ከወሊድ በኋላ ወሲብ ከማድረግ መቆጠብ አለባችሁ፣ ምክንያቱም ከወሊድ በኋላ የሚከሰት ማንኛውም አይነት የደም ፍሳሽ እስኪቆም መጠበቅ ያስፈልጋል፤
ይህም ህጻኑን ከወለዳችሁ በኋላ እስከ ሶስት ሳምንት ማለት ነው። አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ደግሞ ህጻኑ ከተወለደ በኋላ እስከ ስድስት ሳምንት እንዲጠብቁ ይመክራሉ።
አንዳንድ ጥናቶች ከወሊድ በኋላ እስከ ስድስት ሳምንት ወሲብ ከማድረግ እንዲጠብቁ ይመክራሉ።
ከወሊድ በኋላም፣ በመጀመሪያዎቹ ሳምንታት እና ወራት ውስጥ በወሲብ ጊዜ ስሜት አልባ መሆን በብዙዎች የሚከሰት ነው።
ከእንቅልፍ ማጣት የተነሳም የድካም ስሜት ሊሰማችሁ ይችላል፣ እናት ከመሆን የተነሳም ብዙ ፍላጎቶች ሊኖሯችሁ ይችላል።
ጡት በምታጠቡበት ጊዜም፣ ፕሮላክቲን የተባለው ሆርሞን የወሲብ ፍላጎታችሁን ሊቀንሰው ይችላል።