ፎሊክ አሲድ

የፎሊክ አሲድን ነገር አደራ!

ፎሊክ አሲድ በውኃ የሚሟሟ ቫይታሚን ቢ 9 የተባለ ንጥረ ነገር ነው። ፎሊክ አሲድ ሰዉነታችን ቀይ የደም ህዋሳትንና አዳዲስ ህዋሳትን እንዲፈጥር ይረዳዋል። በእግዝና ወቅት ፎሊክ አሲድ ንጥረ ነገሮችን የያዙ ምግቦችን መመገብ አስፈላጊ ነዉ።

በእርግዝና ወቅት በቂ ፎሊክ አሲድ በምግባቸዉ ዉስጥ የማያገኙ ሴቶች አኔሚኒያ (በተለምዶ ደም ማነስ) የተባለዉ የደም በሽታ ሊያጠቃቸዉ ይችላል። ፎሊክ አሲድ ስላነሳቸዉ ደማቸዉ በቂ ኦክሲጂንን አይሸከምም፤ ስለዚህም የድካምና የመዝለፍለፍ ችግር ያጋጥማቸዋል። ህፃናትም በቂ ፎሊክ አሲድ ካላገኙ እድገታቸዉ ይስተጓጎላል።

በእርግዝና ወቅትም ሆነ ከወሊድ ቡኋላ ሴት ልጅ በቂ ፎሊክ አሲድ ማግኘት ይኖርባታል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሰዉነታችን በመድሃኒት መልኩ የሚዘጋጅን የፎሊክ አሲድ ከምግብ ከምናገኘው የበለጠ  ያብላላል።

ፎሊክ አሲድን በመድሃኒትነት መልክ እርጉዝ ሴቶች በየሆስፒታሉ ማግኘት ይችላሉ።

በእርግዝና ወቅት እናትየዉ በቂ ፎሊክ አሲድ ካላገኘች እነዚህን ምልክቶች ይታዩባታል፤  ማስቀመጥ፣ የምግብ የመብላት ፍላጎት ማነስ፣  ድካም፣ የራስ ምታት እና የመሳሰሉት። እናትየዉ በእርግዝና ወቅትም ሆነ ከእርግዝና በፊት ከ0.4 እስከ 0.8 ሚሊግራም ፎሊክ አሲድ በየቀኑ ማግኘት አለባት። የሚያጠቡ እናቶች ደግሞ 0.5ሚሊግራም ማግኘት አለባቸዉ። ሀኪምን በማናገር ማዘዣ ማግኘት ይቻላል።

በተጨማሪም ፎሊክ አሲድን ከተለያዩ የምግብ አይነቶች ማግኘት ይቻላል። ለምሳሌ ከቅጠላቅጠል ምግቦች ባቄላ ቦሎቄ ምስር  እንቁላል ኦቾሎኒ ፓስታ እንዲሁም ጉበት ብሪኮሊ ሩዝ ቶፉ በዋናነት ይጠቀሳሉ። ሌሎችም አረንጓዴ ቅጠላቅጠሎችም ዉስጥ ፎሊክ አሲድ አለ።

ለምሳሌ ያህል ነፍሰ ጡር የሆነችው ሴት ፎሊክ አሲድ የተባለውን ንጥረ ምግብ በበቂ መጠን ካገኘች ጽንሱ የነርቭ ቱቦው በአግባቡ ሳይዘጋ በመቅረቱ ምክንያት በሚመጣ ስፒና ባይፊዳ በተባለ የነርቭ እክል እንዳይጠቃ ማድረግ ትችላለች። የሽሉ የነርቭ ቱቦ የሚዘጋው በተጸነሰ ከ24ኛው እስከ 28ኛው ቀን ባለው ጊዜ ማለትም ብዙ ሴቶች ማርገዛቸውን ከማወቃቸው ከብዙ ቀን በፊት በመሆኑ ለማርገዝ የፈለጉ አንዳንድ ሴቶች ቀደም ብለው ፎሊክ አሲድ መውሰድ ይጀምራሉ።

የፎሊክ አሲድን  መገኛ

ፎሊክ አሲድን ከተለያዩ የምግብ አይነቶች ማግኘት ይቻላል፡፡

  • ፎሊክ አሲድን የምናገኘዉ ከተፈጥራዊ አረንጓዴ አታክልቶች እና ከተለያዩ ቅጠላቅጠል ምግቦች ላይ እናገኛለን ለምሳሌ፡- ባቄላ ቦሎቄ ምስር  እንቁላል ኦቾሎኒ ፓስታ እንዲሁም ብሪኮሊ ሩዝ ቶፉ በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ ሌሎችም አረንጓዴ ቅጠላቅጠሎችም ዉስጥ ፎሊክ አሲድ አለ፡፡
  • የተለያዩ ፍራፍሬዎች ዉስጥ ለምሳሌ – ብርቱካን ፣አቮካዶ፣ሎሚ እና ሙዝ ዉስጥ በብዛት እናገኛለን፡፡
  • ሌላዉ የፎሊክ አሲድ መገኛ በስጋ ዉስጥ ለምሳሌ የበሬ ጉበት ዉስጥ በብዛት ይገኛል ነገር ግን የበሬ ጉበት በቫይታሚን A በብዛት ስላለዉ እርጉዝ ሴት መዉሰድ የለባትም፡፡

የፎሊክ አሲድ  እጥረት ሲከሰት የሚያሳዩ ምልክቶች

  • ፎሊክ አሲድ DNA ላይ ነዉ ስራዉ ስለዚህም እጥረቱ ሲከሰት የወደፊቱ የአንጎላችን  እና የሰረሰር የሚሰራዉ ክፍል ስለሚጎዳ በአግባቡ ሳይዘጋ ስለሚቀር  ጭንቅላታችን በአንጎሉ፣ሰረሰሩ፣ወይም አንገታችን ስር ሊሆን ይችላል በዚህ ጊዜ ኑዉራል ቱብ ድፌክት የሚባል ችግር ይፈጠራል፡፡ ይህ ማለት አንጎላችን ሳይዘጋ ሲቀር ቀላል ጉዳት የሚባለዉ የአንጎል ዉሃ መፍሰስ ወይም ከፍተኛዉ ጉዳት ደግሞ የአንጎሉ መዉጣት ነዉ፡፡

የነርቭ ስርኣት ችግር በፎሊክ አሲድ እጥረት ምክንያት የሚመጣዉ ችግር ነዉ፡፡

በእርግዝና ጊዜ አንዲት እናት ፎሊክ አሲድን ከወሰደች ከ40-50 ያህሉ ህጻናት ለዚህ ችግር ተጋላጭ አይሆኑም፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *