ሁለተኛው ሶስት ወራት ከ13 እስከ 26 ሳምንት
ሁለተኛው ሶስት ወር ከ 13 እስከ 26 ሳምንት ያለው ነው፣ ይህም የእርግዝና አስደሳቹ የእድገት ደረጃ ነው::
በዚህ በሁለተኛው ሶስት ወር ጊዜ ውስጥም አንቺም ሆንሽ ባለቤትሽ ልጃችሁን ለመጀመሪያ ጊዜ በ አልትራሳውንድ ስካን ታዩታላችሁ:: አብዛኞቹ ሆስፒታሎች የልጃችሁን የስካን ፎቶ ይሰጧችኋል:: በአንዳንድ አጋጣሚወችም የልጃችሁን ጾታ የመለየት አጋጣሚውን ልታገኙ ትችላላችሁ፣ ይህም በስካን ወቅት የሚከሰት ይሆናል::
አንዲት ነፍሰጡር ለራሷም ሆነ ለፅንሷ ጤንነት ሲባል የተለያዩ ጥንቃቄዎች በመጀመሪያዎቹ ወራት ስታደርጋቸዉ የነበሩ ጥንቃቄዎችን ቀጥላ ማድረግ ይኖርባታል። በተጨማሪም ማድረግ የሌለባትና ልታደርጋቸዉ የሚገቡ ነገሮችን ማወቅ አለባት፡፡
ከ4ኛ እስከ 6ኛ ወራት ልታደርጊያቸው የሚገቡ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፤ በየቀኑ ገላን መታጠብ፤ በቂ ዕረፍት ማድረግ፤ በግራ ጎን እስከተቻለ ድረስ መተኛት፤ ሰውነትን ዘና ሊያደርግ የሚችልና የሚመች መቀመጫ ላይ መቀመጥ እና የጥርስን ንፅህና መጠበቅ ይኖርባታል፡፡ በተጨማሪም በነዚህ ወራት ማድረግ የሌለባት ለረዥም ሰዓት መቆም እንዲሁም ጠባብ ልብሶችን አለመልበስ እና ከባድ እቃዎችን መሸከም የለባትም፡፡

ሁሉም ሴቶች የተለያዩ ናቸው ቢሆንም ግን አብዛኞቹ ሴቶች በሁለተኛው የሶስት ወር ጊዜ ውስጥ እንደ ማቅለሽለሽ ያሉ በሽታወች እንደሚቀንስላቸው ይገልጻሉ:: ይህም ማለት ባለቤትሽ በእርግዝናሽ ይበልጥ ደስተኛ ይሆናል::
አብዛኞቹ ጥንዶች ለልጃቸው የሚያስፈልጉ ነገሮችን መግዛት ያስደስታቸዋል እናም እናንተ ልጃችሁ በሆስፒታል የሚቆይበትን ቦታ ማመቻቸት ያስፈልጋችኋል፣ ምክንያቱም አብዛኛውን ጊዜ ለልጆች የሚያስፈልጉ ነገሮችን ማሟላት ጊዜ ይወስዳል::
በ13ኛዉ ሳምንት
የእጅ እና የእግር ጣቶች በግልጽ ይለያሉ፣ ግን ከአጥንት ድር ጋር እንደተጣበቁ ይቆያሉ:: በመጀመሪያው ሶስት ወር ጊዜያት አካባቢ ድርብርብ የማጣራት ሙከራ(የእናት ደም + የጽንሱ አልትራሳውንድ) ይደረጋል:: በዚህ ጊዜ ሽሉ በጠንካራ ጉልበት በሚገባ ይዋኛል:: አሁን ላይ ወደ 7 ሳሜ አካባቢ ርዝመት አለው::
በዚህ ወቅት ወተት መሳይና የተለየጠረንያለውየብልት ፈሳሽሊኖር ይችላል። ፈሳሹ የማህፀ ንኢንፌክሽንን የሚከላከል ሲሆን በሚቀጥሉት ሳምንታት የፈሳሹ መጠንሊጨምር ስለሚችል በቂ የውስጥሱሪዎችን ማዘጋጀት ተገቢ ነው።
በ14ኛዉ ሳምንት
የአይን ሽፋሽፍቱም በደንብ ከአደገው አይኑ ላይ ይጣበቃል:: ጽንሱም የድምጽ ጅማቶች ሲኖረው፣ ድምጽ ሳያሰማ ማልቀስ ይጀምራል:: ጣቱንም መጥባት ሊጀምር ይችላል:: የእጅ እና የእግር ጣቶቹም ጥፍር ማብቀል ይጀምራሉ::
በ15ኛዉ ሳምንት
በዚህ ወቅት ከእርግዝና ሆርሞኖች የተነሳ የድድ ማበጥ እና መድማት እንዲሁም የአፍንጫ መደፈን እና ነስር ሊያጋጥም ይችላል።
በ16ኛዉ ሳምንት
ሽሉም ወደ 14 ሳሜ ርዝመት ይኖረዋል:: ቅንድብና ሽፋሽፍቶቹ ብቅ ማለት ይጀምራሉ፣ ምላሱም ጅማቶች ይኖሩታል::
በ17ኛዉ ሳምንት
ልጁ ብርሀን እና ጨለማ መለየት ይጀምራል። ከማህፀን ውስጥ እና ውጭ ያለ ድምፅ መስማት ይጀምራል። በሂደትም የእናቱን ድምፅ ከሌላ ሰው ለይቶ ማወቅ ይጀምራል።
በ18ኛዉ ሳምንት
የአልትራሳውንድ ምርመራ የሚካሄደውም፣ በመዋቅር ደረጃ ከተፈጥሮ የተለየ መሆን አለመሆኑን፣ የእንግዴ ልጁን አቀማመጥ እና የእርግዝና ድግግሞሽን ነው:: አስደናቂ የሚያደርገውም፣ ጥቃቅን የሽሉ ድርጊቶች የሚታዩ መሆናቸው ነው::
በ19ኛዉ ሳምንት
የልጃችሁ የደም ዝውውር መስመሮች ስራቸውን ይጀምራሉ። በዚህ ጊዜ የልጁ ፆታ በአልትራ ሳውንድ አማካኝነት መለየት ይቻላላ። ሴት ከሆነች ማህፀኗ እና የማህፀን ቱቦ ፤ ወንድ ከሆነም የመራቢያ አካላቱ ተለይተው ይታያሉ።