22ኛዉ ሳምንት

በ22ኛዉ ሳምንት ልጅሽ የመንካት፣ የመስማት እንዲሁም የማዳመጥ ስሜቶችን ያዳብራል፡፡ በተጨማሪም ብርሃንን የመለየት ማለትም ቀንና ማታንየመለየት ክህሎቱ ያድጋል፡፡ በዚህ ሳምንት ወላጆቹ የሚናገሩትን መስማት ይጀምራል፡፡ የመስሚያ አካሎቹበዚህ ሳምንት ስለሚዳብሩ ወላጆቹ ለልጃቸዉ በጋራ ሊዘፍኑለት ይችላሉ፡፡

በሆድ ዉስጥ ያለ ልጅ አንዳንድ ጊዜ አምፒሊካልኮርድን በእጆቹ ጠበቅ አርጎ ሊይዝ ይችላል ፡፡ በዚህ ሳምንትእናትየዋከወትሮዉ የተለየ ከባሏ ጋር የመተቃቀፍ ፍላጎት ሊኖራት ይችላል፤ ፍላጎት የማይኖራቸዉ እናቶች ሊኖሩ ይኖራሉ፡፡

ልጅ የእናቱን ድምፅና የልብ ትርታ እንዲሁም በሆዷ አከባቢ የሚፈጠረዉን ድምፅ በደምብ ማዳመጥና መለየት ይችላል፡፡

የዳሌ አጥንት ሙሉ በሙሉ ባልተወሳሰበ መልኩ ቦታውን እየያዘ ይመጣል፡፡ ደም ሙሉ በሙሉ ወደ እንግዴ ልጅ ይለወጣል፡፡ ጭንቅላቱ ብቅ ማለትና ቅንድቡ እየተሰራ ይመጣል፡፡

በ22ኛዉ ሳምንት የልጅሽ የእንቅልፍ ዘይቤ፣ የእንቅስቃሴ ዘይቤ ወይም ልማድ መረዳትና ማወቅ ትቺያለሽ፡፡

በዚህ ሳምንት የልጅሽ ፆታዊ አካላት ወይም ብልቶች ቦታ ቦታቸዉን የሚይዙበት ጊዜ ነዉ፡፡ ፆታ ለመለየት አልትራሳዉንድ አሁን ብትነሺ ወጤቱ መቶ በመቶ እርግጠኛ ልትሆኚበት የምትችይ ፆታዉን መለየት ትቺያለሽ ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *