የት እና ማን እንደሚያዋልድሽ ማወቅ
ከጤና ባለሙያ ጋር በመሆን የት ለመውለድ እንዳሰባችሁ ማቀድ ያስፈልጋል።
በቅርብ የሚገኘው የጤና ማዕከል ወይም ሆስፒታል የት እንደሚገኝ ማወቁ ጠቃሚ ነው።
ለሕክምና እና ለትራንስፖርት ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያስፈልግ ማቀድ በእርግዝና ወቅትም ሆነ ከእርግዝና በኋላ ወላጆች የተለያዩ ወጪዎች ይኖሩባቸዋል።
ስለዚህ በእርግዝና ጊዜ በየወሩ የተወሰነ ገንዘብ ተቀማጭ ማድረጉ አስፈላጊ ነው። በተጨማሪም በእርግዝና ወቅት ወደ ህክምና ቦታ ለመሄድ እንዲሁም ምጥ በሚመጣበት ጊዜ ለመውለድ ወደታቀደበት ተቋም ለመሄድ መጓጓዣ ቀድሞ ማዘጋጀት ያስፈልጋል።
ለምሳሌ፡- ታክሲ አናግሮ የሹፌሩን ስልክ መያዝ ወይም መኪና ያለውን ዘመድ አናግሮ ተዘጋጅቶ መጠበቅ በጣም አስፈላጊ ነው።