7ኛዉ ሳምንት

ማርገዝሽን ለብዙ ሰዉ አንቺ ባትናገሪም ልጅሽ (ፅንስሽ – ሽል) ግን በተደጋጋሚ እየነገረሽነዉ፡፡ በቃላት ሳይሆን በእርግዝና ምልክቶችማለት ነዉ፡፡ ለምሳሌ በመነጫነጭ ፣ የስሜት መዋዠቅ ፣ በዛ ያለ ምራቅና የጡት መጠን መጨመር የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡

በሰባተኛዉ ሳምንት ልጅሽ (ፅንስሽ – ሽል)ልቡ መምታት ጀምሯል፡፡ ፅንሱ የእንግዴ ልጁን እና የእንሽርት ውሀውን አሳድጓል:: የእንግዴ ልጁም በማህጸን ግድግዳ ውስጥ ራሱን በመቅበር ከእናት የደም መስመር ኦክስጅን እና ሌሎች ንጥረ ነገሮችን ያገኛል::

በየደቂቃዉ ወደ 100 የሚጠጉ የጭንቅላት ህዋሳትን እያመረተ ነዉ፡፡ በሳምንቱ ያለው አብዛኛው እድገት በራስ ቅል ላይከሚኖረው የአዲስ ህዋሶች መፈጠር ጋር የተያያዘ ነው። በተጨማሪም እጅና እግሮች እንዲሁም መገጣጠሚያዎች እየተፈጠሩ ነዉ፡፡ ልጅሽ መጠኑ 1 ኢንች ወይንም እስከ 13 ሚሊሜትር ወይም 1.3 ሴንቲሜትር ርዝመትይኖረዋል፡፡ ፊቱ ቅርፅ መያዝእንዲሁም አፍና ምላስ መፈጠር ይጀምራሉ፡፡ የልጅሽ አንጀት፣ ትርፍ አንጀት፣ የደም አይነቱም እየተፈጠረ ነዉ፡፡ ጡንቻዎች እና አጥንቶች እንዲሁም የሰዉነት ክፍሎቹ በማደግ ላይ ናቸዉ፡፡ ጣቶቹም በአልትራሳዉንድ ሊታዩ ይችላል፡፡

በዚህ ሳምንት ዉስጥ በጣም ቀይ ወይም ቡናማ መልክ ያለዉ ደም ከፈሰሰሽ እና በፊኛ ወይም በሆድሽ አካባቢ ህመምከተሰማሽ እንዲሁም የሚፈሰዉ ደም የረጋ ወይን እንደ ስጋ መሰል ከሆነ ችግር ሊኖር ስለሚችል ሀኪም ጋር ቶሎ መታየት አለብሽ ፡፡ እነዚህ የፅንስ መጨንገፍ ወይም ዉርጃ ምልክቶች ሲሆኑ ነገር ግን የሆድ ህመሙ ወይም የደም መፍሰስ ሁልግዜ የፅንስ መቋረጥ ምልክት ላይሆን ይችላል፡፡

ባለፉት አምስት ሳምንታት ማህፀንሽ በእጥፍ አድጓል፡፡ የማለዳ ህመም እንዲሁም ከስሜት መዋዠቅ ጋር ተላምደሻል፡፡ በሰዉነትሽ ውስጥ ብዙ ፈሳሽ በመጠራቀሙ ኩላሊትሽ ከሌላዉ ጊዜ በላይ ስራ ብዙ ነዉ፡፡ ሰዉነትሽ ዉስጥ ባለዉ ደምና ፈሳሽ የተነሳ ኩላሊትሽ ብዙ ፈሳሾችን እያጣራ ወደ ፊኛሽ ይልካል፡፡ በተደጋጋሚ ቶሎ ቶሎ መሽናት ያስፈልግሻል፡፡

የድካም ስሜትና የጡዋት የህመም ስሜት በዚህ ሳምንትና በሚቀጥሉት ሳምንታት የሚያሳዩ እርጉዝ ሴቶች ሴት ልጅ ይወልዳሉ የሚል መላምት (በሳይንስ ያልተረጋገጠ መላምት) ቢኖርም ትክክለኛውን ፆታ ከ18ተኛው ሳምንት ቡኃላ በተለይም በ22ተኛዉ ሳምንት አከባቢ በሚደረግ አልትራ ሳውንድ ብቻ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

ከ4ኛዉ እስከ 7ኛዉ ሳምንት ዉስጥ ብዙ ሴቶች ማርገዛቸዉን ያረጋግጣሉ ፡፡

በዚህም ጊዜ በዚህ ሳምንት ከሀኪም ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ መያዝ አለብሽ፡፡በተጨማሪም ሀኪም ጋር ከመሄድሽ በፊትየሚሰማሽን ስሜቶች የምትጠይቂዉ ጥያቄዎች ማዘጋጀትእንዲሁም የምትወስጃቸዉን ቪታሚኖችና የአመጋገብሽን ሁኔታ በከፊሉ ለዶክተርሽ ብትነግሪዉ የተሻለ ነዉ፡፡ ጥያቄዎችሽን አዘጋጅተሽ በመሄድ ከሀኪሙ ጥሩ ምክር ታገኛለሽ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *