በምግብ ሰዓቶች መኃል ሊርብሽ ይችላል። ስኳርና ቅባት ያላቸውን ምግቦች አትመገቢ፣ በምትኩ
- ፍራፍሬዎች
- የአትክልት ሰላጣ
- የአበባ ጎመን፣ የሾላ ፍሬ
- የአትክልትና የባቄላ ሾርባ
- ከተመጣጠነ እህል የተዘጋጀ ገንፎና ወተት
ካፊን – Coffee
ብዙ ካፊን ህፃናት ሲወለዱ አነስተኛ ክብደት እንዲኖራቸው ያደርጋል ይህ የወደፊት ህይወታቸው ላይ የጤና ችግር ሊያመጣ ይችላል። በጣም ከበዛ ውርጃም ሊያመጣ ይችላል። ካፊን በተፈጥሮ ብዙ አይነት ምግቦች ውስጥ ይገኛል፤ እንደ ቡና፣ ሻይ፣ ቸኮሌት እና አንዳንድ ለስለሳ መጠጦች ተጠቃሽ ናቸው። አንዳንድ የጉንፋን መድሃኒቶች ውስጥም ይገኛል፣ ከመውሰድሽ በፊት ሐኪም አማክሪ።
ካፊን ባጠቃላይ አቁሚ ማለት አይደለም ነገር ግን መጠኑን ቀንሺ፣ በቀን ከ 200 ሚ.ግ የበለጠ አትውሰጂ።
በተለያዩ ምግብና መጠጥ ውስጥ የካፊን መጠን
- አንድ ትልቁ የሻይ ሲኒ ፈጣን ቡና(instant coffee)- 100ሚ.ግ
- አንድ ትልቁ የሻይ ሲኒ የተጣራ ቡና- 140 ሚ.ግ
- አንድ ትልቁ የሻይ ሲኒ ሻይ – 75 ሚ.ግ
- 50 ግራም ንፁህ ቸኮሌት – 50 ሚ.ግ
ተጨማሪ መረጃዎች
ምግብ ስታዘጋጂ
- ፍራፍሬዎችንና አትክልት ስተመገቢ በደንብ እጠቢው ልጅሽን ሊጎዳው የሚችል ተዋስያን ሊኖረው ስለሚችል ምንም አይነት አፈር እላው ላይ አለመኖሩን አረጋግጪ።
- የተዘጋጁ ምግቦችን በደንብ ሳታሞቂ እንዳትበዪ
- የተረፈ ምግብ ፍሪጅ ውስጥ አስቀምጪ ከሁለት ቀን በላይ የሆነው ምግብ አትብዪ።
- ምግብ ምታዘጋጂባቸውን እቃዎች በደንብ እጠቢ።
የሰውነትሽ ክብደት
ብዙ ሴቶች በእርግዝና ወቅት ከ10 እስከ 12.5 ኪ.ግ ክበደት ይጨምራሉ። የሚጨምረው የሰውነት ክበደት መጠን ከሰው ሰው ይለያያል፣ ከእርግዝና በፊት ያለው ክብደትሽ ላይም ይወሰናል።
አብዛኛው ክብደት የሚመጣው በፅንሱ ማደግ ምክንያት ነው። ክብደት በጣም መጨመር ጤናሽን ያጓድለዋል ለደም ግፊት የመጋለጥ ዕድልሽንም ይጨምረዋል። በዚያው ልክ ግን ክብደት ላለመጨመር ብለሽ ምግብ መቀነስ የለብሽም። ምክንያቱም ይህ ልጅሽ ሲወለድ ህይወቱን አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል አነስተኛ ክብደት እንዲኖረው ሊያደርግ ይችላል።
ሁሌም የምታደርጊያቸውን የቀን ተቀን እንቅስቃሴዎችሽን ቀጥዪ ቀለል ያሉ እንቅስቃሴዎችን አድርጊ። ክብደትሽ ከ100 ኪ.ግ በላይ ወይንም ከ50ኪ.ግ በታች ከሆነ ሐኪምሽን ማማከር አለብሽ።
ስጋ ማትመገቢ ከሆንሽ
የተመጣጠነ የተለያዩ አትክልቶችን መመገብ በቂ የንጥረ ነገሮች ምንጭ ነው። ነገር ግን በቂ አይረንና ቪታሚን ቢ 12 አታገኚም ስለዚህ እነዚህን በጣም አስፈላጊ የሆኑ ንጥረነገሮችን ለማግኘት ሐኪም ማማከር አለብሽ።