አይዩዲ

አይዩዲ (በማህፀን ውስጥ የሚቀበር መሳርያ)

አይዩዲ ትንሽ የላስቲክ መሳርያ ሲሆን (እንደ አይነቱ እና ፍላጎትዎ መሰረት) ለወራት ወይም ለአመታት ወደሚቀመጥበት ማህፀን በጤና ጥበቃ ሰጪዎ የሚጨመር ነው። ውጤታማነቱ 99% ወይም ከዛ በላይ ነው።

አይዩዲ ስፐርም እንቁላልን እንዳያገኝ የሚከለክል እና ከስፐርም ጋር የተገናኙ እንቁላሎች በማህፀን ውስጥ እንዳያድግ የሚከለክል መዳብ ወይም ሆርሞኖችን የያዘ ነው።

ጠቀሜታ

  • አንድ ጊዜ አይዩዲ ከተቀመጠ በየቀኑ የወሊድ መቆጣጠርያን ማስታወስ አያስፈልግም።
  • የአይዩዲ መዳብ ቀጣይነት ላለው 10 ዓመታት የእርግዝና መከላከያን ይሰጣል።
  • አይዩዲ ከሆርሞኖች ጋር የወር አበባ ህመሞችን ሊቀንስ የሚችል እና የወር አበባ ፍሰትን በከፍተኛ ሁኔታ ሊቀንስ ይችላል።
  • እነርሱም ለ5 ዓመታት በቦታው ሊቀመጡ ይችላሉ።

ጉዳቶች

  • አይዩዲ በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን አይከላከልም፣
  • ከማህፀን ሊወጣ ይችላል፣
  • ከወር አበባ ጋር ተያይዞ (ህመሞች፣ የተለያዩ የወር አበባ ጊዜያቶች፣ ከባድ እና ረጅም የወር አበባ ጊዜያቶች) ችግሮች ሊፈጥር ይችላል።