አልኮል

ለማርገዝ ስትሞክሪ በእርግጠኝነት መቼ እንደምታረግዢ ስለማታውቂ ባጠቃላይ አልኮል 100% ብታቆሚ ይመረጣል፡፡

በእርግዝና ጊዜ ማንኛውንም አይነት አልኮል (ቢራ፣ ወይን፣ አረቄ፣ ድብልቅ መጠጥ፣ ወይም ሌላ) መጠጣት  ጽንሱን ይጎዳዋል::

ምክንያቱም አልኮል በምትጠጡበት ጊዜ ጽንሱንም እያጠጣችሁት ስለሆነ ነው:: ብርጭቆ ሙሉ ወይን፣ ጠርሙስ ሙሉ ቢራ፣ እና ድብልቅ መጠጦች ሁሉም ተመሳሳይ የአልኮልነት ይዘት አላቸው::

አንዲት ነብሰጡር መፀነሷን ካወቀች ጀምሮ ማድረግ የሌለባት ፡-አለማጨስ እና በሚያጨሱ ሰዎች አካባቢ አለመሆን እና አልኮል አለመጠጣት ምክንያቱም  የህፃኑን የአዕምሮ እድገትና የሰውነት ክፍሎች አገልግሎት ሊያዛባ ስለሚችል አልኮል መጠጦችን መተዉ ነዉ፡፡

መድኃኒቶችን ያለ ሐኪም ትዕዛዝ አለመውሰድ ይህም   የፅንሱን ጤንነት ሊጎዳ  ስለሚችል በእርግዝና ወቅት እየተወሰዱ ያሉ ወይም ሲወሰዱ  ስለነበሩ መድሃኒቶች ከሐኪም ጋር ቀደም ብሎ መመካከር ይገባል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *