ሁለተኛ ሳምንት ላይ እርግዝና ገና አልተፈጠረም፤በዚህሳምንት መጀመሪያ ላይ ወይም ዘግይታ እንቁላል ትወጣለች፡፡ ከዛም በወንዴዉ ዘር ጋር ስትገናኝ ፅንስ ይፈጠራል ማለት ነዉ፡፡
መገንዘብ ያለብን ነገር ብዙዎቹ ህፃናት የሚወለዱት እንቁላልና የወንዴዉ ዘር ከተገናኙ ከ38 ሳምንት ቡኃላ ነዉ፡፡ ነገር ግን እንቁላሉና የወንዴዉ ዘር የተገናኙበትን ቀን በእርግጠኝነት መናገር በሳይንስም በተፈጥሮም ማወቅ ስለማይቻል የእርግዝና ወራት 40 ሳምንት ተደርጎ ይታሰባል፡፡ ማለትም የእርግዝና ወቅት መቆጠር የሚጀምረዉ የመጨረሻዋን የወር አበባ ካየሽበት ቀን ጀምሮ ነዉ ማለት ነዉ፡፡
በዚህ ሁለተኛ ሳምንት ዉስጥ እንቁላልናየወንድ ዘር የሚገናኙበትሳምንት ነዉ፤ በዚህ ሳምንት ፅንሰት ወይም እርግዝና ይጀምራል፡፡ እንደየ ሴቱ የወር አበባ ርዝመትና ጊዜ የሚወሰን ቢሆንም በዚህ ሳምንት ወይም መጨረሻ አከባቢ እንቁላል ወጥታ ከሆነ ከ12 እስከ 24 ሰዓት ባሉት ጊዚያት ዉስጥከወንድ ዘር ጋር ስትገናኝእርግዝና ይጀመራል ማለት ነዉ፡፡
ፅንሰት ሲከሰት የሚወለደዉ ህፃን ፆታ እንዲሁም በዘር የሚተላለፉ ነገሮች ለምሳሌ የአይን ቀለም ፣የፀጉር ቀለም ፣ ቆዳ እንዲሁም የሰዉነት ቅርፅ በፅንሰት ጊዜ ይፈጠራል፡፡ የወንዱ ክሮሞዞም 23 ሲሆኑ የሴቷም 23 ነዉ ፡፡