ሁለተኛው ሶስት ወር ከ 13 እስከ 26 ሳምንት ያለው ነው፣ ይህም የእርግዝና አስደሳጁ የእድገት ደረጃ ነው:: በዚህ በሁለተኛው ሶስት ወር ጊዜ ውስጥም አንቺም ሆንሽ ባለቤትሽ ልጃችሁን ለመጀመሪያ ጊዜ በ አልትራሳውንድ ስካን ታዩታላችሁ:: አብዛኞቹ ሆስፒታሎች የልጃችሁን የስካን ፎቶ ይሰጧችኋል:: በአንዳንድ አጋጣሚወችም የልጃችሁን ጾታ የመለየት አጋጣሚውን ልታገኙ ትችላላችሁ፣ ይህም በስካን ወቅት የሚከሰት ይሆናል::
አንዲት ነፍሰጡር ለራሷምሆነለፅንሷጤንነትሲባል የተለያዩ ጥንቃቄዎች በመጀመሪያዎቹ ወራት ስታደርጋቸዉ የነበሩ ጥንቃቄዎችን ቀጥላ ማድረግ ይኖርባታል። በተጨማሪም ማድረግ የሌለባትና ልታደርጋቸዉ የሚገቡ ነገሮችን ማወቅ አለባት፡፡ ከ4ኛ እስከ 6ኛ ወራት ልታደርጊያቸውየሚገቡ የተመጣጠነምግብመመገብ፤በየቀኑገላንመታጠብ፤በቂዕረፍትማድረግ፤በግራጎንእስከተቻለድረስ መተኛት፤ሰውነትንዘናሊያደርግየሚችልናየሚመችመቀመጫላይመቀመጥ እና የጥርስንንፅህናመጠበቅ ይኖርባታል፡፡ በተጨማሪም በነዚህ ወራት ማድረግየሌለባት ለረዥምሰዓትመቆም እንዲሁም ጠባብልብሶችን አለመልበስ እና ከባድእቃዎችንመሸከም የለባትም፡፡
ሁሉም ሴቶች የተለያዩ ናቸው ቢሆንም ግን አብዛኞቹ ሴቶች በሁለተኛው የሶስት ወር ጊዜ ውስጥ እንደ ማቅለሽለሽ ያሉ በሽታወች እንደሚቀንስላቸው ይገልጻሉ:: ይህም ማለት ባለቤትሽ በእርግዝናሽ ይበልጥ ደስተኛ ይሆናል::
አብዛኞቹ ጥንዶች ለልጃቸው የሚያስፈልጉ ነገሮችን መግዛት ያስደስታቸዋል እናም እናንተ ልጃችሁ በሆስፒታል የሚቆይበትን ቦታ ማመቻቸት ያስፈልጋችኋል፣ ምክንያቱም አብዛኛውን ጊዜ ለልጆች የሚያስፈልጉ ነገሮችን ማሟላት ጊዜ ይወስዳል::