የእርግዝና ክብደት ለመቀነስ

ክብደት ለመቀነስ ተመገቡ፣ በቀን ውስጥ 3 ብዙ ምግብ ከመብላት ይልቅ ከ5 እስከ 6 መጠነኛ ምግቦችን መመገብ ይመከራል፣ ቁርስ መብላት፣ በቂ ምግብ እስከጥጋብ ድረስ መብላት፣ በጣም አለመጥገብ፣ ብዙ ላለመብላት ራስን መቆጣጠር፣ የቅባት መጠን መቀነስ ወይም ከቅባት ነጻ የሆኑ የወተት ተዋጽኦ መመገብ፣ በቀን ውስጥ 8 ወይም 9 ኩባያ ፈሳሽ መጠጣት፤ እንደ ሶዳ ለስላሳ ወይም የታሸጉ ጁስ ጭማቂዎችንና እንዲሁም ስኳር እና ካሎሪ ካላቸው መጠጦች መቆጠብ:: ጣፋጭ፣ ስኳር እና ቅባት ከሆኑ ምግቦች መቆጠብ ይመከራል::

ምናልባት ግን ልክ ከእርግዝና በፊት እንደነበራችሁበት ክብደት ወይም ቅርጽ ላትመለሱ ትችላላችሁ:: ለአብዛኞቹ ሴቶች፣ እርግዝና በአካላቸው ላይ ዘላቂ የሆነ ለውጥ ያስከትላል::  የተለሳለሰ ሆድ፣ ሰፊ ዳሌ፣ እናም ተለቅ ያለ ወገብ ይኖራችኋል::

በአጠቃላይ፣ ራሳችሁን ያን ያህል አትወጥሩት:: ብዙ እናቶች ወደ ቅድመ እርግዝና ክብደታቸው የሚመለሱት ልጃቸው 1 አመት ሲሆነው አካባቢ ነው::