አምሮት

ባልም አርግዟል!

እርግዝና ባልና ሚስት በጋራ ተጋግዛው የሚወጡት የህይወት ምዕራፍ ነው። የሚስቶች የእርግዝና ወቅት ለባሎች አዲስና ፈታኝ ጊዜ ነው፡፡ በተለይ የመጀመሪያ እርግዝና ለሁለቱም እያደር አዲስ የሚባል ክስተት ያለው ዘጠኝ ወር ሊባል ይችላል። ነፍሰጡርነት ለሔዋኖች ብቻ የተሰጠ ሲሆን እርግዝና ደግሞ ባሎችንም የሚያካትት እኩል የሆነ የጋራ ኃላፊነት ነው።

ሚስት ነፍሰጡር ስትሆን፣ ባልና ሚስት ደግም አርግዘዋል!

በእርግዝና ወራት ሰውነት የተለያዩ ለውጦችን ያስተናግዳል፡፡ ነፍሰጡር ሴት በእርግዝናዋ ሳቢያ የተለያዩ ሆርሞኖች በሰውነቷ ውስጥ ይፈጠራሉ፡፡ እነዚህ ሆርሞኖችም በሰውነቷ የተለያዩ ክፍሎች ላይ የሚታዩ ለውጦችን ያስከትላሉ፡፡ በባህርይዋ፣ በአተነፋፈሷ፣ በልብ ምቷ ና በምግብ ፍላጎቷ ላይ ለውጥ ይከተላል፡፡

የባሎች ትዕግስትና የፍቅራቸው ልክ ከሚፈተኑባቸው አጋጣሚዎች መካከል የሚስቶቻቸው የእርግዝና ወቅት ተጠቃሽ ነው። በእርግዝናዋ የመጀመሪያ 3 ወራት ማስመለስና ማቅለሽለሽ በብዛት ሊያጋጥማት ይችላል፡፡ የምግብ ፍላጎቷና ምርጫዋ የተለየ ሊሆንም ይችላል። ነፍሰጡር ሴቶች በእርግዝና ወቅት የተለያዩ ነገሮች እንዲሚያምሯቸው ሲናገሩ ይሰማል:- አፈር፣ የመኪና ወይም የሲጋራ ጭስ፣ የቤንዝን ወይም የተበላሸ ምግብ ሽታ፣ ሣሙና፣ ሊጥ፣ ትርፍራፊ ምግቦች፣ የኮመጠጡ መጠጦች፣ ያምረናል ከሚሏቸው ነገሮች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

አምሮት

በእርግዝና ጊዜ የነፍሰጡር ሴት የምግብ ፍላጎትና ምርጫ  የተለየ ሊሆን ይችላል። በዚህ ጊዜ የቤተሰብ እርዳታና ክትትል ስለሚያስፈልግ  ቤተሰቦቿ በተለይም ባሏ ከጎኗ ሊቆሙ ይገባል። ነፍሰጡር ሴቶች በእርግዝና ወቅት የተለያዩ ነገሮች እንደ ሚያምሯቸው ሲናገሩ ይሰማል:- አፈር፣ የመኪና ወይም የሲጋራ ጭስ፣ የቤንዝን ወይም የተበላሸ ምግብ ሽታ፣ ሣሙና፣ ሊጥ፣ ትርፍራፊ ምግቦች፣ የኮመጠጡ መጠጦች፣ ያምረናል ከሚሏቸው ነገሮች ጥቂቶቹ ናቸው።

በእርግዝና ወቅት ለሚከሰት የተለየ የምግብ አምሮት መነሻ ሊሆኑ የሚችሉ ሁለት መሰረታዊ ምክንያቶች ዉስጥ አንዱ በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የብረት ማዕድን እጥረት መሆኑን ይገለፃል፡፡ በዚህ ማዕድን እጥረት የተነሳ የደም ማነስ የሚፈጠርባቸው ነፍሰጡር ሴቶች በእርግዝናቸው ወቅት የማይበሉ ነገሮችና ለመብላት የመፈለግ ባህርይ ሊያሣዩ ይችላሉ፡፡

የብረት ማዕድን እጥረት የገጠማት ሴት

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ አገራት ከ48 በመቶ በላይ የሚሆኑ ሴቶች የብረት ማዕድን እጥረት እንደሚታይባቸው ዶክተሮች ይናጋራሉ።ለዚህም ምክንያቱ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት፣ አከታትሎ መውለድና በወሊድ ወቅት የሚያጋጥም የደም መፍሰስ ሊሆኑ ይችላሉ።

”በእነዚህ ምክንያቶች የብረት ማዕድን እጥረት የገጠማት ሴት በእርግዝናዋ ወቅት እንደ አፈር፣ ሣሙና፣ ትርፍራፊ ምግቦችና መሰል ያልተለመዱ ነገሮችን የመብላት ፍላጐትና አምሮት ይኖራታል፤ እነዚህ የማይበሉ ነገሮች ደግሞ ንፅህና የሌላቸውና ለምግብነት የሚዘጋጁ ባለመሆናቸው በነፍሰጡሯ ላይ እጅግ አደገኛ የሆኑ የጤና ችግሮችን ሊያስከትሉባት ይችላሉ” የማህፀንና ፅንስ ሃኪም ዶክተር አክሊሉ ወንድሙ። የማይበሉ ነገሮች የሚያምራቸውና የሚበሉ ነፍሰጡር ሴቶች፤ ምናልባትም የሥነ አዕምሮ ችግር ያለባቸው ሊሆኑ ይችላሉ ብለዋል – ዶክተር አክሊሉ።

ጤናማ አምሮት

ሌላው ጤናማ የሚባለውና እርግዝናን ተከትሎ በሴቷ ሰውነት ላይ በሚፈጠር የሆርሞን ለውጥ ሣቢያ በበርካታ ሴቶች ላይ የሚከሰት አምሮት ነው። የሆርሞን ለውጡ ከነርቭ ሥርዓት ሒደት ጋር በተያያዘ የምግብ ፍላጐትና ምርጫ ላይ ለውጥ ይፈጥራል፡፡ ነፍሰጡሯ ሴት የምትመገበው ምግብ፣ በሆዷ ለያዘችው ፅንስ ጭምር በመሆኑ ምግቡን የሚጋራት አካል በውስጧ ስለአለ ሰውነቷ የምግብ እጥረት ያጋጥመዋል፡፡ በዚህ ወቅትም በአንድ የተለየ ወይም የተወሰነ ምግብ ላይ ትኩረት እንድታደርግ ያስገድዳታል፡፡

“ይህ ጤናማ የእርግዝና አምሮት ሊባል ይችላል” ያሉት ዶክተር አክሊሉ፤ ነፍሰጡሯ ምንም ያህል ፍላጐትና አምሮት ቢኖራት ንጽህናቸው ያልተጠበቁ ምግቦችን ወይም ለምግብነት የማይውሉ ነገሮችን በምንም ዓይነት ሁኔታ መመገብ እንደሌለባት አበክረው አስገንዝበዋል፡፡ በእርግዝና ወቅት የሲጋራ ወይንም የቤንዝን ሽታ አማረኝ የሚሉ ሴቶች ወይንም አምሮቱ የሚያጋጥማቸው ነፍሰጡሮች በተቻላቸው መጠን አምሮታቸውን ለመርሳትና በሌሎች ነገሮች ለመለወጥ ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህንን በማድረጋቸው ምክንያትም በእነሱም ሆነ በማህፀናቸው ባለው ፅንስ ላይ የሚፈጠር ችግር አይኖርም ሲሉም ዶክተሩ ተናግረዋል፡፡

ምክር

በአምሮት ሰበብ ለእናቲቱም ሆነ ለጽንሱ እጅግ አደገኛ የሆኑ ነገሮችን ከማድረግም መቆጠብ እንደሚገባ ዶክተር አክሊሉ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ጤናማና ንቁ ልጅ ወልዶ ለመሳምና የእርግዝና ወራትን በሰላም ለማጠናቀቅ፣ ይቻል ዘንድ በእርግዝና ወቅት የሚያጋጥሙትን የተለያዩ አዕምሮቶችን በብልሃትና በጥንቃቄ ማለፍ እንዳለባቸው ነፍሰጡር ሴቶች ሁሉ ሊገነዘቡት ይገባል፡፡

በአዲስ አድማስ / Saturday, 18 January 2014 ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *