ቅድመ ወሊድ ክትትል

በቅድመ  ወሊድ ስለሚሰጡ የሕክምና ክትትሎች መረጃዎች

አንዲት ነፍሰጡር ከትዳር አጋርዋ ጋር ሆና ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ተገቢውን የቅድመ ወሊድ ክትትል ማድረጓ ለራሷም ሆነ በማህፀኗ ውስጥ ላለው ህፃን ጤንነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው።

አንዲት ሴት ነፍሰጡር መሆኗን ካረጋገጠች ቡኋላ ከመውለዷ  በፊት ቢያንስ አራት ጊዜ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ የቅድመ ወሊድ ምርመራ ማግኘት ይኖርባታል። የእርግዝና ምልክቶችን እንዳየች  ወዲያውኑ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ተጨማሪ የህክምና ክትትል ማግኘት  ይኖርባታል።

ወላጆች የቅድመ ወሊድ ክትትል በማድረግ የሚያገኙት ጥቅም፡-

የተስተካከለ የእርግዝና ሁኔታ መኖሩን ለማረጋገጥ እና የህፃኑን ዕድገት እና ጤና ለመከታተል እንዲሁም ከእርግዝና ጋር የተያያዘ ከዚህ ቀደም ያጋጠመ የጤና ችግር ካለ ከዶክተር ጋር ተነጋግሮ ችግሩን  መፍታት  በተጨማሪም ወደፊት ሊያጋጥም የሚችል የጤና ችግር ካለ ቀድመ ጥንቃቄ ለማድረግና  ለመከላከል ይረዳናል።

ተከታታይ የሆነ የጤና ክትትል ለማድረግ ፣ በእርግዝና ወቅትና ከእርግዝና በኋላ የግል ጤንነት ለመጠበቅ እና የኤች.አይ.ቪ. ምክርና የምርመራ አገልግሎት ለማድረግ፣ስለ ተመጣጠነ የአመጋገብ ስርዓት  ምክር ይሰጣቸዋል።

ስለቤተሰብ ዕቅድ የምክር አገልግሎት  እንዲሁም በጤና ተቋም የመውለድን ጥቅም ይማራሉ፤ስለ ልጃቸው አመጋገብ መረጃ ያገኛሉ።