የሚሆነው ማልቀስ ነው:: ማልቀሱ
- ጨቅላው መሽናቱን፣
- መድከሙን፣
- መራቡን፣
- ብቸኝነትን፣
- እንዳልተመቸው፣
- እንደተጸዳዳ፣
- እንቅልፍ እንደፈለገ፣
- መታቀፍ እንደፈለገ፣
- ሆዱን እንዳመመው(ፈስ፣ ላክቶስ ኢንቶለራንስ፣ መጸዳዳት አለመቻል፣ የአንጀት መዘጋት እና ሌሎችም)፣
- ማግሳት እንደፈለገ፣
- እንደበረደው ወይም እንደሞቀው፣
- የሆነ ትንሽ ነገር እየቆረቆረው እንደሆነ፣
- ደህና ስሜት እንዳልተሰማው ወይም
- ደግሞ ጉሮሮውን እያለማመደ መሆኑንን የሚያመላክት ነው::
የጨቅላው ድርጊቶች እና ማልቀሱ ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት ጊዜ ይወስዳል። ይህ ለአንዳንዶች አስቸጋሪ ሂደት ነው:: እንደማንኛውም የህይወት ሁነቶች፣ እነዚህን ነገሮች በሂደት መማር ያስፈልገናል፤ ወይ በሙከራ እና በስህተት፣ ወይም በማንበብ ና በመጠየቅ፣ ወይም ከባለሙያ ጋር አብሮ በመዋል:: በሂደትም ስለ ጨቅላው ባህርይ ይበልጥ የሚረዱት ይሆናል።
የለቅሶ መፍትሄ
አስታውሱ የጨቅላው ማልቀስ በራሱ የሚጎዳ አይደለም፤ ምናልባትም እንዲሁ ፈልጎ ይሆናል:: የሚያለቅስን ህጻን ለማስቆም የሚከተሉት መፍትሄዋችን ይሞክሩ
- ዳይፐሩን ማየት እና መቀየር ወይም ማስተካከል፣ የሽንት ጨርቅ መቀየር፣ ሙሉ ልብሱን ማውለቅ እና ማየት
- የሚመጡት ወይም የሚመጠምጡት ነገር መስጠት፣
- ልጅዎ ያልተራበ መሆኑን መረጋገጥ
- ከህፃኑን ማንሳት እና መሸከም፣ ጠቅልሎ ማቀፍ፣
- ልጅዎን ወደ ሰውነትዎ ኣስጠግተው ይቀፉት እና በተረጋጋ መንፈስ ይተንፍሱ።
- ህፃኑን ሞቅ ባለ ውሃ ገላውን ይጠቡት.
- በሚያረጋጋ ሎሽን ማሸት::
- የሕፃኑን ጀርባ ማሸት።
- ልጅዎን ጭንዎ ላይ በሆዱ ያስተኙት እና የልጅዎን ጀርባ ያሻሹ።
- ማንቀሳቀስ ልጅዎን በሚወዛወዝ ወይም በትንሹ በሚንቀጠቀጥ ወንበር ላይ ያድርጉት። እንቅስቃሴው የሚያረጋጋው ሊሆን ይችላል.
- ልጅዎን ከመኪናው ጀርባ ባለው የጨቅላ መኪና መቀመጫ ላይ ያድርጉት እና ለመንዳት ይሂዱ። ብዙውን ጊዜ የመኪናው ንዝረት እና እንቅስቃሴ ህፃናትን ያረጋጋል
- መልዕክት ለህፃኑ መንገር፣ የሆነ አይነት ጩሀት ማሰማት፣ የውሀ ድምጽ ማሰማት፣
- ለልጅዎ ዘምሩ ወይም ልጅዎን ያነጋግሩ። ሙዚቃይዘምሩ – አንዳንድ ሕፃናት ለድምፅ እና ለእንቅስቃሴ ምላሽ ይሰጣሉ.
- ንጹህ አየር፣ ሕፃኑን በጋሪ ውስጥ ለመንዳት ይውሰዱት።
- ጓደኛን ወይም ዘመድን ለማማከር መጥራት፣ የምታምኑት ሰው እንዲረዳችሁ ማድረግ
- ለራሳችሁ እንዲህ በሉት “ከጥቂት አመታት በኋላ የኔ ልጅ ማቆም እስኪያቅተው መሳቅ ይጀምራል!”
ምንም አድርጉ ምን፣ ብስጭታችሁን ህጻናችሁ ላይ አትግለጹ:: በፍጹም ጨቅላትን የንዴት አትወዝውዙት :: የህጻን የአእምሮ ውስጥ ያሉት የደም ስሮች የውዝዋዜን ተጽዕኖ መቋቋም የማይችሉና ሊሰበሩ የሚችሉ ናቸው::
በተሎ የማይባበል አልቃሻ ህጻን በቤተሰቦቹ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ውጥረት ይፈጥራል:: ይመስገነውና፣ ከፍ እያለ ሲሄድ፣ ራሱን ማረጋጋት የሚችል እና አብዛኛው ልቅሶውም የሚቀንስ ይሆናል:: አረ ሣቁም የማይጠገብ ፍሰኃ ነው።