መካንነት የሴት ችግር ብቻ ተደርጎ መታየት የለበትም፡፡ የወንዶች የመካንነት ችግር ብዙ ምክኒያቶች ሲኖሩት በዋናነት የሚጠቀሱት በወንድ ዘር ፍሬ ማምረቻ ላይ የሚፈጠር ችግር ፣ የስፐርም መጉዋጉዋዣው መዘጋት፣ የወንድ ዘር ወይም ስፐርም ብዛትና ጥራት ማነስ ነው፡፡ በአንድ የግብረ ስጋ ግንኙነት የሚመነጨው የወንድ ዘር ወይም ስፐርም ብዛት አነስተኛ ከሆነ፣ ወይም ጥራቱ ዝቅተኛ ከሆነ ማስረገዝ ላይችል ይችላል፡፡ በአንድ የወሲብ ግንኙነት ከ 20 ሚሊዮን እስከ 300 ሚሊዮን የወንድ ዘር ወይም ስፐርም የሚወጣ ሲሆን፤ ከ20 ወንዶች ውስጥ አንዱ ከወንድ ዘር ወይም ስፐርም ብዛት ጋር የተያያዘ ችግር እንዳለው ይገመታል፡፡
ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ በጥንዶች መካከል ለመካንነት የወንዶች ተሰትፎ ወደ 20% ይጠጋል፡፡ በሴትዋም በወንዱም በኩል ልጅ ያለማግኘት ችግር ሲከሰት ለምክንያትነቱ ከ20-40% ያህል ወንዶች ይጠቀሳሉ። የወንዶች የመካንነት ችግር መፍትሄው የህክምና ምርመራ ማድረግ ነው፡፡
ከአመት ሙከራ በኋላ ማርገዝ ያልቻሉ ጥንዶች፣ ወይም ከ35 አመት በላይ ለሆነች ሴት ደግሞ ከ 6 ወር በኋላ ቅሪት ካልያዘች ለበለጠ እርዳታ ወደ ዶክተር መሄድ ይመከራል:: ዶክተሮች መውለድ ያልቻሉ ጥንዶችን መውለድ እንዲችሉ ሊረዱ ችለዋል::