ልጅሽ እያደገ ነዉ ርዝመቱ ወደ 27ሴንቲ ሜትር ሊጠጋ ይችላል፡፡ ክብደቱ እስከ 360 ግራም ሊደርስ ይችላል፡፡ በዚህ ሳምንት የልጅሽን ስቅታ የበለጠ ማስተዋል ትጀምሪያለሽ፡፡ ከልጅልጅ ቢለያይምአንዳንዶቹ በተደጋሚ ስቅ ሊላቸዉ ይችላል፡፡
የመቅመሻ አካላቶቹስለሚያድጉ በዚህ ሳምንት የምትመገቢዉን ምግብ በትንሽ በትንሹ ማጣጣም ይጀምራል፡፡ የምትበይዉን ምግብ ልጅሽ ከአንድ ከሁለት ሰዓታት ቡኋላ እያጣጣመዉ ነዉ፡፡
ልጅሽ የአይን ቆቡን በስሱ ማርገብገብ ጀምሯል፡፡ ልጅሽ መዋጥ እየተለማመደ ነዉ የሚዉጠዉ አሚኖቲክ ፈሳሽ ሲሆን በዛም ተከትሎ የመዋጥ ክህሎቱ እያደገ ይሄዳል፡፡ አንጀቱን ማኮማተርና ማፍታታት ይጀምራል፡፡ የደም ዝዉዉሩ በዚህ ወቅት በተሟላ መልኩ ይሰራል፡፡
ልጅሽ በተወሰነ ሰዓት ዉስጥ ወይም መደበኛ በሆነ መልኩ መተኛትና መንቃት ችሏል፡፡ በዚህ ሳምንት በእርግዝና መጀመሪያ ሳምንታት የነበሩ ህመሞች ይቀንሳሉ፤ እናም ዘና ብለሽ ከእርግዝናሽ ጋር የተስማማሽበት ወቅት እንደሆነ ይገመታል ይህ ማለት የተለያዩ ጥቃቅን ህመሞች አይኖሩም ማለት አይደለም ፡፡
የልጅሽ እድገት ተከትሎ በቆዳሽ ላይ መጠነኛ የሆነ የቆዳ ሸንተረር ወይንም የቆዳ መስመር መታየት ይጀምራል፤ ይህ የእርግዝና አንዱ ሂደት ስለሆነ ከዚህ ጋር እራስሽን ማላመድ አለብሽ፡፡ ከሁለት እናቶች አንዷን የሚያጋጥም ሲሆን በጣም ጠቆር ያሉ ቆዳ ባላቸዉ ላይ ላይታይም ይችላል፡፡ እነዚህ የቆዳ ሸንተረሮች ከወሊድ ቡኋላ በአብዛኛዉ ቶሎ የመጥፋት እድል አላቸዉ፤ አሊያም ትንሽዬ ምልክት ሊተዉ ይችላሉ፡፡
በዚህ ወቅት ልጅሽ በሆድሽ ዉስጥ ሲገላበጥ በሚሰማሽ ስሜት ለመዝናናት ሞክሪ፤ ምክንያቱም ወደ ቡኋላ ላይ የበለጠ ሃይለኛና አስቸጋሪ የሆነ እንቅስቃሴ የሚያደርግበት ጊዜ ስለሚመጣ ነዉ፡፡
ከልጅሽ እድገት ጋር ተያይዞ ፈስ ወይም አየር በተወሰነ መልኩ ወይም በተደጋጋሚ ሊመጣ ይችላል፡፡በተቻለ መጠን ብዙ ዉኃና ፋይበር ያላቸዉን ምግቦች በመመገብ ሆድ ድርቀትንም ተከላከይ፡፡ ሆድ ድርቀት የመፍሳትን መጠን ሊጨምር ይችላል ፡፡
ወደ 50 ፐርሰን የሚጠጋዉ ሰዉነትሽ ባአሁኑ ሰዓት ደምና ዉሃ ነዉ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ እግርሽ እንደ ማበጥና እግሮችሽ አከባቢ ያሉ የደም ስሮች ይገታተራሉበተቻለ መጠን እግሮችሽን ወደ ላይ ከፍ ለማድረግ ሞክሪ፡፡
ሌላው ደግሞ አንዳንድ ሴቶች ከባላቸዉ ጋር የመተቃቀፍ ፍላጎታቸዉ በዚህ ሳምንት በጣም ከፍ ሊል ይችላል፡፡ ያንዳንዶቹ ደግሞ በተቃራኒዉ በጣም ዝቅ ሊል ይችላል ፡፡ ሁለቱም ጤነኛ ነዉ፡፡ በእግዝና ወቅት ወሲብ ምንም ጉዳት እንደማያደርስ ሀኪሞች ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን አንዳንድ የጤና እክሎች ካሉብሽ ሀኪምን ማማከር አስፈላጊ ነዉ፡፡