የወር አበባ መዘግየት መጥፋት

የወር አበባ ከሚመጣበት ጊዜ ሲዘገይ ብዙ ሴቶችን  የእርግዝና ጥርጣሬ ይገባቸዋል።   ነገር ግን የወር አበባ መጥፋት ወይም መዘግየት ከእርግዝና ጋር ቢያያዝም ሌሎች ምክንያቶችም ሊያዘገዩት አልፍም ሊያዘገዩት ይችላሉ።

መደበኛ  የሆነ የተስተካከለ የወር አበባ ዑደት ያላት ሴት የመጀመሪያው እና ትክክለኛ የነፍሰ ጡርነት ምልክት የወር አበባ መቅረት ነው::  የወር አበባ ከቀረበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ የእርግዝና ምርመራ ማካሄድ ይቻላል::  የተስተካከለ የወር አበባ ዑደት ከሌላት ለመጀመሪያ ጊዜ የነፍሰ ጡርነት ምርመራ ማካሄድ ያለባት ያለጥንቃቄ ወሲብ ከተደረገ ከሀያ አንድ ቀናት በኋላ መሆን አለበት::   ለአንዳንድ ሴቶች የወር አበባቸው አንድ ሳምንት ካልዘገየ በስተቀር ምርመራው ትክክለኛ ውጤት ላያሳይ ይችላል:፡  የእርግዝና ምርመራም የሚደረገው በነፍሰ ጡር ሴት ሽንት ላይ የሚገኘውን  የእርግዝና ሆርሞን በመፈለግ ይሆናል::  ምርመራው ፖዘተቭ ከሆነ ሁሌም ትክክል ነው::  ግን አንዳንድ  ጊዜ ምርመራው በጣም በጊዜ ሲካሄድ ወይም በትክክል ካልተከናወነ  ወይም መመርመሪያ  መሣሪያው ችግር ካለበት ትክክለኛ ውጤት ላያሳይ ይችላል:፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *