በ32ኛዉ ሳምንት

በዚህና በሚቀጥሉት ሳምንታት ወደ ግማሽ ኪሎ የሚጠጋ ክብደት በየሳምንቱ ትጨምሪያለሽነገር ግን ሊያሳስብሽ አይገባም ይህም ክብደት የልጅሽ ማደግ ተከትሎየሚመጣ ነዉ ፡፡

በሚቀጥሉት ሳምንታት ልጅሽ የሰዉነቱን ወደ ግማሽ የሚጠጋ ክብደት የሚጨምርበት ስለሆነ አብዛኛዉ ክብደት በልጅሽ እድገት ምክንያት እንደሆነ ማሰብ ትቺያለሽ፡፡ ልጅሽ እያደገ ነዉ፤ ጥፍር ይኖሩታል፣ የአይን ቅንድብይኖሩታል፣ እንዲሁም የጥርስ ቦታዉ እየተበጀለት ነዉ፡፡ ፀጉርም ማብቀል ይጀምራል፤ በተጨማሪም ልጅሽ አብዛኛዉን ቀን በእንቅልፍ ያሳልፋል፡፡ ቆዳዎቹም የሚያሟልጩ ይሆናሉ፡፡

የልጅሽ ክብደት 1.7 ኪሎግራም አከባቢ የሚጠጋ ሲሆን ርዝመቱም 42 ሴንቲሜትር አከባቢ ሊጠጋ ይችላል፡፡በዚህ ሳምንት የልጅሽ የአተነፋፈስ ዘይቤ መልክ እየያዘ ይመጣና40 እስትናፋሶችን በደቂቃ ማድረግ ይጀምራል፡፡ ሳንባዉ የበለጠ ለዉጪዉ አለም ዝግጁ እየሆነ ይሄዳል፡፡

በዚህ ሳምንት ልጅሽ በሆድሽ ዉስጥ ያለዉን ቦታ ለማብቃቃት ሲል ገልበጥ ይልና ጭንቅላቱ ወደ ታች መቀመጫዉ ወደ ላይ አድርጎ የቦታ ጥበቱን ያብቃቃል፡፡ በአብዛኛዉ የቦታ ጥበቱ የልጅሽ የሰዉነቱ ማደግ በመሆኑ ቦታዋን ማብቃቃት አለበት፡፡የጭንቅላቱ ክብደት ከመቀመጫዉ ክብደት የተለቀ ስለሆነ ጭንቅላቱን ወደ ታች ወደ ማህፀንሽበር አረጎ መቀመጫዉን ወደ ላይ ማድረጉ የተፈጥሮ ደንብ ነዉ፡፡

አንቺም በዚህ ሳምንት የሆድ ድርቀትና ማግሳት እንዲሁምንፋስ ወይም ፈስ ሊያመልጥሽ ይችላል፡፡ ሀይለኛ ድካምና እግሮችሽ አከባቢ የህመም ስሜት ሊኖርሽ ይችላል፡፡ በተጨማሪም ሆድሽ ከመለጠጡ የተነሳ የማሳከክ ባህሪ ቢያመጣም ሊያሳስብሽ አይገባም፡፡ከጡትሽም ነጣ ያለ ወይመ ወደ ቢጫነት የሚያደላ ወተት መሳይ ፈሳሽ ሊወጣ ይችላል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *