ወሊድ

የወሊድ ዕቅድ ማውጣት በወሊድ ጊዜ ብዙ ሁኔታዎችን በምትፈልጓቸው መልኩ ለማመቻቸት ይረዳችኋል።

የወሊድ ዕቅዳችሁን በምታወጡበት ጊዜ ልታስቧቸው ከሚገቡ ነገሮች መካከል ጥቂቶቹ፡-

  • ለመጓጓዣና ለተለያዩ የሕክምና ወጪዎች ገንዘብ ማዘጋጀት፤
  • መጓጓዣ በቀላሉ የሚገኝበትን መንገድ ማመቻቸት፤
  • በወሊድ ወቅት ሊረዳ የሚችል የቤተሰብ አባል በቅርብ እንዲኖር ማድረግ፣
  • ለህፃኑ የሚሆን ልብሶችና የመኝታ ቦታ ማመቻቸት፤
  • ከወሊድ በኋላ እናቲቱ የምትመገበውን ምግብ ቀደም ብሎ ማሰናዳት።

የምጥ ምልክቶች

የምጥ ምልክቶች የሚባሉት ከባድ የሆድ ቁርጠት፣ ከባድ የሆነ መድከም፣ ከብልት የሚወርድ ፈሳሽ መጨመር እና መወፈር፣ የደም መታየት፣ የጀርባ ህመም በዋናነት ይጠቀሳሉ። እነዚህን ምልክቶች ሲታዩ ወደ ጤና ተቋም በቶሎ መሄድ ያስፈልጋል ወይም አምቡላንስ (በ907) ደዉለዉ በመጥራት ቶሎ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ።

ከላይ እንደተገለፀው 39ነኛ ሳምንት ላይ ሙሉ የእርግዝና ጊዜሽ እንደሞላ ይታመናል፣ ማለትም ምጥ በየትኛውም ሰዓት ሊጀምር ይችላል ማለት ነው።

የመጀመሪያዎቹ ምልክቶች የሚቀጥለውን ያካትታሉ

  • በአንድ ሰዓት ውስጥ አቀማመጥሽን ብትቀይሪው እንኳን የማይቆም ከ 5 ጊዜ በላይ የሆነ ከ30-70 ሰከንድ የሚቆይ ቁርጠት
  • መድማት
  • ከማህፀን የሚወጣ ፈሳሽ መቀየር
  • ቡናማ፣ ሮዝማ ወይም ደም ያለው ንፍጥ መሰል ፈሳሽ መታየት
  • ብዙ የጠራ ቀጭን ውሃ መሰል ፈሳሽ ወይም ሽርት ውሃ መንጠባጠብ፣ ሽርት ውሃ መፈሰስ መጀመርን ያመለክታል
  • ቀጣይነት ያለው ወይም መጣ ሄድ የሚል የሚርገበገብ የጀርባ ህመም
  • ማቅለሽለሽ እና ማስቀመጥ

በሕክምና ምጥ እንዲመጣ ወይም እንዲፋጠን ማድረግ

ልጁ ወደ አለም ከመቀላቀሉ በፊት የውስጥ አካላቶቹ እና ስርዓቶቹ የተቻለውን ያክል እድገታቸውን ጨርሰው እንዲወጡ ሐኪሞች  40ኛ ሳምንቱን በማህፀን ውስጥ ቢጨርስ ይመርጣሉ ። ነገር ግን ሐኪምሽ በሕክምና ምጥ እንዲመጣብሽ ለማድረግ የሚያስወስኑት ብዙ ምክንያቶች አሉ። በእርግዝና የሚመጡ የደም ግፊት እና ስኳር ወይም ልጁን ሊጎዳው በሚችል ኢንፌክሽን መያዝ ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ። ሌሎች ምክንያቶች የሽርት ውሃ ማነስ፣ ምጥ ከመጀመሩ በፊት የሽርት ውሃ መፍሰስ እና እንደ የኩላሊት ጠጠር ያሉ ሌሎች ሁኔታዎች ሊሆኑ ይችላሉ።

በተፈጥሮአዊ መንገድ ምጥን ማፋጠን

የጎሎ ዘይት፣የቀይ እንጆሪ ሻይ ቅጠል፣ በፀደይ ወቅት የሚበቅል ቢጫ አበባ እና የበልሰም ኮምጣጤ የሚታወቁ ጥሩ የምጥ ማፋጠኛ መንገዶች ናቸው። አናናስ፣ ማደርቻ፣ ቅመም የሚበዛባቸው ምግቦችም በብዙዎች ዘንድ ምጥን ለማፋጠን እንደሚረዱ ይታመናል፣ ነገር ግን ጉዳት እንደሌላቸውና ውጤታማነታቸው ላይ የተደረጉ ጥናቶች የሉም፣ ስለዚህ ከመጠቀምሽ በፊት ሐኪምሽን ማማከር አለብሽ።

መቼ ነው ወደ ሐኪም መሄድ ያለብሽ

  • የልጅሽ እንቅስቃሴ መቀነስ ሲሰማሽ
  • ከላይ የተጠቀሱት የምጥ ስሜቶች ካሉሽ
  • ድንገተኛ የሆና የእይታ ብዥ ማለት፣ በእራስ ምታት የታጀበ ከፍተኛ ድካምና ማዞር፣ ከእምብርት በላይ የሆድ ክፍል ህመም፣ ድነገተኛ የፊትና የእጅ ማበጥ፣ የትንፋሽ ማጠር፣ ድንገተኛ ሰውነት መጨመር፣ ማቅለሽለሽና ማስመለስ( የደም ግፊት መጨመርንና በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት ደም ግፊትን ሊያመለክት ይችላል)
  • ሽንትሽን ስትሸኚ የማቃጠል ስሜት፣ ደመናማ ወይም ጠቆር ያለ ሽንት ሽታ ከጀርባ ሕመም ጋር(ኩላሊት አካባቢ)፣ ወፍራም ነጭ ወይም አረንጓዴአማ ቢጫ ዝልግልግ ፈሳሽ፣ በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ የህመም ስሜት፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ እና ማስቀመጥ ( የኩላሊት/የፈንገስ ወይም የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽንንሊያመለክት ይችላል)
  • በድካም የታጀበ ከፍተኛ ውሃ መጥማትና የአፍ መድረቅ፣ ማቅለሽለሽ፣ ከበፊቱ በበለጠ ሽንት መምጣጥ፣ የሽንት መጠን ማነስ(በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት ስኳር ህመምን ሊያመለክት ይችላል)
  • በአንድ በኩል ብቻ ማበጥ ወይም አንድ እጅ ወይም እግር ከሌላው በበለጠ ማበጥ(የደም መርጋት ችግርን ሊያመለክት ይችላል)

የት እና ማን እንደሚያዋልድሽ ማወቅ

ከጤና ባለሙያ ጋር በመሆን የት ለመውለድ እንዳሰባችሁ ማቀድ ያስፈልጋል።

በቅርብ የሚገኘው የጤና ማዕከል ወይም ሆስፒታል የት እንደሚገኝ ማወቁ ጠቃሚ ነው።

ለሕክምና እና ለትራንስፖርት ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያስፈልግ ማቀድ በእርግዝና ወቅትም ሆነ ከእርግዝና በኋላ ወላጆች የተለያዩ ወጪዎች ይኖሩባቸዋል።

ስለዚህ በእርግዝና ጊዜ በየወሩ የተወሰነ ገንዘብ ተቀማጭ ማድረጉ አስፈላጊ ነው። በተጨማሪም በእርግዝና ወቅት ወደ ህክምና ቦታ ለመሄድ እንዲሁም ምጥ በሚመጣበት ጊዜ ለመውለድ ወደታቀደበት ተቋም ለመሄድ መጓጓዣ ቀድሞ ማዘጋጀት ያስፈልጋል።

ለምሳሌ፡-  ታክሲ አናግሮ የሹፌሩን ስልክ መያዝ ወይም መኪና ያለውን ዘመድ አናግሮ ተዘጋጅቶ

መጠበቅ በጣም አስፈላጊ ነው።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *