የእርግዝና ግንኙነት

በአንድ  የወሲብ ግንኙነት ከ 20 ሚሊዮን እስከ 300 ሚሊዮን የወንድ ዘር ወይም ስፐርም  የሚወጣ ሲሆን፤ ከነዚህ ሚሊየኖች ውስጥ አንዱ የወንድ ዘር ብቻ ወደ እንቁላሉ ይገባል:: በመጀመሪያው  ሁለት ቀናት   ብዙ ስፐርሞች በማህፀን ውስጥ ይሞታሉ፡፡  ነገር  ግን  የወንድ ዘር በማህፀንና በፋሎፒያን  ቱቦ ውስጥ እስከ አምስት አልፎም እስከ ሰባት ቀናት መቆየት ይችላል፤ እናም ልክ እንቁላል በወጣበት ጊዜ ሊያገኘው ይችላል:: ከስንት አንድ ቢሆንም እስከ ሰባት ቀን በማህፀን ውስጥ በህይወት ቆይቶ እንቁላልን ሊያገኝ  የሚችል የወንድ ዘር ወይም ስፐርም ሊኖር ይችላል፡፡

በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከ2 እስከ 3 ጊዜ ወሲብ  የሚያደርጉ ከሆነ፣ በዛሳምንት ውስጥ የምትወጣን እንቁላል የሚጠብቅ የወንድ ዘር በማህፀን ውስጥ ሊኖር ይችላል::  አንዳንድ ሰዎች ለመፀነስ፣ ልክ እንቁላሉ  በፈራበት ጊዜ ወሲብ በማድረግ ብቻ እንደሆነ ያምናሉ፣ ይህ ግን ብቸኛ እውነት አይደለም::  በአጠቃላይ የሴቷ የወር አበባ ከታየበት የመጀመሪያ ቀን ጀምረን አንድ ብለን ቆጠራ ብንጀምር፣ ከስምንተኛው  ቀን እስከ  አስራ ዘጠነኛው ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ የግብረስጋ  ግንኙነት ብንፈጽም እርግዝና ሊከሰት ይችላል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *