ጥሬ ወይም ያልበሰለ እንቁላል
እንቁላል ብቻውንም ይሁን ከሌላ ምግብ ጋር ተቀላቅሎ ስትመገቢ ቢጫውም ነጩም ክፍል በደንብ መብሰላቸውን አረጋግጪ። ይህ የምግብ መመረዝን ይከላከላል።
ጥሬና በደንብ ያልበሰለ ስጋ
ስጋም ይሁን የዶሮ ስጋ ስትመገቢ ምንም አይነት ሮዝ(ያልበሰለ) ስጋ ወይም ደም እንዳይኖረው በደንብ አብስይው። ቋሊማ እና የተፈጨ ስጋ ስትመገቢ ልዩ ጥንቃቄ ማድረግ አለብሽ። የተጠበሰ ስጋ ውጫዊ ክፍሉ በደንብ ከበሰለ መመገብ ትችያለሽ
ቪታሚን ኤ
ማንኛውንም አይነት በኪኒን መልክ የተዘጋጁ ቪታሚን ኤ ምንጮች ለምሳሌ የዓሳ ጉበት ዘይት አትውሰጂ። ባጠቃላይ ቪታሚን ኤ ያላቸውን ምግቦች በሙሉ አቁሚ ማለት አደለም ቪታሚን ኤ ለፅንሱ እድገት አስፈላጊ ነው። ብዙ ቪታሚን ኤ ፅንሱ ላይ ጉዳት ያመጣል።
ጉበት
ጉበት አለመመገብ ይመከራል፣ ምክንያቱም በውስጡ ልጅሽን ሊጎዳ የሚችል ብዙ መጠን ያለው ቪታሚን ኤ ሊይዝ ይችላል።
አንዳንድ የዓሳ ዘሮች
አንዳንድ የዓሳ ዘሮች በውስጣቸው ሜርኩሪ የሚባለውን ማዕድን ስለያዙ የፅንሱ ነርቭ ስርዓት ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ። ቱና ተመጋቢ ከሆንሽ የምትወስጂውን መጠን መቀነስ አለብሽ፣ በሳምንት መካከለኛ መጠን ያለውን ጣሳ አራት ጊዜ መመገብ ትችያለሽ። ቅባት ያላቸውን የዓሳ ዘሮች በሳምንት ከሁለት ጊዜ በላይ አትመገቢ።
ፓሰቸራይዝድ ያልሆነ ወተት
መጠጣት ያለብሽ ፈልቶ በመቀዝቀዝ ከተዋስያን የፀዳ ወተት መሆን አለበት። የምታገኚው ጥሬ ወተት ከሆነ አፍይው። ፓሰቸራይዝድ ያልሆነ የፍየል ወይም የበግ ወተትም ይሁን ተዋፆዎች እንዳትጠቀሚ።