ከወሊድ በኋላ

ከወሊድ በኋላ በሁሉም ሴቶች ላይ የሚያጋጥሙ የተለያዩ ምልክቶች አሉ። ከእነዚህ ጥቂቶቹ ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የድካም ስሜት፣ በጡት አካባቢ የህመም ስሜት መሰማት፣ የጡት ወተት መፍሰስ ናቸዉ።

እናቶች ከወሊድ በኋላ የሚፈስ ደም መቀነሱንና መቆሙን ማረጋገጥ አለባቸው።  በቂ ዕረፍት ማድረግ እና የተመጣጠነ ምግብ መመገብ አለባቸው።

  • ለድኅረ ወሊድ ክትትል ወደ ጤና ተቋም ሄዶ ለእናትና ለህፃኑ አስፈላጊውን ሕክምና ማድረግ፤
  • በቀን ውስጥ የምትችሉትን ያህል የእንቅልፍ ሸለብታ ለማግኘት መሞከር፤ ሲመሽ ወደ መኝታም በጊዜ መሄድ፤ ቢያንስ ህጻኑ ሌሊቱን ሙሉ መተኛት እስኪችል ድረስ
  • በወሊድ ግዜ የቆዳ ለቆዳ ንኪኪ ማድረግ ልጅዎን ጡት ለማጠባት መሞከር ጥሩ ጅምር ሊሆን ይችላል። ከወሊድ በኋላ ሁሉም ነገር ጤነኛ እና የተረጋጋ ከሆነ የጤና እንክብካቤ ለሚያደርግልዎ ሰው ልጁዎን በደረትዎ ላይ እንዲያስቀምጥልዎ ይጠይቁ።
  • ለህጻኑ በቂ ጡት መስጠት፤ ይህ ለአንዳንድ እናቶች ክብደታቸውን እንዲያስተካክሉ ይረዳቸዋል
  • ከወሊድ በኋላ ወሲብ ከማድረግ መቆጠብ፤ አንዳንድ ጥናቶች ከወሊድ በኋላ እስከ ስድስት ሳምንት እንዲጠብቁ ይመክራሉ።
  • በህክምና ባለሙያ የታዘዘላችሁን መድሀኒት በሚገባ መውሰድ
  • በአራስነት ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደገኛ የጤና ምልክቶችን አውቆ ጤናን መከታተል ይገባል።

ጡት ማጥባት

እንደ አዲስ ወላጅ በጣም ብዙ አስፈላጊ የሆኑ ውሳኔዎችን መወሰን አለበዎት። አንዱ ልጁዋትን ጡት ማጥባት ነው ያለብኝ ወይም የአራስ ልጆችን የድቄት ወተት በመጠቀም ጡጦ ማጥባትን መምረጥ። የጤና ባለሙያዎች ጡት ማጥባት ለእናትየውም ሆነ ለህፃኑ እጅግ በጣም ቴናማ የሆነ አማራጭ ነው ብለው ይስማማሉ።

እናቶች ጡት ከማጥባት የሚያግዷቸው በጣም የተወሰኑ የጤና ችግሮች ናቸው ያሉት። ይሁን እንጂ ጥሩ የሚባል ድጋፍ በመስጠት እና በእውቀት አብዛኞቹ እነኝህ ችግሮችን መቋቋም ይችላል።