የሴቶች መካንነት

ፍሬያማነትን  ብዙ ነገሮች  ሊጎዱት  ይችላሉ:: ከእነዚህም ውስጥ ውጥረት፣  ማጨስ፣  የአባላዘር  በሽታዎች፣  እንዲሁም ሌሎች  የጤና  ችግሮች በዋናነት ይጠቀሳሉ::  ደግሞም፣ ሴት እድሜዋ ሲጨምር፣  ቅሪት የመያዝ እድሏ እየጠበበ ይመጣል::

ነፍሰ  ጡር  እንዳይሆኑ  ሊያግዱ  የሚችሉ  የተለያዩ  ምክንያቶች  አሉ::  አንደኛው ምክንያት ሊሆን የሚችለው በየወሩ ፍሬያማነት  (እንቁላል)  ላይከሰት ይችላል:: በቅርቡ  የሆርሞናል የወሊድ  መቆጣጠሪያ  ተጠቃሚ  ከነበሩ፣ ፍሬያማነት ሊዘገይ  ወይም  ደግሞ ስርዐትን  ያልተከተለ ሊሆን ይችላል:: የመርፌ  የወሊድ  መቆጣጠሪያ ተጠቃሚ ከሆኑ፣ እስከ አመት ድረስ ፍሬያማነት ሊዘገይ ወይም ደግሞ ስርዓትን ያልተከተለ ሊሆን ይችላል::

ከሚደረጉት  ህክምናዎች  ውስጥም፣ የኑሮ  ዘዴን ላይፍ ስታይልን መለወጥ፣ ውጥረትን መቀነስ፣ ሴቶች እንቁላል እንዲያፈሩ የሚያደርጉ መድሀኒቶች መስጠት፣  የመራቢያ አካላት ላይ በሚደረግ የቀዶ ጥገና፣ በመራቢያ  ቴክኖሎጂዎች እርዳታ ለምሳሌ  እንደ ቪትሮ ፈርትላይዜሽን  ወዘተ ይጠቀሳሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *