የወር አበባ መዘግየት መጥፋት

የወር አበባ ከሚመጣበት ጊዜ ሲዘገይ ብዙ ሴቶችን የእርግዝና ጥርጣሬ ይገባቸዋል። ነገር ግን የወር አበባ መጥፋት ወይም መዘግየት ከእርግዝና ጋር ቢያያዝም ሌሎች ምክንያቶችም ሊያዘገዩት አልፍም ሊያዘገዩት ይችላሉ።

መደበኛ የሆነ የተስተካከለ የወር አበባ ዑደት ያላት ሴት የመጀመሪያው እና ትክክለኛ የነፍሰ ጡርነት ምልክት የወር አበባ መቅረት ነው። የወር አበባ ከቀረበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ የእርግዝና ምርመራ ማካሄድ ይቻላል።

የተስተካከለ የወር አበባ ዑደት ከሌላት ለመጀመሪያ ጊዜ የነፍሰ ጡርነት ምርመራ ማካሄድ ያለባት ያለጥንቃቄ ወሲብ ከተደረገ ከሀያ አንድ ቀናት በኋላ መሆን አለበት።

ለአንዳንድ ሴቶች የወር አበባቸው አንድ ሳምንት ካልዘገየ በስተቀር ምርመራው ትክክለኛ ውጤት ላያሳይ ይችላል።

የእርግዝና ምርመራም የሚደረገው በነፍሰ ጡር ሴት ሽንት ላይ የሚገኘውን የእርግዝና ሆርሞን በመፈለግ ይሆናል። ምርመራው ፖዘተቭ ከሆነ ሁሌም ትክክል ነው። ግን አንዳንድ ጊዜ ምርመራው በጣም በጊዜ ሲካሄድ ወይም በትክክል ካልተከናወነ ወይም መመርመሪያ መሣሪያው ችግር ካለበት ትክክለኛ ውጤት ላያሳይ ይችላል።

የጽንስ አጀማመር

ነፍሰ ጡር ለመሆን (መፀነስ ለመጀመር) እንቁላል በወንድ ዘር በልጽጋ በማህፀን ውስጥ መቀመጥ አለበት። የጽንስ አጀማመርም እንቁላልን ከማበልጸግ የሚጀምርና የበለጸገች እንቁላል በተሳካ ሁኔታ በማህፀን ውስጥ መቀመጥ ነው።

በእያንዳንዱ የወር አበባ ጊዜ የበለጸገች እንቁላል ከኦቫሪ ትለቀቃለች። እንቁላሉ ከተለቀቀ በኋላ በዛ በተወሰነ ጊዜ ብቻ እርጉዝ ይኮናል። እንቁላሉም ከፋሎፒያን ቱቦ ወደ ታች ማህፀን ይጓዛል።

እንቁላል ሊኖር የሚችለው ቢበዛ እስከ 24 ሰዓት ድረስ ነው። በእያንዳንዱ ወር፣ የማህፀን ግድግዳ ሊከሰት ለሚችል እርግዝና ይዘጋጃል።

የእርግዝና ወቅት ማለት በወንድ ዘር የዳበረችው እንቁላል ማህፀን ውስጥ ማደግ ከጀመረችበት ቀን ጀምሮ ወደፊት ልጅ እስከሚወለድበት ቀን ድረስ ያለው ጊዜ ነው።

አብዛኛው እርግዝና ለ 9 ወራት ወይም ለ40 ሳምንታት ያህል ጊዜ ይቆያል። አንድ እርግዝና መቆጠር የሚጀምረው የወር አበባ ከቆመበት ቀን ጀምሮ ወይም ዋናው ጽንስ ከማጋጠሙ በፊት ያሉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ነው።

የወር አበባው መጨረሻ ከታየ ከአርባ ሳምንታት በኋላ ልጅ ይወለዳል።