የወሊድ ዕቅድ ማውጣት በወሊድ ጊዜ ብዙ ሁኔታዎችን በምትፈልጓቸው መልኩ ለማመቻቸት ይረዳችኋል።
የወሊድ ዕቅዳችሁን በምታወጡበት ጊዜ ልታስቧቸው ከሚገቡ ነገሮች መካከል ጥቂቶቹ፡-
- ከጤና ባለሙያ ጋር በመሆን የት ለመውለድ እንዳሰባችሁ ማቀድ ያስፈልጋል።
- በቅርብ የሚገኘው የጤና ማዕከል ወይም ሆስፒታል የት እንደሚገኝ ማወቁ ጠቃሚ ነው።
- ከጤና ባለሙያ ጋር በመሆን የት ለመውለድ እንዳሰባችሁ ማቀድ ያስፈልጋል።
- በቅርብ የሚገኘው የጤና ማዕከል ወይም ሆስፒታል የት እንደሚገኝ ማወቁ ጠቃሚ ነው።
- ለመጓጓዣና ለተለያዩ የሕክምና ወጪዎች ገንዘብ ማዘጋጀት
- መጓጓዣ በቀላሉ የሚገኝበትን መንገድ ማመቻቸት
- በወሊድ ወቅት ሊረዳ የሚችል የቤተሰብ አባል በቅርብ እንዲኖር ማድረግ
- ለህፃኑ የሚሆን ልብሶችና የመኝታ ቦታ ማመቻቸት
- ከወሊድ በኋላ እናቲቱ የምትመገበውን ምግብ ቀደም ብሎ ማሰናዳት፡፡
የት እና ማን እንደሚያዋልድሽ ማወቅ
- ለሕክምና እና ለትራንስፖርት ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያስፈልግ ማቀድ በእርግዝና ወቅትም ሆነ ከእርግዝና በኋላ ወላጆች የተለያዩ ወጪዎች ይኖሩባቸዋል። ስለዚህ በእርግዝና ጊዜ በየወሩ የተወሰነ ገንዘብ ተቀማጭ ማድረጉ አስፈላጊ ነው።
- በተጨማሪም በእርግዝና ወቅት ወደ ህክምና ቦታ ለመሄድ እንዲሁም ምጥ በሚመጣበት ጊዜ ለመውለድ ወደታቀደበት ተቋም ለመሄድ መጓጓዣ ቀድሞ ማዘጋጀት ያስፈልጋል።
ለምሳሌ፡- ታክሲ አናግሮ የሹፌሩን ስልክ መያዝ ወይም መኪና ያለውን ዘመድ አናግሮ ተዘጋጅቶ
መጠበቅ በጣም አስፈላጊ ነው።