ሁለተኛው ሶስት ወር ከ 13 እስከ 26 ሳምንት ያለው ነው፣ ይህም የእርግዝና አስደሳቹ የእድገት ደረጃ ነው::
በዚህ በሁለተኛው ሶስት ወር ጊዜ ውስጥም አንቺም ሆንሽ ባለቤትሽ ልጃችሁን ለመጀመሪያ ጊዜ በ አልትራሳውንድ ስካን ታዩታላችሁ:: አብዛኞቹ ሆስፒታሎች የልጃችሁን የስካን ፎቶ ይሰጧችኋል:: በአንዳንድ አጋጣሚወችም የልጃችሁን ጾታ የመለየት አጋጣሚውን ልታገኙ ትችላላችሁ፣ ይህም በስካን ወቅት የሚከሰት ይሆናል::
አንዲት ነፍሰጡር ለራሷም ሆነ ለፅንሷ ጤንነት ሲባል የተለያዩ ጥንቃቄዎች በመጀመሪያዎቹ ወራት ስታደርጋቸዉ የነበሩ ጥንቃቄዎችን ቀጥላ ማድረግ ይኖርባታል። በተጨማሪም ማድረግ የሌለባትና ልታደርጋቸዉ የሚገቡ ነገሮችን ማወቅ አለባት፡፡
ከ4ኛ እስከ 6ኛ ወራት ልታደርጊያቸው የሚገቡ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፤ በየቀኑ ገላን መታጠብ፤ በቂ ዕረፍት ማድረግ፤ በግራ ጎን እስከተቻለ ድረስ መተኛት፤ ሰውነትን ዘና ሊያደርግ የሚችልና የሚመች መቀመጫ ላይ መቀመጥ እና የጥርስን ንፅህና መጠበቅ ይኖርባታል፡፡ በተጨማሪም በነዚህ ወራት ማድረግ የሌለባት ለረዥም ሰዓት መቆም እንዲሁም ጠባብ ልብሶችን አለመልበስ እና ከባድ እቃዎችን መሸከም የለባትም፡፡
ሁሉም ሴቶች የተለያዩ ናቸው ቢሆንም ግን አብዛኞቹ ሴቶች በሁለተኛው የሶስት ወር ጊዜ ውስጥ እንደ ማቅለሽለሽ ያሉ በሽታወች እንደሚቀንስላቸው ይገልጻሉ:: ይህም ማለት ባለቤትሽ በእርግዝናሽ ይበልጥ ደስተኛ ይሆናል::
አብዛኞቹ ጥንዶች ለልጃቸው የሚያስፈልጉ ነገሮችን መግዛት ያስደስታቸዋል እናም እናንተ ልጃችሁ በሆስፒታል የሚቆይበትን ቦታ ማመቻቸት ያስፈልጋችኋል፣ ምክንያቱም አብዛኛውን ጊዜ ለልጆች የሚያስፈልጉ ነገሮችን ማሟላት ጊዜ ይወስዳል::