እርጉዝ መሆንን ለማወቅ የሚረዱን ምልክቶች የወር አበባ ጊዜውን ጠብቆ መምጣቱን ካቆመና ጡት ከወትሮው መጠኑን ከጨመረና ከጠነከረ፣ጡት መወጠርና በጡት ጫፍ ላይ ከመጠን በላይ የሆነ የመጥቆር ሁኔታ ጫፉም ከጠቆረ እንዲሁም የምግብፍላጎት መቀያየር፣ ቶሎቶሎ ሽንት መምጣት፣ ተለመደ የድካም ስሜት መጀመር፤ የማስመለስና የማቅለሽለሽ ስሜት መጀመር የማሽተት አቅም ከወትሮው መጨመረ እና የሰውነ ትሙቀት መጨመር ሊከሰት ይችላል፡፡
ልብይበሉ!
እነዚህነፍሰጡርመሆንየሚጠቁሙምልክቶችናቸው።ቢሆንምግንእርግጠኛመሆንየሚቻለዉወደጤናተቋምሂደዉ በህክምናበማረጋገጥ ይገባል፡፡
ለማርገዝ ስትሞክሪ መከተል ያለብሽ አመጋገብ
ብዙ ሴቶች ስለአመጋገብ ስረዓታቸው መጨነቅ የሚጀምሩት ካረገዙ በኃላ ነው ነገር ግን ጤናማ አመጋገብ ከእርግዝና በፊት እንደሚያሰፈልግ አየጨመረ የመጣ ማስረጃ አለ፡፡ ለማርገዝ እየሞከርሽ ከሆነ፣ ካረገዝሽ በኃላ ጤናማ እርግዝና እንዲኖርሽ ጥሩ የአመጋገበ ልማድ ሊኖርሽ ይገባል፡፡ አንዳንድ ልማዶች በቀላሉ ለመተው ከባድ ናቸው፣ ካረገዝሽ በኃላ ከመቸገር አሁኑኑ ለመተው መሞከር አለብሽ፡፡
ምን መመገብ አለብሽ?
እናት ለመሆን እያሰብሽ ከሆነ ከታች የተዘረዘሩትን ምግቦች መመገብ ሰውነትሽ በደንብ ስራወን እንዲሰራ ያደርገዋል፡፡ ለመፀነስ ምቹ ሁኔታ ያመቻቻል እንዲሁም ለፅንሱ ዕድገት በአልሚ ንጥረ ነገሮች የበለፀገ መሰረት ይጥላል፡፡
ምግብ | ጥቅም |
ጥራጥሬ | ቪታሚነ ቢ፣ ኢ ና አሰር(ፋይበር) |
አትክልትና ፍራፍሬ | ቪታሚን ሲ፣ ፀረ ወክሳጅ(antioxidants) |
ብሩንዶ፣ ባቄላ | ፕሮቲን፣ ዚንክ፣ አይረን |
ቅባቱ የወጣ የወተት ተዋፆ | ፕሮቲን |
አሜጋ 3(አሳ) | የፅንሱ አእምሮና የነርቭ ስርአት እንዲያድግ ያደርጋል፣ ያለጊዜ የመወለድን አደጋ ይቀንሳል |
በኪኒን መልክ የተዘጋጁ ቪታሚኖችን ከ ፎሊክ አሲድ ጋር | የህብለ ሰረሰርና የአምሮ ጉድለቶችን ይቀንሳል፣ በተለይ ከእርግዝና በፊት ያሉ ጥቂት ሳምንታትና የመጀመሪያዎቹ ሦስት የእርግዝና ወራት |
ፍራፍሬና አትክልት
ፍራፍሬዎችና አትክልቶች የብዙ አይነት ቪታሚኖችና ማዕድናት ምንጭ ናቸው እነዚህን ንጥረ ነገሮች ማግኘት በተለይ ከማርገዝሽ በፊት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ለምሳሌ እንደ ስፒናች፣ ሰላጣ፣ አበባ ጎመን ያሉ አትክልቶች በ ፎሌት ቪታሚን ቢ የበለፀጉ ናቸው፡፡ ከማርገዝ በፊትና እርግዝና ከተፈጠረ በኃላ በፎሌት የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ በፅንሱ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ የነርቭ ቱቦ በአግባቡ ሳይዘጋ በመቅረቱ ምክንያት የሚመጡ ስፒና ቢፊዳ የመሳሰሉ የነርቭ እክሎችን ለመከላከል ይቻላል፡፡
በቪታሚን ሲ የበለፀጉ የብርቱካን ዘሮች፣ እንጆሪ፣ አበባ ጎመን እና ቲማቲም አይረንን ሰውነተሽ ከአንጀትሽ ማጣራትና መውሰድ እንዲችል ይረዳዋል፣ አይረን ላረገዙ ሴቶች በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
ባጠቃላይ ከፍተኛ መጠን ያለው ጥቅም ለማግኘት የተለያየ ቀለም ያላቸውን ፍራፍሬና አትክልት ተመገቢ፡፡
ጥራ ጥሬ
ለማርገዝ የምትፈልግ ሴት በተለያዩ ንጥረ ነገሮች የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ አለባት፣ ጥራጥሬዎች ጥሩ መጀመሪያዎች ናቸው፡፡ እንደ አጃ፣ ቡኒ ሩዝ፣ ስንዴ የመሳሰሉት አህሎች በቀን ከምትመገቢው ምግብ ግማሹን ቦታ ቢይዙ ተመራጭ ነው፡፡ የተጣሩ(የተፈተጉ) ካርቦሃይደሬቶች(ፓስታ፣ የፉርኖ ዱቄት ዳቦና ነጭ ሩዝ) በቀጥታ የማርገዝ እድልሽን አይቀንሱትም ነገር ግን የማጣራት ሂደቱ እህሉን እንደ አሰር፣ ቪታሚን ቢና አይረን ያሉ ቁልፍ ነጥረ ነገሮቹን ያሳጣዋል፡፡
ዓሳ
እንደ አንዳንድ ሳይንቲስቶች ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ ለማርገዝ አዎንታዊ ተፅኖ አለው፡፡ የዚህ አስፈላጊ ፋት ዋነኛ ምንጭ ዓሳ ነው፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በኦሜጋ 3 የበለፀገ የአመጋገብ ስርዓት ውፃትን ይቆጣጠራል፣ የእንቁላሉን ጥራት ያሻሽላል እንደውም እንቁሊጢ(እንቁላል የሚያመርተው አካል) ቶሎ እንዳያረጅ ያደርገዋል፡፡ በተጨማሪም ለልጁ አእምሮና አይን እድገት አስፈላጊ ነው ሌሎች ከእርግዝና ጋር የተያያዙ ጥቅሞች አሉት፡፡ ሙሉ የእርግዝና ጊዜውን ሳይጨርስ መውለድ አደጋን ይከላከላል፣ በእርግዝና የሚመጣ ደመ ግፊት መያዝን ይቀንሳል፣ ድብርትንም ቀለል ያደርጋል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ የዓሳ ዘሮች በውስጣቸው ሜርኩሪ የሚባለውን ማዕድን ስለያዙ የፅንሱ ነርቭ ስርዓት ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡
ልትመጥኛቸው ወይንም ልታቆሚያቸው የሚገቡ ምግቦች
ካፊን
በእርግጠኝነት ካፊን መፀነስ መቻል ላይ የሚያመጣው ችግር አይተወቅም ስለዚህ በተቻለ መጠን የምትወስጂውን የካፊን መጠን መቀነስ አለብሽ፡፡ ከ 500 ሚ.ግ በላይ ካፊን በቀን መውሰድ መፀነስ እንዳትችዪ ሊያደርግሽ እንደሚችል አንዳንድ ግኝቶች ያሳያሉ፡፡ባለሙያዎች በቀን ከ 300 ሚ.ግ በታች ካፊን መውሰድ የማርገዝ ዕድልሽ ላይ ተፅኖ እንደማይኖረው ይስማማሉ፡፡ ነገር ግን ለመፀነስ እየተቸገርሽ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ ብታቆሚው ይመከራል፡፡ ካረገዝሽ በኃላ የምትወስጂው የካፊን መጠን በቀን ከ 200 ሚ.ግ መብለጥ የለበትም ምክንያቱም ውርጃ ሊያስከትል ይችላል፡፡
አልኮል
አልፎ አልፎ ቢራ ወይንም አንድ ብርጭቆ ወይን ብትጠቺ የማርገዝ እድልሽን ላይቀንሰው ይችላል ነገር ግን በቀን 2 ወይም ከዛ በላይ መጠጣት የማርገዝ ዕድልሽን ይቀንሳል፡ በመጠኑ መጠጣት እንኳን ለውርጃ የመጋለጥ እድልሽን ይጨምረዋል፡፡ በእርግጠኝነት መቼ እንደምታረግዢ ስለማታውቂ ባጠቃላይ አልኮል ብታቆሚ ይመረጣል ምክንያቱም አልኮል ፅንሱን ይጎዳዋል፡፡
ሊስቴርያ
ሊስቴሪያ ስጋ፣ ለስላሳ አይብ(ቺዝ)፣ ፓስቸራይዝድ ያልሆኑ የወተት ተዋፆዎች ውስጥ ሊገኝ የሚችል ባክቴሪያ ነው፡፡ እርጉዝ ሴቶች ከሌላው ሰው ይልቅ በዚህ ባክቴሪያ የመጠቃት ዕድላቸው ይጨምራል፡፡ ይህ ባክቴሪያ በመጀመሪያው የእርግዝና ሦስት ወር ውስጥ ምንአልባትም ገና ማርገዝሽን እንኳን ሳታውቂ እንዲያስወርደሽ ያደርጋል፡፡ ሊስቴሪያን ለመግደል ሊያጋልጡሽ የሚችሉ ምግቦችን ከመመገብሽ በፊት በደንብ አሙቂያቸው፣ የተረፈ ምግብ የሙቀት መጠኑ 40 ዲግሪ ወይም ከዛ በታች በሆነ ፍሪጅ ውስጥ ይቀመጥ፡፡ ከፍሪጅ ውጪ ከሁለት ሰዓት በላይ የተቀመጠ ምግብ እንዳትመገቢ፡፡
ቪታሚን እና ማዕድናት
ከተመጣጠነ አመጋገብ ሁሉንም የሚያስፈልጉሽን ንጥረ ነገሮች ማግኘት ብትችይም ለልጅሽ ጤንነት ስትይ ከማርገዝሽ በፊት አንዳንድ ተጨማሪ ቪታሚኖችን መውሰድ አለብሽ፡፡
አይረን
ከማርገዝሽ በፊት የሰውነትሽን አይረን ክምችት መጨመር አለብሽ፣ በተለይ ደግሞ የወር አበባሽ ከባድ ከሆነ፡ ምክንያቱም በየወሩ የአይረን መጠንሽ እየቀነሰ ነው ማለት ነው፡፡ ስታረግዢ አያደገ ያለው ፅንስ ካከማቸሽው አይረን ስለሚወስድ ሰውነትሽ የሚያስፈልገውን መጠን ሊያገኝ አይችልም፡፡ የአይረን ማነስ ስትፀንሺ ልጅሽን ከመጉዳቱ በላይ አንቺንም ለእርግዝና ጊዜና ከወለድሽ በኃላ የአይረን ማጠር ደም ማነስ ያጋልጥሻል፡፡ ደም ማነስ ቀይ የደም ሴልሽ ከትክክለኛው መጠን እንዲያንስ ያደርገዋል ይህም ያለሽን ኃይል ይመጠዋል፡፡ ስጋ ማትመገቢ ከሆነ በኪኒን መልክ የተዘጋጀ አይረን እንድትወስጂ ሊደረግ ይችላል፡፡
ፎሊክ አሲድ
ፎሊክ አሲድ የቪታሚን ቢ አይነት ሲሆን በፅንሱ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ የነርቭ ቱቦ በአግባቡ ሳይዘጋ በመቅረቱ ምክንያት የሚመጡ ስፒና ቢፊዳ የመሳሰሉ የነርቭ እክሎች የመጠቃት እድልን ይቀንሳል፡፡ ለማርገዝ እያሰብሽ ከሆነ በቀን 400 ማይክሮግራም እስከ እርግዝናሽ 12ተኛ ሳምንትድረስ በኪኒን መልክ የተዘጋጀ ፎሊክ አሲደ ውሰጂ፡፡ ከኪኒኑ በተጨማሪ ጥቁር አረንጓዴ ቅጠል ያላቸውን አትክልቶች፣ ቡኒ ሩዝ፣ ለውዝ፣ ጥራጥሬ የመሳሰሉ ፎሊክ አሲድ ያላቸውን ምግቦች መመገብ አለብሽ፡፡ ከዚህ በፊት ስፒና ቢፊዳ ያለው ልጅ ወልደሽ ከሆነ፣ አንጀትሽ አንዳንድ ምግቦች የመቻል ችግር ካለብሽ፣ ስኳር ካለብሽ ወይም የሚጥል በሽታ መድሃኒት የምትወስጂ ከሆነ ሐኪምሽን አማክሪ ከፍ ያለ መጠን ያለው ፎሊክ አሲድ ሊያስፈልግሽ ይችላል፡፡
ፕሮቲን
የጤናማ አመጋገብ ዋነኛ ክፍል ነው፡፡ በአሜሪካ ሃርቨርድ የሕክምና ትምህረት ቤት በተደረገ ጥናት ከስጋ ፕሮቲን ከሚያገኙ ሴቶች ይልቅ ከለውዝ፣ ባቄላ፣ አተር፣ አኩሪ አተር ከመሳሰሉት አህሎች ፕሮቲን ያገኙ ሴቶች በውፀት ምክንያት ለሚመጣ መካንነት ችግር የመጋለጥ ዕድላቸው ይቀንሳል፡፡ ስለዚህ የፕሮቲን ምንጭሽን ቀይሪ፡፡
ተጨማሪ መረጃዎች
ክብደትሽን ተቆጣጠሪ
ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ ብዙም ይሁን ትንሽ ለመፀነስ ያለመቻል ላይ አስተዋፆ እንዳለው ይተወቃል፡፡ ክብደት በጣም ሲበዛ ወይንም በጣም ሲያንስ የመራቢያ ዑደትሽን ያዛባዋል፡፡ ስለዚህ ጤናማ ክብደት ሊኖርሽ ይገባል፡ ይህም የሰውነትሽ ክበድት ከቁመትሽ አንፃር ቦዲ ማስ ኢንዴክስ(body mass index) በመለካት ይተወቃል፣ ማለትም ክብደትሽን(ኪ.ግ) ለ በሁለት በተባዛ ቁመትሽ(ሜ) ማካፈል፡፡ ትትክለኛው መጠን ከ 19-24 ነው፡ ከዚህ መጠን ከበለጠ ወይንም ካነሰ ሐኪምሽን አማክሪ፡፡
ኮሊን
ከዚህ በፊት ሰምተሽው ላታቂ ትችያለሽ ነገረ ግን ይህ ንጥረ ነገር በአደገኛ ዘረመል አማካኝነት ፅንሱ ላይ ሊመጡ የሚችሉ ጉድለቶችን ሊቀንስ የሚችል ሃይል አለው፡፡ ብዙ ሴቶች በቂ ኮሊን አያገኙም፡፡ የእንቁላል ቢጫው ክፈል ጥሩ ምነጭ ነው፡፡
የሱ አመጋገብ
ለመፀነስ ስታስቢ ያንቺ ጤናማ አመጋገብ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ሁሉ የሱም አመጋገብ ወሳኝ ነው፡፡ ያለማርገዝ ችግር በወንዱ ክብደት ወይንም አመጋገብ የመጣ ሊሆን ይችላል፡፡ አባት ለመሆን የሚሹ ሁሉ ቪታሚን ሲ እና ኢ፣ ዚንክ፣ ፎሊክ አሲድ ጤናማ የወንዴ ዘር(ስፐርም) እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡ እነዚህን ንጥረ ነገሮች መፀነስ ካሰባችሁበት ጊዜ 3 ወር ቀደም ብሎ መውሰድ መጀመር አለበት ምክንያቱም የወንዴ ዘር ሙሉ ለሙሉ ለማደግ 74 ቀን አካባቢ ይወስድበታል፡፡
ውሃ
ውሃ በደንብ ጠጪ፣ በቂ ውሃ ካልጠጣሽ የማህፀን ፈሳሽሽ የወንዴው ዘር እንደፈለገው እንዳይንቀሳቀስና ወደ እንቁላሉ በቀላሉ መድረስ እንዳይችል ያደርገዋል፡፡ ወንዱም ቢሆን የሚረጨው ፈሳሽ ጤናማ እንዲሆን እና ወደ እንቁላሉ ወንዴ ዘሩን ማድረስ እንዲችል ውሃ መጠጣት አለበት፡፡
እርግጥ ነው አመጋገባቸው መጥፎ ሆኖ ምንም የማርገዝ ችግር የሌለባቸው ብዙ ሴቶች አሉ በተመሳሳይ ሁኔታ ጥሩ ምግበ እየበሉ ማርገዝ ያልቻሉ ብዙ ሴቶች አሉ፡፡ ነገር ግን ለማርገዝ ስትሞክሪ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ የማርገዝ ዕድልሽን ይጨምረዋል ከዛም በላይ ስታረግዢ ሰውነትሽ ጤናማ እንዲሆን ይረዳዋል፡፡ መፀነስ ያልቻልሽው በሌሎች ምክንያቶችም ሊሆን ስለሚችል ሐኪም አማክሪ፡፡
የእርግዝና መከላከያ
የወንድ ኮንዶም
- በመመርያዎቹ መሰረት ሚጠቀሙት ከሆነ 98 በመቶ ውጤታማ ነው፡፡
- ከላስቲክ እና ፕላስቲክ የሚሰሩት፣ እርግዝናን እና በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን የሚከላከሉ ኮንዶሞች በወንድ ልጆች ብልቶች ላይ የሚጠለቁ ሲሆኑ ለተጨማሪ መከላከያነት ከሌሎች የወሊድ መቆጣጠርያ ዘዴዎች ጋር ሊጠቀሟቸው የሚችሏቸው ናቸው፡፡ ኮንዶሞች ውጤታማ እና በትንሽ ወጪ በቀላሉ የሚገኙ እና አንዳንድ ጊዜ በነፃ የሚገኙ ናቸው፡፡
- ሁለቱም ሴቶች እና ወንዶች የኮንዶምን ከአጋሮቻቸው ጋር ለመጠቀም እንዴት እንደሚወያዩ ከተረዱት ውጤማነቱ ሊጨምር ይችላል፡፡
- የመጠቀሚያ ማለቂያ ጊዜን የኮንዶም ማሸጊያ ላይ ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም ላስቲክ በጊዜ ብዛት ሊበላሽ ስለሚችል እና ኮንዶሞች የመጠቀሚያ ማለቂያ ጊዜ በኋላ ከተጠቀሙባቸው ሊቀደድ ይችላል፡፡
የሴት ኮንዶም
- የሴት ኮንዶም በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት እርግዝናን ለመከላከል እና በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን አደጋ ለመቀነስ የሚጠቅም ኪስ ነው፡፡ በእያንዳንዱ ጥግ ላይ ተጣጣፊ ቀለበቶች አሉት፡፡
- ልክ ከሴት ልጅ ብልት ግንኙነት በፊት በሴት ልጅ ብልት ውስጥ ይገባል፡፡ በተዘጋው ጥግ ላይ ያለው ቀለበት በሴት ልጅ ብልት ውስጥ ኪሱን ይይዛል፡፡ በተከፈተው ጥግ ላይ ያለው ቀለበት በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ከሴት ልጅ ብልት ቀዳዳ ውጭ ይቀመጣል፡፡
- ቀጣይነት ባለው እና ትክክለኛ አጠቃቀም፣ የሴት ኮንዶሞች የ5 በመቶ ውድቀት አላቸው፡፡
- የሴት ኮንዶም ከግንኙነት በፊት እስከ 8 ሰዓታት ሊገባ ይችላል፡፡ከግንኙነት በኋላ ወዲያው በማውጣት ይጣላል፡፡
- የሴት ኮንዶሞች እና የወንድ ኮንዶሞች በተመሳሳይ ጊዜ መጠቀም አይገባም፤ ምክንያቱም እርስ በእርስ ሊጣበቁ ስለሚችሉ እና መንሸራተት ሊፈጥሩ ወይም አንዱ ወይም ሁለቱም መሳርያዎች ሊቀደዱ ይችላሉ፡፡
መታቀብ
መታቀብ ማለት የግብረ ስጋ ግን ኙነት አለማድረግ ነው፡፡ ከግብረ ስጋ ግንኙነት ከታቀቡ አያረግዙም፡፡ በህይወትዎ ውስጥ የሆነ ጊዜ የግበረስ ግንኙነት ላለማድረግ ሊወስኑ ይችላሉ፡፡ መታቀብን በየቀኑ ምርጫዎ የሚያደርጉት ነው፡፡ መታቀብን የመረጡት ለምን እንደሆነ ለራስዎ ማስታወስ ይኖርብዎታል፣ ስለሚመጡት አደጋዎች ያስቡ፣ ለግብረ ስጋ ግንኙነት የሚያነሳሱ ሁኔታዎች በሚኖሩበት ወቅት ውሳኔዎን በድጋሚ አይገምግሙ- በንፁህ አይምሮ ማሰብ እስከሚችሉ ድረስ በውሳኔዎ ይፅኑ፡፡
ሰዎች እርግዝናን ለመከላከል፣ በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል፣ ለግብረ ስጋ ግንኙነት ዝግጁ እስከሚሆኑ ድረስ ለመጠበቅ፣ ትክክለኛ አጋራቸውን እስከሚያገኙ ድረስ ለመጠበቅ፣ ግብረ ስጋ ግንኙነት ሳይፈፅሙ ከፍቅር አጋራቸው ጋር ለመደሰት፣ ትምህርት፣ ስራ ወይም ተጨማሪ ስራዎች ላይ ለማተኮር፣ ግላዊነትን፣ ስነምግባር ወይም ሀይማኖታዊ አመለካከትን እና እሴትን ለመጠበቅ፣ መለያየትን ለማቆም፣ ከአጋር ሞት ለመፈወስ፣ በበሽታ ወይም በወረርሽኝ ወቅት የህክምና ትዕዛዝን ለመከታተል መታቀብን ይመርጣሉ፡፡
ማንኛውም ሴት ወይም ወንድ ከግብረስጋ ግንኙነት ጨዋታ ሊታቀብ ይችላል፡፡ ብዙ ሰዎች በህይወታቸው ውስጥ በተለያዩ ጊዜያቶች ይታቀባሉ፡፡ አንዳንዶች ከግብረስጋ ግንኙነት ጨዋታ በህይወታቸው ውስጥ ለረጅም ጊዜያቶች መታቀብን ሊመርጡ ይችላሉ፡፡
ጠቀሜታዎች፡ በመታቀብ ምንም አይነት የጤና ችግሮች የማይኖሩ ሲሆን ነፃ ነው፡፡ ብልትዎ ከአጋርዎ ብልት ጋር ካልተነካካ በስተቀር የማያረግዙ ሲሆን በግብረ ስጋ ግንኙነት በሚተላለፉ በሽታዎች አይያዙም፡፡
ጉዳቶች፡ ሀሳብዎን ከቀየሩ እና የግብረ ስጋ ግንኙነት ለማድረግ ከወሰኑ፣ መታቀብ ምንም አይነት መከላከያ አይሰጥም፡፡ ሌላ የወሊድ መቆጣጠርያ ዘዴ በቅርበት ሊኖርዎት ይገባል፡፡ ያስታውሱ፤ የግብረ ስጋ ግንኙነት ባያደርጉም በግብረ ስጋ ግንኙነት በሚተላለፉ በሽታዎች ሊያዙ ይችላሉ፡፡ በአፍ የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ ወይም የእርስ በእርስ የቆዳ ንክኪ፣ ለምሳሌ የእያንዳንዳቸውን ብልት በማሻሸት እና በመደባበስ ሊያዙ ይችላሉ፡፡
ለማርገዝ ካቀዱ፡ በቀላሉ መታቀብን ማቆም ነው፡፡ ወዲያው ለማርገዝ መሞከር ይችላሉ፡፡
አይዩዲ (በማህፀን ውስጥ የሚቀበር መሳርያ)
አይዩዲ ትንሽ የላስቲክ መሳርያ ሲሆን (እንደ አይነቱ እና ፍላጎትዎ መሰረት) ለወራት ወይም ለአመታት ወደሚቀመጥበት ማህፀን በጤና ጥበቃ ሰጪዎ የሚጨመር ነው፡፡ ውጤታማነቱ 99% ወይም ከዛ በላይ ነው፡፡
አይዩዲ ስፐርም እንቁላልን እንዳያገኝ የሚከለክል እና ከስፐርም ጋር የተገናኙ እንቁላሎች በማህፀን ውስጥ እንዳያድግ የሚከለክል መዳብ ወይም ሆርሞኖችን የያዘ ነው፡፡
ጠቀሜታ፡ አንድ ጊዜ አይዩዲ ከተቀመጠ በየቀኑ የወሊድ መቆጣጠርያን ማስታወስ አያስፈልግም፡፡ የአይዩዲ መዳብ ቀጣይነት ላለው 10 ዓመታት የእርግዝና መከላከያን ይሰጣል፡፡ አይዩዲ ከሆርሞኖች ጋር የወር አበባ ህመሞችን ሊቀንስ የሚችል እና የወር አበባ ፍሰትን በከፍተኛ ሁኔታ ሊቀንስ ይችላል፡፡ እነርሱም ለ5 ዓመታት በቦታው ሊቀመጡ ይችላጉዳቶች፡ አይዩዲ በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን አይከላከልም፣ ከማህፀን ሊወጣ ይችላል፣ ከወር አበባ ጋር ተያይዞ (ህመሞች፣ የተለያዩ የወር አበባ ጊዜያቶች፣ ከባድ እና ረጅም የወር አበባ ጊዜያቶች) ችግሮች ሊፈጥር ይችላል፡፡
ማቋረጥ
አይህ ዘዴ ወንዱ ብልቱን ከሴቷ ብልት ውስጥ ከመርጨቱ በፊት ማውጣትን ይጠይቃል፡፡ ይህን ዘዴ ሊጠቀሙ የሚችሉት ሌላ ዘዴ ከሌለ ነው፡፡
በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን ሊከላከል የማይችል እና በወንዱ በኩል እጅግ በጣም ጥሩ የሆነ ራስን መቆጣጠር እና ልምድን ይጠይቃል፡፡
ይህ ዘዴ የማይታመን እና በግምት ከ18-19% ያለመስራት እድል ለው፡፡ ማንኛውም የእርግዝና ምልክት ካጋጠመዎት የእርግዝና መጣራት ማድረግ ይገባዎታል፡፡
ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ
ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ የወሊድ መቆጣጠርያ ሲሆን ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ የሚፈጠረውን እርግዝና ለመከላከል ነው፡፡ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያን ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ ወዲያው ወይም እስከ 5 ቀናት መጠቀም ይችላሉ፡፡ የወሊድ መቆጣጠርያዎ እንደማይሰራ፣ በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ ኮንዶሙ እንደተበጠሰ፣ በወርሀዊ ዑደት ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የወሊድ መቆጣጠርያ ኪኒኖች እንዳልወሰዱ ወይም የግብረ ስጋ ግንኙነት ተደፍረው እንዳደረጉ ካሰቡ ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡
ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ እርግዝና እንዳይከሰት ያደርጋል፡፡ ነገር ግን ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ልክ እንደ ኪኒን ወይም ኮንዶሞች ከግብረ ስጋ ግንኙነት በፊት ወይም በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት እንደ ሚወሰደው የወሊድ መቆጣጠርያ ውጤታማ አይደለም፡፡ ስለዚህ በግብረ ስጋ ግንኙነት ንቁ ከሆኑ ወይም ንቁ ለመሆን ካቀዱ፣ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ እርግዝናን ለመከላከል እንደ ብቸኛ መከላከያ አይጠቀሙ፡፡ በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን ወይም ከኤች አይ ቪ ኤድስን አይከላ ከልልዎም፡፡
ድንገተኛ የወሊድ መቆጣጠርያ በኪኒን ወይም በማህፀን ውስጥ በሚቀበር መሳርያ (አይዩዲ) መዳብ መልክ ይገኛል፡፡ ከልቅ ግብረ ስጋ ግንኙነት በ5 ቀናት ውስጥ ኪኒኖቹ መወሰድ ወይም በማህፀን ውስጥ የሚቀበርረው መሳርያ (አይዩዲ) መከተት ይኖርባቸዋል፡፡
ዲያፍራም
ዲያፍራም ስስ ላስቲክ፣ ክብ ቅርፅ ንጣፍ ሲሆን ስፐርም ወደ ማህፀን እንዳይገባ ለመከላከል በማሕፀን በር ላይ የሚሸፈን ነው፡፡
ዲያፍራም የሚሰራው አብዛኞቹን ስፐርሞች ወደ ማህፀን እንዳይገቡ በማገድ ነው፡፡ በመከላከያ ንጣፉ አካባቢ የተገኘ ማንኛውም ስፐርምን እንዲገድል ስፐርሚሳይድ ወደ ዲያፍራሙ ይጨመራል፡፡
ዲያፍራ ለትክክለኛ እና ቀጣይነት ላለው አጠቃቀም የመስራት እድል በግምት 5% አለው፡፡ ከትክለኛው አጠቃቀም ጉድለት የተነሳ በመጀመርያው አመት አጠቃቀም ከእያንዳንዱ 100 ሰዎች መካከል ከ 18 እስከ 20 የሚሆኑት ያረግዛሉ፡፡ ማንኛውም የእርግዝና ምልክቶች ካጋጠመዎት የእርግዝና መጣራት ማድረግ ይገባዎታል፡፡
ዲያፍራምን በመጠቀም በጣም የተለመደው የጎንዮሽ ጉዳት የሴት ብልት መቆጣት ነው፡፡ የላስቲክ አለርጂዎች፣ መርዛማ የንዝረት በሽታ ምልክቶች ታሪክ ያላቸው፣ የሴቷ ብልት ወይም የማህፀን በር ልክ ያለመሆን ተጨማሪ ችግሮች ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡
ዲያፍራም በወንዱ ወይም በሴቷ የመውለድ ስራ ላይ ምንም አይነት ጉዳት የለውም፡፡ ዲያፍራሞችን የማይጠቀሙ ከሆነ ወዲያው ማርገዝ ይችላሉ፡፡ ዲያፍራም በግብረ ስጋ ግንኙነት ከሚተላለፉ በሽታዎች ሊከላከል አይችልም፡፡
ተጨማሪ መረጃ በአካባቢዎ ካሉ የጤና ማዕከላት ማግኘት ይችላሉ፡፡
የእርግዝና መከላከያ
ብዙ ሴቶች እርግዝናን ለማዘግየት ወይም እንዳይከሰት ለማድረግ የእርግዝና መከላከያ መጠቀም ባሁኑ ጊዜ እየተለመደ ነዉ፡፡ የተጠቃሚዉን መጨመር ተከትሎ የተለያዩ እንክብሎች በየመድኃኒት ቤቱ መገኘት ጀምሯል፡፡
የእርግዝና መከላከያ ለባለትዳሮች አራርቆ ለመዉለድ እና ቁጥር ከመመጠኑም በተጨማሪ ጽንስ ማስወረድን ለማስቀረት ይረዳል፡፡ የእርግዝና መከላከያ ከጥቅሙ ባሻገር እንደየሰዉ ቢለያይም የተለያዩ ጉዳቶችን እንደሚያስከትሉ ይታወቃል፡፡
እርግዝና መከላከያ የሚያስከትሉ ችግሮች በዋናነት የሚጠቀሱት የራስ ምታት፣የማቅለሽለሽ እና የሰዉነት ዉፍረት መጨመር ይጠቀሳሉ፡፡
የእርግዝና መከላከያ ከመዉሰድ በፊት የተለያዩ ጥንቃቄዎችን መዉሰድ አለብን ፡፡
ለምሳሌ ፡- ሲጋራ የሚያጨስ ሰዉ፤የልብ በሽታ እና የማያቋርጥ ራስ ምታት ያለዉ ሰዉ፤ የሱኳር በሽታ ያለበት ሰዉ ፤ የጉበት በሽታ ያለበት ሰዉ እና እድሜዉ ከ35 አመት በላይ የሆኑ ሶቶች መድኃኒቱን ባይወስዱ ይመረጣል፡፡
የእርግዝና መከላከያ ሲወሰድ የጉበት ምርመራ እና የደም ዝዉዉር ሂደትን ስለሚገታ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡
ከብዙ አይነት የእርግዝና መከላከያዎች አብዛኛዉን ጊዜ በኛ ሀገር ህብረተሰቡ የሚጠቀምበትን እንይ፡፡
ኮንዶም
ኮንዶም ላልተፈለገ እርግዝና መከላከል የሚችል እና የግብረስጋ ግንኙነት አማካኝነት ከሚተላለፉ በሽታዎችን ይከላከላል፡፡ ወጣቶች ኮንዶምን በግብረስጋ ግንኙነት ጊዜ በጥንቃቄ ከተጠቀሙ ላልተፈለገ እርግዝና አይጋለጡም፡፡
ድንገተኛ እና አስቾኳይ ጊዜ የእርግዝና መከላከያ
የአስቾኳይ ጊዜ የእርግዝና መከላከያ ያልተጠበቀ ወሲባዊ ግንኙነትን እና በመደፈር እርግዝና እንዳይፈጠር ለመከላከል ይጠቅማል፡፡ የአስቾኳይ የእርግዝና መከላከያ ወሲባዊ ግንኙነት ከተፈጸመ በ72 ሰዓት ዉስጥ የሚወሰድ መከላከያ ነዉ፡፡
ይህ የእርግዝና መከላከያ ግብረስጋ ግብኙነት ከተፈጸመ በ72 ሰዓት መካክል ይወሰዳል፡፡ ነገር ግን እንክብሉን በመዘግየት መዉሰድ እንደየሰዓቱ ርቀት እርግዝናን የመከላከል ብቃቱ ይለያያል ቶሎ ከተወሰደ የመከላከል አቅሙ ጠንካራ ነዉ፡፡ ይህ የአስቾኳይ ጊዜ የእርግዝና መከላከያ ሲወሰድ የተዘጋጀችዉን እንቁላል ያፈራርሳል፡፡ በዚህ ክስተት የማህጸን ጊርጊዳን ሊነካ ስለሚችል ከአንድ ጊዜ በላይ ባይወሰድ ይመረጣል፡፡
ድንገተኛ እና አስቾኳይ ጊዜ የእርግዝና መከላከያ አላስፈላጊ እርግዝናን ለመከላከል ቢወሰድም አቅሙ ከፍተኛ በመሆኑ ይህን መከላከያ የሚወስዱት ሴቶች ላይ የተለያዩ የማህጸን ችግሮች ያጋልጣቸዋል፡፡
