ከዚህ በታች እንደተብራራው፣ ልጁን በጉጉት እንደሚጠብቅ አባት በእርግዝና ሂደት ውስጥ የምትሳተፉበት የተለያየ መንገድ አለ፥
- ከወሊድ በፊት ባሉት ቀጠሮወች ከባለቤታችሁ ጋር የህክምና ቀጠሮ ቦታወች ዘንድ በመገኘት ልጃችሁ እንዴት እያደገ እያለ ተመልከቱ፣ ምናልባትም ደግሞ የልጃችሁን የልብ ምት ልታደምጡ ትችላላችሁ::
- በአልትራሳውንድ እና በቀን አቆጣጠር ስካን ላይ ከባለቤታችሁ ጋር መገኘት:: ይህም ልጃችሁ ምን እንደሚመስል ማየት የሚያስችላችሁ እና ወደ ቤታችሁ የምትወስዱት ፎቶ እንድታገኙ ያስችላችኋል::
- መረጃ ይኑራችሁ _ ስለ እርግዝና እና ስለ ወሊድ አንብቡ:: ይህም የእርግዝና መሰረታዊ ሀሳብ እንዲኖራችሁ እንዲሁም በምጥ እና በወሊድ ጊዜ ምን መጠበቅ እንዳለባችሁ የሚያስችላችሁ ነው::
- አንተ እና ባለቤትህ ጥሩ ስሜት እንዲኖራችሁ ለልጃችሁ የሚያስፈልጉትን ነገሮች መሸመት::
- የሴትም ሆነ የወንድ የስም ዝርዝሮችን በማውጣት የትኛውን ስም እንደምትመርጡ ከባለቤታችሁ ጋር መወያየት፣ በ5ኛው ወር የአልትራሳውንድ ስካን የልጃችሁን ጾታ የማወቅ አጋጣሚውን ልታገኙ ትችላላችሁ፤ ምንም እንኳ፣ ያልታሰበ አስደናቂ ነገር እንዲሆን ከፈለጋችሁ ሁለት አይነት የስም ዝርዝሮችን ማውጣት ትችላላችሁ::
- የህመም ማስታገሻ መንገዶችን እንዲሁም በምንአይነት ጊዜ ልጃችሁን መውለድ እንዳለባችሁ የወሊድ ጊዜ እቅድ ማውጣት:: ሀሳባችሁን በመግለጽ ተሳትፎ ማድረግ፣ ግን ልዩ የወሊድ ጊዜ እንዲኖራችሁ የባለቤታችሁንም ሀሳብ ማድመጥ ይገባችኋል::
- የወሊድ ፈቃድ:- አብዛኞቹ ቀጣሪወች የወሊድ ፈቃድ ለአባቶች ይሰጣሉ፣ ይህንንም ከአሰሪዎቻችሁ ዘንድ ተወያዩበት::