Skip to content (Press Enter)
የወንድ ኮንዶም – የእርግዝና መከላከያ
- በመመርያዎቹ መሰረት ሚጠቀሙት ከሆነ 98 በመቶ ውጤታማ ነው።
- ከላስቲክ እና ፕላስቲክ የሚሰሩት፣ እርግዝናን እና በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን የሚከላከሉ ኮንዶሞች በወንድ ልጆች ብልቶች ላይ የሚጠለቁ ሲሆኑ ለተጨማሪ መከላከያነት ከሌሎች የወሊድ መቆጣጠርያ ዘዴዎች ጋር ሊጠቀሟቸው የሚችሏቸው ናቸው። ኮንዶሞች ውጤታማ እና በትንሽ ወጪ በቀላሉ የሚገኙ እና አንዳንድ ጊዜ በነፃ የሚገኙ ናቸው።
- ሁለቱም ሴቶች እና ወንዶች የኮንዶምን ከአጋሮቻቸው ጋር ለመጠቀም እንዴት እንደሚወያዩ ከተረዱት ውጤማነቱ ሊጨምር ይችላል።
- የመጠቀሚያ ማለቂያ ጊዜን የኮንዶም ማሸጊያ ላይ ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም ላስቲክ በጊዜ ብዛት ሊበላሽ ስለሚችል እና ኮንዶሞች የመጠቀሚያ ማለቂያ ጊዜ በኋላ ከተጠቀሙባቸው ሊቀደድ ይችላል።