ድንገተኛ እና አስቾኳይ ጊዜ የእርግዝና መከላከያ በድግግሞሽ የሚወስዱ ሴቶች ለወደፊት ማህጸናቸዉ ጽንስ የመሸከም አቅምም ይደክማል፡፡ በተጨማሪም የማህጸን ኢንፌክሺን እና የማህጸን ቱቦአቸዉ ላይ ጉዳት ሊደርስበት ይችላል፡፡
በኛ ሀገር ብዙ ተጠቃሚዎችን ያለዉ እና በቂ ግንዛቤ ያልተጨበጠበት መድሃኒት ነዉ ብለዉ የጤና ባለሞያዎቹ ይገልጻሉ፡፡ ብዙ ወጣቶች በተደጋጋሚ ከመድሃት ቤት እንደሚገዙት እና ልክ እንደ ራስ ምታት መድሃኒት እንደሚወስዱት የፋርማሲ ባለሞያዎች ይገልጻሉ፡፡
ምንም እንኳን መከላከያዉ ላልተፈለገ እርግዝና የሚከላከል ቢሆንም ወጣቶቹ ሊያተኩሩበት የሚገባቸዉ ያለጥንቃቄ የሚፈጸመዉ ግብረስጋ ግንኙነት እራሳቸዉን መጠበቅ አለባቸዉ፡፡
ብዙ ወጣቶች ይህ ድንገተኛ እና አስቾኳይ ጊዜ የእርግዝና መከላከያ እርግዝናን እንጂ ኤች አይ ቪ ኤድስን እና የተለያዩ የአባላዘር
በሽታዎችን እንደማይከላከል ልብ ያላሉት እና ልብ ሊሉት የሚገባ ወሳኝ ነገር ነዉ፡፡
ድያፍራም ወይም የማህጸን ሽፋን
ድያፍራም የማህጸን ሽፋን ሲሆን የሴቷ ብልት ዉስጥ የሚገባ ፕላስቲክ ነገር ነዉ፡፡ ድያፍራም እርግዝናን የመከላከል ብቃት አለዉ፡፡ድያፍራምን ለመጠቀም የጤና ተቋማት በመሄድ በቀላሉ መጠቀም ይቻላል፡፡
የእርግዝና መከላከያ እንክብሎች
የእርግዝና መከላከያ ክኒኖች እንቁላል እንዳይኖር ይከላከላሉ። የእርግዝናመ ከላከያ ክኒን ለመጠቀም የተለያዩ አይነት በገበያ ላይ ይገኛል ስለዚህም ልዩነቶቹን የሚያዉቁ ባለሞያዎች ወይም በሐኪምትዕዛዝብንጠቀም ይመረጣል፡፡ የእርግዝና መከላከያ እንክብሎችን በአግባቡ ከተጠቀምን እርግዝና እንዳይፈጠር አስተማማኝ ነዉ፡፡እንደየመድሃኒቶቹ ቢለያዩሙ ለተለያዩ በሽታዎች መንስኤ ከመሆናቸዉ በተጨማሪም የጎንዮሽ ጉዳቱ ከፍተኛ ስለሆነ የሀኪም ክትትል አስፈላጊ ነዉ፡፡
ማህጸን ዉስጥ የሚቀመጥ የእርግዝና መከላከያ
IUD (intrauterine device) የእርግዝና መከላከያ በባለሞያ ማህጸን ዉስጥ የሚገባ የእርግዝና መከላከያ ነዉ፡፡ ይህ ሽቦመሰል የእርግዝና መከላከያ ማህጸንውስጥየሚኖረውየእንቁላልእድገትያስተጓጉለዋል ፡፡ ከ3 እስከ 6ቀን ምቾት ላይሰጥ ይችላል ከዛ ባለፈ ምንም አይነት ጉዳት አያስከትልም፡፡IUD ሚባል የእርግዝና መከላከያ ክኒን ከመዉሰድ እና በመርፌ የሚሰጠዉን የሆርሞን የእርግዝና መከላከያ ከመዉሰድ በማህጸን ዉስጥ የሚቀመጠዉን ቢጠቀሙ እርግዝናን የመከላከሉ ብቃቱም ከፍተኛ ነዉ፡፡ IUD እርግዝና መከላከያ የጎንዮሽ ጉዳትም ስለሌለዉ ይሄንን ከሀኪም ጋር በመመካከር እናቶች ቢጠቀሙ የተሻለ ነዉ ይላሉ የህክምና ባለሞያዎች፡፡
ቆዳስር የሚቀበረው የእርግዝና መከላከያ
የክንድ ቆዳ ስር የሚቀበረዉ የእርግዝና መከላከያ ለሦስት ወይምለ አምስት አመታት በሴቷ የጡንቻ ቆዳ ስር ይቀበራል።
ይህ የእርግዝና መከላከያ አርርቆ ለመዉለድ እና ለመዉለድ ባቀዱ ጊዜ በቀላሉ ያንን ክንድ ስር የሚቀበረዉን በማዉጣት መዉለድ ይችላሉ፡፡ይህንን መከላከያ ለመጠቀም የጤና ባለሞያ ጋር መሄድ እና በቀላሉ መጠቀም ይቻላል፡፡
ማህጸን ውስጥ የሚቀመጥ እንክብል
ማህጸን ውስጥ የሚቀመ ጥቀጭን ሽቦ ነዉ፡፡ ይህ ሽቦ እንቁላል ወደ ማህጸን እንዳይጣበቅ ይከላከላል፡፡ በተጨማሪም የወንዱ ዘር ወደ ማህጸን እንዳይገባ ይከላከላል፡፡ይህእንክብል ከአምስት እስከ አስር አመታት ባሉት ጊዜ ያትውስ ጥውጤታ ማሲሆን ጥሩ የእርግዝና መከላከያም ነው።