የተፈጥሮ ወሊድ እና የሲ

የተፈጥሮ ወሊድ ለህጻኑም ሆነ ለእናቲት ከ ሲ-ሴክሽን (ቀዶ ጥገና) ወሊድ በጣም ደህንነት ያለው ነው::  አንዳንድ ጊዜ ለምሳሌ የህጻኑ አቀማመጥ በሆድ ውስጥ ወደጎንና ወደጎን ከሆነ ወይም የእንግዴ ልጁ ሰርቪክስን (የማህፀን በርንወይም ህፅንተ አንገትን) (የእንግዴልጅ ፕሪቪያ) ከሸፈነ፤ የ ሲ-ሴክሽን ወሊድ ብቸኛ አማራጭ ይሆናል:: በአንዳንድ ሁኔታዎች ሲ-ሴክሽን የተወሰነ ጥቅም ይኖረዋል፤ ጉዳቱና ጥቅሙን ማመዛዘን ያስፈልጋል:: ጥቅሙንም ሆነ ጉዳቱን ከህክምና ባለሙያዎች በመረዳት፤ የሚጠቅመውን መወሰን የጥንዶቹ መብት ነው::

ጥቅሙ መሰረት የሚያደርገው በእርግዝናና በምጥ ወቅት ባለው ሂደት ይሆናል:: የህክምና ባለሙያው ወይም አዋላጇ ምጥ ወይም ተፈጥሯዊ ወሊድ ለህጻኑም ሆነ ለእናት አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል ካሰቡ የሲ-ሴክሽን ወሊድ ይመክራሉ፡፡ ለምሳሌ፣ በቂጡ በኩል የዞረን ህጻን ለመውለድ አስቸጋሪ ይሆናል፣ በዚህ አይነት አቀማመጥ ያሉትን በተፈጥሯዊ ወሊድ ለማድረግ መሞከር ህጻኑን ሊጎዳ ይችላል:: ወይም በምጥ ጊዜ የጽንሱ የልብ ምት ለውጥ ካሳየ፣ ህጻኑ በቂ ኦክስጅን እያገኘ አለመሆኑን ያመለክታል:: በእነዚህ የተለዩ ሁኔታዎች፣ የሲ-ሴክሽን ወሊድ ህጻኑ የመጎዳቱን እድል ይቀንሰዋል::

ምንም እንኳ ምጥ እና ተፈጥሯዊ ወሊድ ከባድ ስራ ቢሆንም፣ ከቀዶ ጥገና ወሊድ ሲነጻጸር በጥቅሉ ለሴቶች አካል ቀለል ያለ ነው:: ከሲ-ሴክሽን ወሊድ በተለየ ተፈጥሯዊ ወሊድ በተለምዶ የማገገም ሂደቱ አጭር እና ያነሰ ህመም ያለው ነው፤ እንዲሁም ሴቶች ከልጆቻቸው ጋር ይበልጥ ጊዜ እንዲኖራቸው ያደርጋል:: አዳዲስ ጥናቶች እንደሚያመለክቱትም ምጥ እና ተፈጥሯዊ ወሊድ ለህጻናቱም ጥሩ ናቸው:: ምጥን እንዲጀምር የሚያደርገውና የሚያስቀጥለው ሆርሞንም ልጁ ለመወለድ ዝግጁ እንዲሆን ይረዳል፣ አንዳንድ የመተንፈሻ አካል ችግሮችንም ይቀንሳል:: በተፈጥሮ የሚወለዱ ህጻናትም ከባድ ከሚባሉት የህጻናት በሽታዎች እንደእነ አስም፣ ስኳርና አላርጂክ የመያዝ እድላቸው አናሳ ነው፤ ለተጋነነ ውፍረትም አይጋለጡም:: አጥኚወች እንደሚያስቡትም ይህን ጥቅም የሚያገኙት በወሊድ ጊዜ ለጤናማ ባክቴሪያወች ስለሚጋለጡ እንደሆነ ነው::

ሲ-ሴክሽን ቀዶ ጥገና እንደሆነ የታወቀ ሀቅ ነው:: ሁሉም ቀዶ ጥገናዎችም የራሳቸው የሆነ አደጋ አላቸው፤ ልክ እንደ ኢንፌክሽን፣ የሰውነት ክፍሎች እና የደም ቱቦዎች ላይ የሚደርስ ቁስልና የደም መፍሰስ:: ሲ-ሴክሽን በህጻናት ላይም ችግር ያመጣል፣ እንደ መተንፈሻ አካል ችግሮች ስለዚህም በጨቅላ ህጻናት ክትትል ክፍል ወይም ኢንተንሲቭ ኬር ዩኒት ህክምና ያስፈልጋቸዋል:: ከሲ-ሴክሽን በኋላ ያለ የማገገም ሂደትም ከተፈጥራዊ ወሊድ አንጻር አስቸጋሪ ነው:: ለበለጠ መረጃ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *