በ31ኛዉ ሳምንት

በ31ኛዉ ሳምንት የፅንሱ አማካኝ ርዝመት ወደ 40ሴንትሜትር ይጠጋል እንዲሁም ወደ 1.3ኪሎግራም ይመዝናል፡፡ የእንቅስቃሴው መጠን ከበፊቱ ይቀንሳል። ልጅሽ ሽንት መሽናት የሚጀምርበትወቅት ነዉ፤ በሆድሽ ዉስጥ እንደ ሽንት ያለ ፈሳሽ ነገር ይሸናል፤ ይህም ጤነኛ ነገር ስለሆነ ሊያሳስብሽ አይገባም፡፡

የልጅሽ የስሜት ሁዋሳቶች በጣም ያድጋሉ፤ዓይኖቹብርሃንና ጨለማን መለየት ችሏል፤ አፍንጫዉ ተስተካክሎ ተፈጥሯል፡፡ ምንም እንኳን በሆድሽ ዉስጥ አየር ባይኖርም በሆድሽ ዉስጥ የከበበዉን አምኖቲክ ፈሳሽ ዉስጥ ያለዉን ያንቺን ጠረን ማሽተት ይጀምራል፡፡ስለዚህ መጀመሪያ የሚያዉቀዉ የእናቱን ጠረን ስለሆነ ደስ ሊልሽ ይገባል፡፡

ልጅሽ ጨለማና ብርሃንን መለየት ቢችልም ነገር ግን የእንቅልፍ ዘይቤዉን ከጨለማና ከብርሃን ጋር ማድረግ ገና አልለመደም፡፡

በተጨማሪም ጆሮዎቹ መስማት እንዲሁም ሙዚቃን የማጣጣም ክህሎት ይኖረዋል፡፡ ስትናገሪለት እንዲሁም ሙዚቃም ስትዘፍኚለት ያዳምጣል፡፡ አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያመለክቱ ልጅሽ እንደሚሰማዉ ሙዚቃ የልብ ምቱና የልብ ትርታዉ ይጨምራልም ይቀንሳልም፡፡

ከዚህ ቡኃላ በየሳምንቱ ወደ 450 ግራም ወይም ወደ ግማሽ ኪሎ የሚጠጋ ክብደት ትጨምሪያለሽ፡፡ ከእናት እናት ቢለያይም በአብዛኛዉ የቃር ስሜት ሊያጠቃሽ ይችላል፡፡ ይህም የሚሆነዉ አንዱ ልጅሽ በሆድሽ ዉስጥ በሚገላበጥበት ጊዜ ግፊት በሆድሽ ላይ ስለሚያሳድር ነዉ፡፡ቃሩ ከበዛብሽ ሀኪም በማማከርየአንታይአሲድ መዉሰድ ትቺያለሽ ፡፡

በዚህ ሳምንት ጡቶችሽ እንደ ወተት የሚመስል ፈሳሽ ሊያወጣ ይችላል፡፡ ስለዚህም በጡት መያዣሽ ዉስጥ ትንሽዬ ጨርቅ መክተት ይመከራል፤ ይህ የሚያሳስብ አይደለም ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *