የህፃንን ውልደት ማክበር በቤተሰብ ውስጥ በጣም አስደሳች ጊዜ ነው:: የጨቅላ ህፃን ህይወት እና ዘላቂ ጤንነት በብዙ ነገሮች ይወሰናል፤ ከነዚህም ውስጥ የእናቲት እድሜ፣ በእርግዝና እና ከእርግዝና በኋላ ያለው ባህርይና የጤና ሁኔታ:: የጤና ተመራማሪዎች ለጨቅላ ህጻን ሞት ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ ያሏቸው ነገሮች የሚከተሉት ናቸው::
- የእናቲቱ ከመጀመሪያው በህክምና የታገዘ የእርግዝና እንክብካቤ አለማግኘት፤ ከዘገየ
- የአኗኗር ዘየ ላይፍ ስታይል፤ ማጨስ፣ ደካማ አመጋገብ፣ ውፍረት፣ ከባድ ጭንቀት ውጥረት፣ የቤት ውስጥ ብጥብጥ፣ ዝቅተኛ የእናትነት ጊዜ ክብደት
- ጊዜውን ያልጠበቀ ምጥ፤ እርግዝና ጊዜውን ሳይጨርስ አካላችሁ ለመውለድ ሲዘጋጅ::
ፆታ -ወንድወይምሴት
ፆታ -ወንድወይምሴት ልጅ
በእርግዝና ወቅት ወላጆች የፅንሱን ፆታ ለማወቅ ይጓጋሉ፡፡ የወዳጅ የዘመድ የመጀመሪያ ጥያቄ ወንድ ነዉ ወይስ ሴት ልጅ የሚለዉ ሲሆን ቀጥሎም የልጁ ስም መጠየቅ የተለመደ ነው፡፡
ፆታ የሚፈጠረዉ ልክ የወንዴዉ ዘርና የሴቷ እንቁላል በሚገናኙበት በፅንሰት ወቅት ይወሰናል፤ ነገር ግን እስከ20 እንዲሁም 21ኛ ሳምንት ድረስ የፆታው ምንነት በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም፡፡ ሁኖም ግን ከ19ኛ ሳምንት ቡኃላ በአልትራሳዉንድ የሚወለደዉ ልጅ ፆታ ማወቅ ይቻላል፡፡
ፆታ የሚፈጠረዉ በፅንሰት ጊዜ ቢሆንም ከእርግዝና ሰባተኛ ሳምንት ጀምሮ የወንዱም የሴቷም ፆታ አከላዊ ፍጥረት ይጀምራል፤ ይህም ማለት የወንዱም የሴቷም የፆታ ክፍሎች ቦታ ቦታቸዉን መያዝ ይጀምራሉ፡፡ እስከ 9ኛ ሳምንት ድረስ የወንዱም ሆነየሴት ፆታ ቅርፃቸዉ አንድ አይነት ቢሆንም ከዛ ቡኃላ ግን የወንዱም የሴቷም ፆታ ክፍሎች ትክክለኛ መልካቸዉን መያዝይጀምራሉ፡፡ እርግዝና የሚቆጠረዉ ከፅንሰት ሁለት ሳምንት ቀደም ብሎ ስለሆነ ፆታ ማወቅ የሚቻለዉ በዚህኛዉ አቆጣጠር ከ19 ሳምንታት ቡሃላ ነዉ፡፡ ነገር ግን ፅንሰት ከተፈጠረበት ወደፊት ከ17 ሳምንት ቡሃላ ማወቅይቻላል ሁለቱም አንድ አይነት ቢሆንም 19 ሳምንት የሚባለዉ እርግዝና መቆጠርየሚጀምረዉ ከፅንሰት 2 ሳምንት ቀደም ብሎ በመሆኑ ነዉ፡፡
የፆታ -መላምት
እናቶች ከልምድ በመነሳት የሚወልዱትን ልጅ ፆታ የሚገምቱባቸዉአንዳንድ ምልክቶች አሉ፡፡ እነዚህ ምልክቶች በእርግጠኝነት ፆታዉን መናገር ባያስችሉም ከልምድ በመነሳት እናቶች የዘየዱት መላምት ነው፡፡ አልፎ አልፎ ልክ ሊሆን ይችላል፤ ላይሆንም ይችላል፡፡ ከነዚህ ዉስጥ ጥቂቶቹን ለመግለፅ እንሞክራለን
- በእርግዝና ጊዜ የሚሰማ የጡዋት ጡዋት የህመም ስሜት ቶሎ ከጀመረ የሚወለደዉ ልጅ ፆታ ሴት ሊሆን ይችላል ፡፡ ማለትም በእርግዝና ወቅት የሚሰማ ህመም ልክ እርግዝናዉየሚታወቅበት የመጀመሪያ ወራቶች ከጀመረ የሚወለደዉ ልጅ የሴት ፆታ ሊኖራት ይችላል፡፡
- ሁለተኛዉ የእንቅልፍ አተኛኘት ሁኔታበእርግዝና ወቅት እንቅልፍ ስትተኚ ወደ ግራጎን መተኛት የሚያስመርጥሽ ከሆነ የሚወለደዉ ልጅ ፆታዉ ወንድ ነዉ
- የእንቅልፍ አተኛኘትሽወደ ቀኝ በኩል መተኛትን የምትመርጪ ከሆነ የሚወለደዉ ልጅ ፆታ ሴት ልትሆን ትችላለች ፡፡
- የሆድ ህመም መጠኑ ሀይለኛ ከሆነ ሴት ልትወልጂ ትቺያለሽ ፡፡
- የእርጉዝ ሴት እጅ በጣም የመድረቅ ባህሪ ካመጣ የሚወለደዉ ልጅ ወንድ ሊሆን ይችላል፡፡
- የእርጉዝ ሴት እጆች በጣም ረጠብ የሚሉ ከሆነ የሚትወለደዉ ልጅ ሴት ልትሆን ትችላለች፡፡
- የእርጉዝ ሴት ፊት የማበጥና የመወፈር ምልክት ከታየባት የሚትወለደዉ ልጅ ሴት ልትሆን ትችላለች፡፡
- በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የጡዋት ህመም ከበዛ ወይንምበእርግዝና የመጀመሪያ ወራቶችቶሎ ከጀመረ የሚወለደዉ ልጅ ሴት ትሆናለች የሚልመላምቶች አሉ፡፡
ባጠቃላይብዙ መላምቶች ቢኖሩም የሚወለደዉ ልጅ ፆታበትክክለኛ የሚታወቅበት መንገድ በአልትራሳዉንድ ሲሆን በእግዝና ወቅትከ 18 እስከ 22ኛ ባሉት ሳምንታትዉስጥ የሚታወቅ ነዉ፡፡ ይህም አልትራሳዉንዱ ጥሩ የሆነ ምስል ካሳየ ሲሆን ከ21ኛ ሳምንታት ቡኃላ ግን አልትራሳዉንዶች በአብዛኛዉ በትክክል ያሳያሉ፡፡ መልካም ዕድል!