በዚህ በአራተኛ ሳምንት የወር አበባሽን እየጠበቅሺ ሊሆን ይችላል፡፡ የወር አበባ በዚህ ሳምንት አልመጣም ማለት አርግዘሽ ሊሆን ስለሚችል ነቃ ማለትና ስለ እርግዝና ምርመራ ማሰብ አለብሽ፡፡
አራተኛዉ ሳምንት ማለት የመጨረሻዉን የወር አበባ ካየሽ አንድ ወር ያህል ጊዜን ያካትታል፡፡ በዚህኛዉ አራተኛ ሳምንት የወር አበባ ይጠበቃልመቅረቱየእርግዝና ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህኛዉ ሳምንት የእርግዝና ምርመራ ማድረግ ተጨባጭ ዉጤት ሊያሳይ ይችላል፡፡ ነገር ግን እስከ ሳምንቱ መጨረሻ መቆየት ይመከራል፡፡ ብዙዎቹሴቶች በዚህኛዉ ሳምንት አሊያም በአምስተኛዉ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የሚያደርጉት የእርግዝና ምርመራ ትክክለኛዉንዉጤት ያሳያል፡፡
በዚህ ሳምንት የእርግዝና ማረጋገጫ ቴስተር ከመድኃኒት ቤትበመግዛትበግልሽ ምርመራ ማድረግ ትቺያለሽ፤ ሀኪሞች ግን ከ8 እስከ 12 ኛዉ ሳምንት ባሉት ጊዜ ዉስጥ ምርመራ በማድረግ ዘላቂነቱን ያረጋግጣሉ፡፡
ለአንዳንድ ሴቶችየወር አበባቸዉ ከቀረበት ከ2 እስከ 3 ሳምንት ዉስጥ የእርግዝና ሆርሞን በምርመራ ላይገኝ ይችላል፡፡
የጽንስ አጀማመርም ከሩዝ ዘር የቀጠነ ነው:: በፍጥነት የሚከፋፈሉት ህዋሶችም የተለያዩ የአካል ስርዐቶችን የምግብ መንሸራሸሪያ ስርዐትንም በማካተት በመገንባት ሂደት ላይ ይቀጥላሉ::
በዚህ ሳምንት መጋቤ እንግዴ ልጅ ወይም ፕላሴንታ ይፈጠርና ለፅንሱ ምግብ እንዲሁም ኦክሲጂንና የመሳሰሉት ነገሮች ይመግባል፡፡ ማወቅ ያለብሽ ባጠቃላይ በእርግዝና ወቅት የተመጣጠነ ምግብ መመገብ አስፈላጊ ነዉ፡፡ የተመጣጠነ ምግብ ለፅንሱ ጤንነትና እድገት በጣም አስፈላጊ ነዉ፡፡