በእርግዝና ወቅት የጤና ሁኔታዎች
በእርግዝና ወቅት ከመጀመሪያው በሰውነት ላይ የሚከሰቱ የተለያዩ አካላዊ ለውጦች ይኖራሉ። ለምሳሌ የመድከምና ቶሎ ቶሎ የመተንፈስ ስሜት፣ ማቅለሽለሽ ማስመለስና ማስታወክ፣ የሙቀት ስሜትና ላብ በእርግዝና ወቅት ሌላ ምንም አይነት ችግር ሳይኖር ልናያቸው የምንችላቸው ስሜቶች ናቸው። አንዳንድ ምልክቶች በእርግዝና ወቅት ሙሉ ሊቀጥሉ ይችላሉ።በእርግዝና ወቅት ተደጋግመው የሚታዩ ምልክቶች እና ራስሽ ልትወስጃቸው የምትችያቸውን መፍትሔዎች ያሳያል።
በእርግዝና ጊዜ ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ የሚሆን ነገሮችን በማድረግ ችግሮቹን መቆጣጠር ይችላል።
ደረት አካባቢ ወይም ጨጓራን የማቃጠል ስሜት መሰማት የምግብ ፍላጎት መቀያየር፤የምግብ ማስጠላት ወይም ፍላጎት መጨመር፤የምግብ መክበድና አለመዋሀድ ስጀምር ፡-ቅምማ ቅመም የበዛበት ምግቦችን ማስወገድ እና የምግብ መጠን እየቀነሱ መመገብና ቀለል ያሉትን ምግቦች በመመገብ መቆጣጠር ይቻላል።
- የሆድ ድርቀትን ለመከላከል ፍራፍሬና አረንጓዴ አትክልቶችን አብዝቶ መመገብ እና ብዙ ውሃ መጠጣት
- የእግር እብጠትን ለመከላከል ጠባብ ልብሶችን አለመልበስ፣
- ለረዥም ሰዓት አለመቆም፣
- በቂ እረፍት ማድረግ እና እግርን ከወገብ ከፍ ያለ ቦታ ላይ አድርጎ ጋደም ለማለት መሞከር
- ለማቅለሽለሽ እና ለመሳሰሉት መፍትሄው ቅባትና ቅመም ያላቸዉ ምግቦችን አለመመገብ እንዲሁም ትንሽ ትንሽ እና ቶሎ ቶሎ በመመገብ ችግሮቹን መቆጣጠር ይቻላል።
ልብ በሉ!
እነዚህ መፍትሔዎች (ለምሳሌ፡– እረፍት ማድረግ፣ አመጋገብን ማስተካከል፣ ወዘተ) ችግሮቹን ካልቀነሱ ወደ ጤና ተቋም ሄዶ ሀኪም ማማከር ያስፈልጋል።