በ39ኛው ሳምንት

39ነኛው ሳምንትሽ ላይ እርግዝናሽ የመጨረሻ ሳምንቱ ላይ ደርሷል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ማለትም ልጅሽ በማንኛውም ሰዓት ሊወለድ ይችላል፡፡ በአሜሪካ ፅንስና ማህፀን ሐኪሞች ኮሌጅ በተደረገ ጥናት ከ39ነኛ ሳምንት በኃላ የተወለደ ህፃን ከአተነፋፈስ፣ ከሙቀት መቆጣጠር እና አመጋገብ እንዲሁም እንደ ከባድ ኢንፌክሽን እና ሽባ መሆን ላሉ ችግሮች የመጋለጥ እድሎቹ ይቀንሳሉ፡፡

የልጁ እድገት

 የአንጎል እድገት

የልጅሽ አንጎል በፍጥንት እያደገ ነው ፣ ከ 4 ሳምንት በፊት ከነበረው 30% ያክል አድጓል፡፡ ህፃኑ 3 ዓመት እስከሚሞላው ድረስ የአንጎል እድገት በዚሁ ፍጥነት ይቀጥላል፡፡

የቆዳ እና የቆዳ ስብ እድገት

እያደገ ያለው የቆዳ ስብ የመጨረሻ የእድገት ደረጃው ላይ ደርሷል፣ በደምስር ዙሪያ የተከማቸው ጥቅጥቅ ያለ የስብ ንብርብር ልጅሽን ወፍራም ያስመስለዋል፡፡ በኃላ የቆዳ ቀለሙ ምንም ይሁን ምን በዚህ ጊዜ ቆዳው  ከቀይ መሰል ወደ ነጭ ይቀየራል፡፡ በመጀመሪያ አመቱ ትክክለኛ  ቀለሙን ይይዛል፡፡ በዚህ ጊዜ ያረጁ የቆዳ ህዋሳት እየወደቁ ከስር በሚያድጉት አዳዲስ የቆዳ ህዋሳት ይተካሉ፡፡

የውስጥ አካላት እድገት

ሆርሞን የሚያመነጨው የስርዓተ ዝግ ዕጢ  ብዙ የጫና ሆርሞኖችን በማምረት አራሱን ለመወለድ ያዘጋጃል በዚህ ጊዜ የሚመረተወው የጫና ሆርሞን ብዛት ልጅሽ በሕይወቱ ሙሉ ከሚያመርተው ይበልጣል፡፡ ይህ ሆርሞን ልጁ ከተውለድ በኃላ እንግዴ ልጁ ስለማይኖር በምትኩ የውስጥ አካላት እና ስርአቶች ስራቸውን እንዲያከናውኑ ይረዳል፡፡

እንደ አንጎልና ስረአተ ነርቭ፣ ሳንባም ልጅሽ እስከ ሚወለድበት ጊዜ ድረስ ማደጉን ይቀጥላል፡፡ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ  ሳንባ ልጁ የመጀመሪያ ትነፋሹን ሲተነፍስ የአየር ከረጢቶች እንዳይጣበቁ የሚያደርጉትን ገፀ አግባሪ(ሰርፋክታንት) እያመረቱ ነው፡፡ እንደውም ልጅሽ በዚህ ሳምንት ቢወለድ እንኳን ሳንባዎቹ ካለምንም እርዳታ መተንፈስ የሚያስችለው የእድገት ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡

በሽታ መከላከያ ስርዓት

እንግዴ ልጁ ለልጅሽ  የሚያስፈልገውን በሽታ መከላከያ እና አስፈለጊ ንጥረ ነገሮች በማቅረብ ከማህፀን ሲዎጣ በሽታ መከላከል እንዲችል ያዘጋጀዋል፡፡ ከተወለደ በኃላ ጡት ስታጠቢው ደግሞ የበለጠ በሽታ መከላከያዎችን ያገኛል፡፡

ልጅሽ ምን ያክል ትልቅ ነው?

ልጅሽ በ39ነኛው ሳምነት ላይ ርዝመቱ 50.8 ሴ.ሜ አካባቢ ሲሆን አማካኝ አዲስ የተወለደ ህፃን ቁመት ይኖረዋል ማለት ነው፡፡ ክበደቱ ደግሞ 3.29 ኪ.ግ አካባቢ ይሆናል፡፡

የልጁ አቀማመጥ

በዚህ ሰዓት ለመወለድ ዝግጁ ሆኖ የልጅሽ ጭንቅላት ወርዶ በዳሌ አጥንት መኃል ገብቶ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ምጥ ከተጀመረ በኃላ ሊስተካከልም ይችላል፡፡ ከ37ተኛው ሳምንት በኃላ ልጁ ወደታች መውረድ ይጀምራል፡ ተስተካክሎ ጭንቅላቱ ተዘቅዝቆ ለመወለድ ትክክለኛው አቀማመጥ ላይ ይሆናል፡፡ የሰውነቱ አቀማመጥ ቀጥ ያለ ወይንም አግድም ሊሆን ይችላል፡፡

ድንገት ልጅሽ ሳይገለበጥ እግሩ ወድታች ከሆነ ወይንም ወደጎን የተኛ ከሆነ ሐኪምሽ አንዳንድ ቦታዎችን ከውጪ ጫን በማለት የመገልበጥ ሃሳብን ሊያቀርብ ይችላል፡፡ ይህ መንገድ ካልሰራ እግሩ ወደታች የሆነ ህፃንን በማህፀን መውለድ ለህይወት አስጊ የሆኑ ችግሮችን ስለሚያስከትል በቀዶ ጥገና ለመውለድ ቀጠሮ ሊያዝ ይችላል፡፡

በሰውነትሽ ላይ የሚመጡ ለውጦች

በነዚህ የመጨረሻ ሳምንታት በማህፀንሽ ከሽርት ውሃው ይልቅ ብዙ ቦታ የሚይዘው ልጅሽ ስለሆነ አማካይ ክበደቱ ላይ በመድረሰ የሰውነት ክብደት መጨመርሽ ይቀንሳል ወይም ያቆማል፡፡

የልጅሽ ወደታች መውረድ ሆድሽ ወዳ ታች ዝቅ እንዲል ያደርገዋል፡፡ ነገር ግን የሆድሽ ወደ ታች ዝቅ ማለት ልጁ አሁኑኑ ይወለዳል ማለት አይደለም፣ ምክንያቱም ብዙ እርግዝናዎች ላይ ፅንሱ ወደ ታች የሚወርደው ምጥ ከመጀመሩ ከሳምንታት በፊት ነው  በተለይ የመጀመሪያ እርግዝና ሲሆን፡ የልጅሽ ወደታች ዝቅ ማለት ለጨጓራ እና ለሳንባ(መለጠጥ) ቦታ ስለሚኖራቸው የጨጓራ ማቃጠል፣ የምግብ አለመፈጨት ፣ የደረት ህመምእና የትንፋሽ ማጠር ስሜቶች ይታገሳሉ፡፡

በዚህ ሳምንት የሚደረጉ ምርመራዎች

በእርግዝና  የመጨረሻ ሦስት ወር ወቅት ወይም ከመውለድሽ በፊት ሊከሰት የሚችል የደም ግፊት መያዝ እድልን ለመመርመር በሁሉም ቅድመ ወሊድ ምረመራዎች ጊዜ ሐኪምሽ የደም ግፊትሽን ይለካሻል፡፡ ሌላው የተለመደ ምርመራ የፅንሱን ጤንነት ለማረጋገጥ የልጁን ልብ ምት ማየት እና የልጁን እድገት ለማወቅ ከጭን አጥንት እስከ ማህፀን አናት ድረስ ርዝመቱን መለካት ነው፡፡

ሌላው ሐኪምሽ ሊያደርግ የሚችለው ምርመራ ደግሞ የማህፀን በር ለልጁ መወለድ ለመዘጋጀት መለስለስ፣ መከፈት እና መሳሳት መጀመሩን መመርመር ነው፡፡

ልጁ መንቀሳቀስ ከቀነሰ፣ እንደ የሽርት ውሃ መቀነስ እና እንግዴ ልጅ መዛባት ያሉ ውስብስብ ችግሮች ሲያጋጥሙ ቅደመ ወሊድ ምርመራ  ሊታዘዝ ይችላል፡ ይህ ምርመራ የፅንሱን ልብ ምት ማየት እና አልትራሳወንድ ማድረግን ያካትታል፡፡

በ39ነኛው ሳምንት ላይ በአልትራሳወንድ የሚታየው ልጅሽ ሲወለድ ከሚመስለው ጋር በጣም የተቀራረበ ነው፡፡

 39ነኛ ሳምንት ምልክቶች

  • የዳሌ አጥንት ህመም
  • የማህፀን መኮማተር ወይም ጥብቅ የማለት ስሜት
  • የእግር መሸማቀቅ
  • ከእምብርት በታች ሆድ ላይ ወይም ዳሌ አካባቢ ጫና ስሜትናአልፎ አልፎ የሚሰማ ውጋት
  • የእጅና የእግር ማበጥ
  • እንቅልፍ ማጣት እና እና በእረፍት ጊዜ የሚያም የእግር ህመም
  • ከእምብርት በታች ሆድ ላይ ወይም ብልት አካባቢ የሚሰማ ውጋት
  • የመገጣጠሚያ(የጉልበት፣ የዳሌ እና መንገጭላ)፣ የጭን እና የጀርባ ህመም
  • ራስ ምታት እና ብርድ ብርድ ማለት
  • የጉሮሮ ህመም፣ ነስር ወይም ንፍጥ በንፍጥ መሆን
  • ድካም እና ማዞር
  • የቆዳ ሸንተረር በተለይ በሆድ እና ታፋ አካባቢ
  • ማሳከክ በተለይ በተወጠረው ሆድ አካባቢ እና ጡት አካባቢ
  • የደም ስር ማበጥ፣ ኪንታሮት
  • የሆድ ድርቀት ወይም ተቅማጥ
  • ድብርት እና ቶሎ ቶሎ የስሜት መለዋወጥ
  • ቶለ ቶሎ ሽንት መምጣት( ልጁ ወደ ታች በወረደ ቁጥር የሽንት ፊኛ ላይ የሚያሳድረው ጫና ይጨምራል)
  • ሰውነትሽ የልጅሽን የመጀመሪያ ወተት፣ በብዙ ንጥረ ነገሮች እና በሽታ መከላከያ የተሞላውን እንገር ማመንጨት ስለሚቀጥል ጡቶችሽ ማፍሰስ ይጀምራሉ

 

 

 

 

 

 

የምጥ ምልክቶች

 

ከላይ እንደተገለፀው 39ነኛ ሳምንት ላይ ሙሉ የእርግዝና ጊዜሽ እንደሞላ ይታመናል፣ ማለትም ምጥ በየትኛውም ሰዓት ሊጀምር ይችላል ማለት ነው፡፡

የመጀመሪያዎቹ ምልክቶች የሚቀጥለውን ያካትታሉ

  • በአንድ ሰዓት ውስጥ አቀማመጥሽን ብትቀይሪው እንኳን የማይቆም ከ 5 ጊዜ በላይ የሆነ ከ30-70 ሰከንድ የሚቆይ ቁርጠት
  • መድማት
  • ከማህፀን የሚወጣ ፈሳሽ መቀየር
  • ቡናማ፣ ሮዝማ ወይም ደም ያለው ንፍጥ መሰል ፈሳሽ መታየት
  • ብዙ የጠራ ቀጭን ውሃ መሰል ፈሳሽ ወይም ሽርት ውሃ መንጠባጠብ፣ ሽርት ውሃ መፈሰስ መጀመርን ያመለክታል
  • ቀጣይነት ያለው ወይም መጣ ሄድ የሚል የሚርገበገብ የጀርባ ህመም
  • ማቅለሽለሽ እና ማስቀመጥ

 

በሕክምና ምጥ እንዲመጣ ወይም እንዲፋጠን ማድረግ

ልጁ ወደ አለም ከመቀላቀሉ በፊት የውስጥ አካላቶቹ እና ስርዓቶቹ የተቻለውን ያክል እድገታቸውን ጨርሰው እንዲወጡ ሐኪሞች  40ኛ ሳምንቱን በማህፀን ውስጥ ቢጨርስ ይመርጣሉ ፡፡ ነገር ግን ሐኪምሽ በሕክምና ምጥ እንዲመጣብሽ ለማድረግ የሚያስወስኑት ብዙ ምክንያቶች አሉ፡፡ በእርግዝና የሚመጡ የደም ግፊት እና ስኳር ወይም ልጁን ሊጎዳው በሚችል ኢንፌክሽን መያዝ ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሌሎች ምክንያቶች የሽርት ውሃ ማነስ፣ ምጥ ከመጀመሩ በፊት የሽርት ውሃ መፍሰስ እና እንደ የኩላሊት ጠጠር ያሉ ሌሎች ሁኔታዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

በተፈጥሮአዊ መንገድ ምጥን ማፋጠን

የጎሎ ዘይት፣የቀይ እንጆሪ ሻይ ቅጠል፣ በፀደይ ወቅት የሚበቅል ቢጫ አበባ እና የበልሰም ኮምጣጤ የሚታወቁ ጥሩ የምጥ ማፋጠኛ መንገዶች ናቸው፡፡ አናናስ፣ ማደርቻ፣ ቅመም የሚበዛባቸው ምግቦችም በብዙዎች ዘንድ ምጥን ለማፋጠን እንደሚረዱ ይታመናል፣ ነገር ግን ጉዳት እንደሌላቸውና ውጤታማነታቸው ላይ የተደረጉ ጥናቶች የሉም፣ ስለዚህ ከመጠቀምሽ በፊት ሐኪምሽን ማማከር አለብሽ፡፡

መቼ ነው ወደ ሐኪም መሄድ ያለብሽ

  • የልጅሽ እንቅስቃሴ መቀነስ ሲሰማሽ
  • ከላይ የተጠቀሱት የምጥ ስሜቶች ካሉሽ
  • ድንገተኛ የሆና የእይታ ብዥ ማለት፣ በእራስ ምታት የታጀበ ከፍተኛ ድካምና ማዞር፣ ከእምብርት በላይ የሆድ ክፍል ህመም፣ ድነገተኛ የፊትና የእጅ ማበጥ፣ የትንፋሽ ማጠር፣ ድንገተኛ ሰውነት መጨመር፣ ማቅለሽለሽና ማስመለስ( የደም ግፊት መጨመርንና በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት ደም ግፊትን ሊያመለክት ይችላል)
  • ሽንትሽን ስትሸኚ የማቃጠል ስሜት፣ ደመናማ ወይም ጠቆር ያለ ሽንት ሽታ ከጀርባ ሕመም ጋር(ኩላሊት አካባቢ)፣ ወፍራም ነጭ ወይም አረንጓዴአማ ቢጫ ዝልግልግ ፈሳሽ፣ በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ የህመም ስሜት፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ እና ማስቀመጥ ( የኩላሊት/የፈንገስ ወይም የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽንንሊያመለክት ይችላል)
  • በድካም የታጀበ ከፍተኛ ውሃ መጥማትና የአፍ መድረቅ፣ ማቅለሽለሽ፣ ከበፊቱ በበለጠ ሽንት መምጣጥ፣ የሽንት መጠን ማነስ(በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት ስኳር ህመምን ሊያመለክት ይችላል)
  • በአንድ በኩል ብቻ ማበጥ ወይም አንድ እጅ ወይምእግር ከሌላው በበለጠ ማበጥ(የደም መርጋት ችግርን ሊያመለክት ይችላል)

 

ማህፀንውስጥበቂቦታስለሚኖርጽንሱእንደፈለገይገለባበጣል፤በየጊዜውበመገለባበጥየተለያዩአቀማመጦችንይይዛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *