ልጃችሁ በሆዳችሁ ውስጥ ምን ያደርጋል?
ጽንሱ በሆድ ውስጥ ሲንቀሳቀስ አስደሳች ስሜት ለእናቲቱ ይፈጥራል:: ህጻኑም በመላው የእርግዝና ጊዜያቶች ውስጥ ንቁ ነው::
የጽንሱ እንቅስቃሴ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰማዎት ከ 16-22 ባሉት ሳምንታት ውስጥ ነው:: በፊት ወልደው ለሚያውቁ ሴቶች ይህ ስሜት ቀደም ብሎ ሊመጣ ይችላል። በመጀመሪያ የጽንሱ እንቅስቃሴ በአብዛኛው አይሰማዎትም፤ አልያም የማህፀን እንቅስቃሴ በሳምንት አንድ ሁለት ጊዜ ብቻ ይሰማና ከትንሽ ጊዜ በኋላ እንቅስቃሴው በየቀኑ ይሰማል።
ጽንሱ በሚያድግበት ጊዜ፣ እንቅስቃሴው በጉልህ ይሰማዎታል በሂደትም እንቅስቃሴው በይበልጥ ይሰማዎታል:: ምናልባት ግን ትንንሽ እንቅስቃሴዎች ላይሰማዎት ይችላሉ፣ ለምሳሌ አውራጣታቸውን ሲመጠምጡ ወይም የእጅ እና የእግር ጣቶቻቸውን ሲያሳስቡ ስሜቱን ላታደምጡት ትችላላችሁ::
በመጨረሻዎቹ የእርግዝና ጊዚያቶች ደግሞ አንዳንድ ምቶችንና መገላበጦችን ምናልባት ስርቅታንም ሊያደምጡ ይችላሉ:: እነዚህ ሁሉ እንቅስቃሴዎች በመጨረሻዎቹ የእርግዝና ጊዜያት በጉልህ የሚታወቅዎት ሲሆኑ ምጥ እስከሚጀምርበት ሰዓት ድረስ ሊዘልቁ ይችላሉ::