እርግዝናን ማረጋገጥ

እርግዝና መኖሩን ለማረጋገጥ ቀላሉ መንገድ የእርግዝና ምርመራ ማድረግ ነው። ይህም በማንኛዉም የጤና ተቋም ወይም ክሊኒክ በመሄድ የሽንት ምርመራ በማድረግ ይታወቃል።

በሌላ በኩል አንዲት ሴት ማርገዝ አለማርገዟን ለማረጋገጥ ከፈለገች የእርግዝና ማረጋገጫ ቴስተር ከመድኃኒት ቤት በመግዛት ማረጋገጥ ትችላለች። መሳሪያውን ለመጠቀም መጀመሪያ ስለ አጠቃቀሙ የሚገልጸዉን መመሪያ መከተል አስፈላጊ ነዉ። የሽንት ናሙና በተዘጋጀው የፕላስቲክ ዕቃ ውስጥ ትንሽ ያህል ሽንት ከጨመርን በኋላ መሳሪያዉን ወይም የቴስተሩን ጫፍ በሽንቱ ዉስጥ በማስገባት ለ5 ደቂቃ ያክል ማቆየት ከዛም አዉጥቶ ዉጤቱን በማየት ማረጋገጥ ይቻላል።

ውጤቱ + ከሆነ እርግዝና ተከስቷል ማለት ነዉ ውጤቱከሆነ እርግዝና አልተከሰተም ማለት ነዉ።

የእርግዝና ማረጋገጫ  ቴስተር የተለያዩ አይነቶች ስላሉ አጠቃቀማቸዉም ሊለያይ ስለሚችል ከምትገዢበት መድሃኒት ቤት ጠይቀሽ አጠቃቀሙን እንዲያስረዱሽ ማድረግ ትቺያለሽ። ግን አንዳንድ ጊዜ ምርመራው በጣም በጊዜ ሲካሄድ ወይም በትክክል ካልተከናወነ ወይም መመርመሪያ መሣሪያው ችግር ካለበት ትክክለኛ ውጤት ላያሳይ ይችላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *