የሆድ መነፋት ይኖራል። መለስተኛ ህመምና የሆድ ድርቀት በነፍሰጡር እናቶች ላይ የሚታዩ የተለመዱ ምልክቶች ናቸው። የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ እንዲሁም አትክልትና ፍራፍሬዎችን መመገብ የሆድን ድርቀት ሊያቀል ይችላል። በዚህ ወቅት ማህፀን መስፋትና ጥቂት የክብደት መጨመርያጋጥማል።
በዚህ ሳምንት ልጅሽ ከሶስት ሳምንት በፊት ያለዉን ክብደት በእጥፍ ጨምሯል፡፡ ቁመቱ 2.5ኢንች ነዉ ይህም ትልቅ የእጅ መዳፍ ያህል ነዉ፡፡ በእርግጥ ይሄን የሚያክል ልጅ ሁሉንም አካል አሉት ማለት የማይታመን ቢሆንም ሆድ ዉስጥ ያለዉ እዉነታ ግን እንደዚህ ነዉ፡፡
የህጻኑ የምግብ መፈጨት ሂደት ማከናወን ጀምሯል ፡፡ የሚዉጠዉ አሚኖቲክ ፍሉድ የተባለ ፈሳሽ ነዉ፡፡ አብዛኛዉ የህጻኑ የተፈጥሮ የሰዉነት ሂደት መከናወኛ ስራ ጀምሯል፡፡
ከዚህ ቀጥሎ የሚመጡት 28 ሳምንታት የልጅሽ ተክለ ሰዉነት እያደገ እና እየበለጸገ ከመሄድ ዉጪ ሁሉም ዋና ዋና አካላቶቹ ተሟልተዋል፡፡ በዚህ ሳምንት አጥንቶቹ ነጭ የደም ሴሎችን እያመረቱ እና የአጥንት ጅማቶችና ቅልጥሞችንም እያመረቱ ይገኛሉ፡፡
ፒቱታሪ ግላንድ የሚባሉ እጢዎች ጭንቅላቱ ዉስጥ ሆርሞን እንዲመነጩ እያደጉ ነዉ፡፡
በዚህ ሳምንት ምርመራ ላይየህጻኑ የልብ ምት ለመስማት ከፈለግሽ በዘመናዊ የአልትራሳዉንድ ማሽን በመጠቀም መስማት ትቺያለሽ፡፡
በ12ኛዉ ሳምንት ሰዉነትሽ ላይ የሚታዩ ለዉጦች
በመጨረሻዉ የአንደኛ ደረጃ የእርግዝና ጊዜ ዉስጥ ከፍተኛ የመፍዘዝ እና የድካም ስሜት ይሰማሻል፡፡ ማህጸንሽ በመጠኑ መለጠጥ ይጀምራል፡፡ ማህጸንሽ ከእምብርትሽ በታች ጥቂት ወደ ላይ ከፍ እያለ ይመጣል፡፡
ባለፉት ሳምንት የነበሩ የማቅለሽለሽ እና የድካም ስሜቱ ቀጥሏል፡፡ ሆድሽን ማህጸንሽ ወደ ታች ስለሚገፋዉ ቶሎ ቶሎ ሽንት ይይዝሻል፡፡
የጡትሽ መጠን እና ህመሙ እየጨመረ ይሄዳል፡፡
የልብ ማቃጠል እና የረሃብ ስሜቱ እንደቀጠለ ነዉ፡፡ የደም ፍሰቱ ወደ ልጅሽ ያጋድላል ለዚህም አንቺ በቂ የደም ፍሰት አታገኚም፡፡ የቀነሰ የደም ፍሰት ጭንቅላትሽ ላይ የጭንቀት ስሜት እና የተዘበራረቀ ስሜት ያስከትልብሻል፡፡ ከዚህ የተነሳ ቶሎ የመደሰት እና የመከፋት ስሜት እንዲሁም ሰዉነትሽ እንዲደክም ያደርጋል፡፡ የድካም ስሜቱን ለመቀነስ መጠነኛ የእግር ጉዞ ብታደርጊ የተሻለ ነዉ፡፡ ነገር ግን በባዶ ሆድ ወይም የረሃብ ስሜት እየተሰማሽ ከሆነ እንቅስቃሴ ባታደርጊ ይመተጣል ፡፡
ምክንያቱም የማዞር እና የማጥወልወል አደጋ ሊከሰትብሽ ይችላል፡፡
በዚህ ሳምንትም ሆድሽ ላያስታዉቅ ይችላል፡፡ ነገር ግን የሚጠቡሽን ልብሶች ባትጠቀሚ ይመረጣል ዳሌሽ አከባቢ ያሉ ጡንቻዎች ሲጨናነቁ መሃጸንሽ እንዲለጠጥ የሚያደርጉ ሆርሞኖች ሊስተጓጎሉ ይችላሉ፡፡
የእርግዝና ስሜቶች
እርግዝናን ተከትሎ የሚመጡ ሆርሞኖች አሉ፡፡ እነዚህ ሆርሞኖች የደም ዝዉዉር ወደ ልጁ እንዲፋጠን ያደርጋል፡፡ ይህም አንቺ ላይ የደም ዝዉዉሩ ይቀንሳል ማለት ነዉ፡፡
በዚህ ሳምንት ቶሎ ቶሎ ሽንት መሽናት የተለመደ የእርግዝና ክስተት ነዉ፡፡
እርግዝናን ተከትሎ የሚመጣ ከሰዉነት መጨመር ጋር ተያይዞ የጡት መጠን ይጨምራል፡፡ ጡትሽ ስትነኪዉ የህመም ስሜት ይኖረዋል፡፡
በዚህ ሳምንትም የማቅለሽለሽ እና የማስመለስ ችግሮች ሊቀጥሉ ይችላሉ፡፡ ብዙ እናቶች በእርግዝና ጊዜ የሚመጣ የማቅለሽለሽ እና የማስመለስ ችግር በ12ኛ እስከ 14ኛዉ ሳምንት ሊተዋቸዉ ይችላል፡፡ ከበፊቱ እየቀነሰ ቢመጣም ሙሉ በሙሉ አይቆም ይችላል፡፡
በእርግዝና ሆርሞን የተነሳ ቶሎቶሎ አፍሽ ዉስጥ ምራቅ ይሞላል፡፡ ይህንን ችግር ለመፍታት አፍሽን መቦረሽ እንዲሁም የሜንታ ከረሜላ እና ማስቲካ በመጠቀም ምራቅ እንዲበዛብሽ ማድረግ ይቻላል፡፡
በእርግዝና ጊዜ የማሽተት አቅም ስለሚጨምር ከሩቅ ቦታ የምግብ ሽታ በማሽተት ያንን ምግብ መጎምጀት አንዳንድ እናቶች ላይ የተለመደ ነዉ፡፡
በዚህ ሳምንት የንፋስ እና ቶሎ ቶሎ የመፍሳት አሁንም እንደቀጠለ ነዉ፡፡ ይህም የሚመጣዉ የምግብ ቶሎ ቶሎ አለመፈጨት እና የሆድ ድርቀት ይመጣል፡፡ ይህም የተለመደ ስለሆነ ሊያሳስብሽ አይገባም ፡፡
የድብርት ስሜት ወይም የሙድ መዋዠቅ ያጋጥምሻል፡፡ ይህ ስሜት ሰዉነትሽ በቂ ደም ስለማያመነጭ የድካም ስሜት እንዲሁም የመጫጫን ስሜት ያጋጥምሻል፡፡
በዚህ ሳምንት በቂ ምግብ እና በቂ ዉኃ መዉሰድ አለብሽ፡፡ ልጅሽ የምትመገቢዉን እንደ ሚጋራሽ አትርሺ፡፡
መጠነኛ የራስ ህመም ከደም ዝዉዉሩ ማነስ ጋር ተያይዞ ይከሰታል፡፡