የመጀመሪያው የእርግዝና ቀን ማለት የመጨረሻው የወር አበባ (ፍሰት የጀመረበት) የታየበት የመጀመሪያው ቀን ማለት ነው፡፡ የመጀመሪያው የእርግዝና ሳምንት ማለት የመጨረሻዋ የወር አበባ ከታየበት ጊዜ (ቀን) ጀምሮ ይቆጠራል:: የመውለጃ ጊዜሽ የሚሰላው የመጨረሻዋን የወር አበባ ካየሽበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ነው፣ ይህ የመጀመሪያው የእርግዝና ሳምንት የ 40 ሳምንት የቆጠራ ጊዜሽ አካል ነው፡፡
ፅንሰት የሚከሰትበትንቀን በእርግጠኝነት ማወቅ አይቻልም፡፡ ስለዚህም ዶክተሮችየእርግዝናን ጊዜ መቁጠር የሚጀምሩት የመጨረሻው የወር አበባ ከታየበትቀን ጀምሮ ወደ ፊት ያሉትን ቀናቶች የእርግዝና ቀን ብለውመቁጠር ይጀምራሉ ፡፡