ሶስተኛው ሶስት ወራት

ሶስተኛው ሶስት ወር የእርግዝና የመጨረሻው ምዕራፍ ነው፣ ከ 37-40 ሳምንት ወይም ተጨማሪ ሳምንት ያካተተ ነው:: በዚህ ጊዜ ነው ለአዲሱ ልጃችሁ የምትዘጋጁት ምክንያቱም ታላቁ ቀን ከዚህ ብዙም አይርቅምና  ነው:: በምጥ ጊዜም ራስችሁን ወይም ባለቤታችሁን ለማዘገጀት የተለያዩ ነገሮችን ማድረግ ትችላላችሁ፣ ለምሳሌ ማንበብ እንዲሁም የተለያዩ  የህመም ማስታገሻ መንገዶችን ልታደርጉ ትችላላችሁ:: የህመም ማስታገሻ መንገዶችን ከባለቤታችሁ ዘንድ መወያየቱ ይጠቅማል ስለዚህም በምጥ ጊዜ ልትረዷት ትችላላችሁ እንዲሁም ለማስታገሻነት ምን እንደምትመርጥ ታውቃላችሁ::

በመጨረሻዎቹ  ሶስት የእርግዝና  ወራት  መደረግ ስለሚኖር ባቸው  ነገሮችና ከዚህ በፊት ቀደምባለላት የእርግዝና ወራት ላይተ  ጠቅሰው ከነበሩት ሊደረጉ የሚገባቸዉ ነገሮች በተጨማሪ ከዚህበታች የተገለጹትን መከተል አስፈላጊ ነው።

ጠንከር ያለና ተከታታይ  የሕመም  ምልክቶች ሲታይ ቶሎ የጤና ባለሙያ ማማከርና ተገቢውን ሕክምና በቂዕረፍት ማድረግ እንዲሁም  ስትተኚ ተጨማሪ ትራሶችን  ከእግር  ስር ወይም ከጀርባ  በማድረግ  ምቾት ሊጨምር  ይችላል።

በመጨረሻ  ወራትም  ለረዥም ሰዓት መቆም  እና  ከበድ ያሉ የጉልበት ሥራዎችን መስራት እንዲሁም ከባድ እቃዎችን መሸከም  የተከለከለ  ነዉ፡፡

ምጥ  በሚጀም ርበት  ጊዜ  ጥቂት  አመላካች  ነገሮችን  ልታዩ  ትችላላችሁ::

  • ፈሳሽ ወይም  ውሀ መፍሰስ _ ይህ  ማለት  የባለቤታችሁ የእንሽርት ውሀ መፍሰሱን እና ምጥ ሊጀምር እንደሆነ ያመላክታል:: ይህ ከተከሰተ በአፋጣኝ ባለቤታችሁን ወደ ሆስፒታል መውሰድ አለባችሁ ወዲያውኑም ለዶክተር ወይም ለሚድዋይፍ ማሳወቅ አለባችሁ::
  • መጨመታተር _ ይህ ከባድ ህመም የሚመጣ እና የሚሄድ ስሜት ሆኖ እየተጧጧፈ የሚሄድ ነው:: ባለቤታችሁ የመጨመታተር ስሜት ከተሰማት በአስቸኳይ ለሆስፒታል ደውላችሁ በመንገድ ላይ መሆናችሁን ማሳወቅ አለባችሁ:: የመጨመታተር ጊዜውንም መቁጠር አለባችሁ:: መጨመታተሩ በፍጥነት እየጨመረ ከሄደ ለአምቡላንስ መደወል ያስፈልጋል::
  • ደም መፍሰስ _ ባለቤታችሁ የደም መፍሰስ ከገጠማት በአፋጣኝ ወደ ሆስፒታል እንድትሄዱ ይመከራል::
  • የሆድ ህመም _ ባለቤታችሁ የሆድ ህመም ከገጠማትና ከምጥ ጋር እንደሚያያዝ ከተሰማት ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል መደወል ወይም መሄድ ያስፈልጋል፣ ይህም እንደ ህመሙ ጽኑነት ይወሰናል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *