በዚህ በሶስተኛዉ ሳምንት የወር አበባሽ መቅረቱን እንኳን እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡ ሶስተኛዉ ሳምንት ማለት የመጨረሻዉን የወር አበባ ካየሽበት ከመጀመሪያዉቀን አንስቶ ከሁለት ሳምንት ቡሃላ ማለት ነዉ፡፡
ለማንኛውም እንቁላልና የወንድ ዘር ከተገናኙ እንኳን ደስ ያለሽ!እርግዝና ወይም ፅንሰት ተጀምሯል ማለት ነዉ፡፡ እንደየሰዉ ቢለያይም አንዳንድ ሴቶች የእርግዝና ምልክት ከሚባሉትን አንዳንዱን ምልክቶች ሊያዩ ይቻላሉ፡፡ ለምሳሌ የጡት ጫፍ መጠንከር፣ በተደጋጋሚ ቶሎ ቶሎ ሽንት መሽናት፣ ጠንካራ የሆነ የማሽተት ችሎታ መጨመር አልፎ አልፎም ማቅለሽለሽና ማስታወክ ሊያጋጥማቸዉ ይችላል፡፡ አንዳንዶቹ ላይ ደግሞ ምንም የተለየለዉጥ ላታይ ይችላል፡፡
የሽንት ምርመራ ወይም የደም ምርመራ በማድረግ በዚህ ሳምንት እርግዝናሽን ለማረጋገጥ መሞከር ትቺያለሽ፤ እንደየሰዉ ቢለያይም ትክክለኛየምርመራ ዉጤት ላይገኝ እንዲሁም ሊዘገይ ይችላል፡፡
ከፅንሰት ሰላሳ ሰዐት በኋላ፣ ህዋሱ ለሁለት ይከፈላል:: ከሶስት ቀን በኋላ፣ የዳበረው ህዋስ ለ 16 ህዋስ ይከፋፈላል:: ከተጨማሪ ሁለት ቀናት በኋላ፣ የዳበረው ህዋስ ከፋሎፒያን ቱቦወደ ማህጸን ይፈልሳል:: ከጽንሰት ሰባት ቀናት በኋላ፣ የዳበረው ህዋስ በወፍራሙ የማህጸን ውስጠኛው ሽፋን(ኢንዶሜትሪዩም) ራሱን ይደብቃል:: ይህ የዳበረው ህዋስም በዚህ ደረጃ ላይ ቅሪት ተብሎ ይታወቃል፡፡