እነሆ አሁን እርግዝናሽ 4 ወር ሞላዉ፡፡ ግማሹን የእርግዝና ግዜሽን ጨርሰሻል፤ ማለትምካሁን ቡኋላ 20 ሳምንታት ብቻ ይቀሩሻል፡፡
ልጅሽ እያደገ ነዉ፤ እስከ 20ኛ ሳምንት የልጅሽን ቁመት መለካት አስቸጋሪ ነዉ፡፡ ምክያቱም እግሮቹን አጣጥፎ ስለሚቀመጥ ትክክለኛዉን ርዝመቱን ማወቅ ያዳግታል፡፡ ከዚህ ከ20 ሳምንት ቡኋላ ግን ከእግሩ ጫፍ እስከ ጭንቅላቱ ያለዉን ቁመት ማወቅ ይቻላል፡፡
የልጅሽ ቁመት ከመቀመጫዉ እስከ ራሱ ጫፍእስከ 18 ሴንቲሜትር ሊረዝም ይችላል፡፡ እንዲሁም ከእግሩ ጫፍ እስከእራሱ ጫፍ እስከ 25 ሴንቲሜትር ሊረዝም ቢችልምነገር ግን ከሰዉ ሰዉ ሊለያይ ይችላል፡፡
ልጅሽ መዋጥ ከመጀመሩ ጋር ተያይዞ ሜኮኒየም የሚባል ፈሳሽመጸዳዳት ይጀምራል፤ ማለት ሜኮኒዬም በመቀመጫዉ በኩል ይወጣል፤ ይህም ምንም ጉዳት የማያደርስ አሚኖቲክ ፈሳሽ ነው፡፡
በዚህ ሳምንት አልትራሳዉንድ ፆታን የማረጋገጥ እድሉ ከፍተኛ ነዉ፡፡ አልትራሳዉንድ ከመነሳትሽ በፊት ፆታ ማወቅና ያለማወቅ ፍላጎትሽን ለሀኪምሽ በመንገር ማወቅ ከፈለግሽ ማወቅ ትችያለሽ፡፡
ልጅሽ ማደጉን ተከትሎ ጨጓራሽ ላይ ግፊት ሊፈጥር ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ቃር እንዲሁም የሆድ ህመም ሊያጋጥምሽ ይችላል፡፡ ለዚህም የጨጓራ መድሓኒቶችን መዉስድትችያለሽ፡፡ ስትተኚ ተለቅ ያሉ ትራሶችን ብትጠቀሚ የምግብ መፈጨትን ሊያፋጥን ይችላል፡፡
ፅንሱ የዉስጥ የሰዉነት ክፍልን በጣም ከመጫኑ ጋር ተያይዞ አንዳንድ እናቶች የመተንፈስ ችግር አልፎ አልፎ ሊያጋጥማቸዉ ይችላል፡፡
አብዛኛዉ ሴቶች ከ18 እስከ 22 ባሉት ሳምንታት ዉስጥ በሆዳቸዉ ዉስጥ የልጃቸዉ እንቅስቃሴ ሊሰማቸዉ ይችላል፡፡ በተለይ ሁለተኛ ልጃቸዉንየሚወልዱ ሴቶች ከዛም በፊት የልጃቸዉን እንቅስቃሴ ይሰማቸዋል፡፡ እናም ታድያ የልጅሽን እንቅስቃሴልትሰሚ ትቺያለሽ፤ እስካሁን ካልሰማሽ ማለት ነዉ፡፡
አይረን ወይንም ብረት ንጥረ ነገሮች ያላቸዉ ምግቦችን እንድትመገቢ ይመከራል፡፡ምክንያቱም ልጅሽ ብዙ አይረን ወይም የብረት ንጥረ ነገሮችን ካንቺ ስለሚወስድ አንቺም ብዙ አይረን ያላቸዉን ምግቦች መመገብ አለብሽ፡፡ ለምሳሌ አታክልቶችን፣ እንቁላል፣ ዶሮ፣ ጉበት የመሳሰሉትን እንዲሁም ቅጠላማ የሆኑ አታክልቶች ጥሩ የብረት ንጥረ ነገር አላቸዉ፡፡ ይህን ትኩረት ልትሰጪዉ ይገባል፡፡ የብረት ንጥረ ነገር ካነሰሽ አኔሚያ ወይም በተለምዶ ደም ማነስ የሚባለዉ እንዲሁም ጊዜዉ ያልደረሰ ምጥ ሊያጋጥምሽ ይችላል፡፡ ስለዚህ የአይረን ምግቦችን መዉሰድ አለብሽ፡፡
አንዳንድ እናቶች የእርግዝና ዲያሪ ወይም መዝገብ እንዲሁም ፎቶ መነሳትና የተለያዩ ነገሮችን ያደርጋሉ፡፡አንዳንዶቹደግሞ ከወዲሁ የወሊድ ፕላን ወይም እቅድ ያወጣሉ፡፡