እርግዝናን መከላከል

የእርግዝና መከላከያ

 ብዙ ሴቶች እርግዝናን ለማዘግየት ወይም  እንዳይከሰት ለማድረግ የእርግዝና መከላከያ መጠቀም ባሁኑ ጊዜ እየተለመደ ነዉ። የተጠቃሚዉን መጨመር ተከትሎ  የተለያዩ እንክብሎች በየመድኃኒት ቤቱ መገኘት ጀምሯል።

የእርግዝና መከላከያ ለባለትዳሮች  አራርቆ ለመዉለድ  እና የልጆችን ቁጥር ከመመጠኑም በተጨማሪ  ጽንስ ማስወረድን ለማስቀረት ይረዳል።  የእርግዝና መከላከያ ከጥቅሙ ባሻገር እንደየሰዉ ቢለያይም የተለያዩ ጉዳቶችን እንደሚያስከትሉ ይታወቃል።

እርግዝና መከላከያ የሚያስከትሉ ችግሮች በዋናነት የሚጠቀሱት የራስ ምታት፣የማቅለሽለሽ እና የሰዉነት ዉፍረት መጨመር ይጠቀሳሉ።

የእርግዝና መከላከያ ከመዉሰድ በፊት  የተለያዩ  ጥንቃቄዎችን መዉሰድ አለብን ።

ለምሳሌ ፡- ሲጋራ የሚያጨስ ሰዉ፤የልብ በሽታ እና የማያቋርጥ ራስ ምታት ያለዉ ሰዉ፤ የሱኳር በሽታ ያለበት ሰዉ ፤ የጉበት በሽታ ያለበት ሰዉ እና እድሜዉ ከ35 አመት በላይ የሆኑ ሶቶች መድኃኒቱን ባይወስዱ ይመረጣል።

የእርግዝና መከላከያ ሲወሰድ የጉበት ምርመራ እና የደም ዝዉዉር ሂደትን ስለሚገታ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል።

ከብዙ አይነት የእርግዝና መከላከያዎች አብዛኛዉን ጊዜ በኛ ሀገር ህብረተሰቡ የሚጠቀምበትን እንይ።