የጽንስ አጀማመር

ነፍሰ  ጡር  ለመሆን (መፀነስ ለመጀመር) እንቁላል  በወንድ  ዘር በልጽጋ  በማህፀን ውስጥ  መቀመጥ  አለበት::   የጽንስ አጀማመርም  እንቁላልን  ከማበልጸግ  የሚጀምርና  የበለጸገች እንቁላል  በተሳካ ሁኔታ በማህፀን ውስጥ  መቀመጥ ነው::

በእያንዳንዱ  የወር አበባ  ጊዜ የበለጸገች እንቁላል  ከኦቫሪ ትለቀቃለች::  እንቁላሉ ከተለቀቀ በኋላ በዛ በተወሰነ ጊዜ ብቻ እርጉዝ ይኮናል::  እንቁላሉም ከፋሎፒያን ቱቦ ወደ ታች ማህፀን ይጓዛል::  እንቁላል ሊኖር የሚችለው ቢበዛ እስከ 24 ሰዓት ድረስ ነው::  በእያንዳንዱ ወር፣ የማህፀን ግድግዳ ሊከሰት ለሚችል እርግዝና ይዘጋጃል::

የእርግዝና  ወቅት  ማለት በወንድ ዘር  የዳበረችው እንቁላል ማህፀን ውስጥ ማደግከጀመረች በት ቀንጀምሮ ወደፊት ልጅ  እስከ ሚወለድ በትቀንድረስ ያለው ጊዜ ነው። አብዛኛው  እርግዝና ለ 9 ወራት ወይም ለ40  ሳምንታ ትያህል ጊዜ ይቆያል።አንድ እርግዝና መቆጠር የሚጀምረው የወር አበባ ከቆመበት ቀን ጀምሮ ወይም ዋናውጽንስ ከማጋጠሙ በፊት ያሉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ነው። የወር አበባ መጨረሻከታየ ከአርባ ሳምንታት በኋላ ልጅ ይወለዳል።