ጽንስ በሆድ ውስጥ

ልጃችሁ በሆዳችሁ ውስጥ ምን ያደርጋል?

ጽንሱ በሆድ ውስጥ ሲንቀሳቀስ አስደሳች ስሜት ለእናቲቱ ይፈጥራል። ህጻኑም በመላው የእርግዝና ጊዜያቶች ውስጥ ንቁ ነው። የጽንሱ እንቅስቃሴ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰማዎት ከ 16-22 ባሉት ሳምንታት ውስጥ ነው። በፊት ወልደው ለሚያውቁ ሴቶች ይህ ስሜት ቀደም ብሎ ሊመጣ ይችላል።

በመጀመሪያ የጽንሱ እንቅስቃሴ በአብዛኛው አይሰማዎትም፤ አልያም የማህፀን እንቅስቃሴ በሳምንት አንድ ሁለት ጊዜ ብቻ ይሰማና ከትንሽ ጊዜ በኋላ እንቅስቃሴው በየቀኑ ይሰማል።

ጽንሱ በሚያድግበት ጊዜ፣ እንቅስቃሴው በጉልህ ይሰማዎታል በሂደትም እንቅስቃሴው በይበልጥ ይሰማዎታል። ምናልባት ግን ትንንሽ እንቅስቃሴዎች ላይሰማዎት ይችላሉ፣ ለምሳሌ አውራጣታቸውን ሲመጠምጡ ወይም የእጅ እና የእግር ጣቶቻቸውን ሲያሳስቡ ስሜቱን ላታደምጡት ትችላላችሁ።

በመጨረሻዎቹ የእርግዝና ጊዚያቶች ደግሞ አንዳንድ ምቶችንና መገላበጦችን ምናልባት ስርቅታንም ሊያደምጡ ይችላሉ። እነዚህ ሁሉ እንቅስቃሴዎች በመጨረሻዎቹ የእርግዝና ጊዜያት በጉልህ የሚታወቅዎት ሲሆኑ ምጥ እስከሚጀምርበት ሰዓት ድረስ ሊዘልቁ ይችላሉ።

እንቅስቃሴዎች ስለጽንሱ ጤና ምን ይላሉ?

ጽንስ ምንም ጤነኛ ቢሆን እንኳ፣ ሁልጊዜም አይንቀሳቀስም። ሁሉም ጤነኛ ህጻናት ጸጥተኛ ይሆናሉ ወይም ለአጭር ጊዜ ይተኛሉ። በአብዛኛው፣ ንቁ ልጅ ጤነኛ ነው። አንዳንድ እናቶች ጽንሱ ደህና ቢሆንም እንኳ፣ የሌሎችን እናቶች ያህል የጽንሱ እንቅስቃሴ አይሰማቸውም። ትልቅ ተክለ ሰውነት ያላቸው ወይም የእንግዴ ልጁ ከማህጸናቸው ፊት ለፊት ከሆነ ያን ያህል ጠንከር ያለ የጽንስ እንቅስቃሴ አይሰማቸውም።

የጽንሱን እንቅስቃሴ ዕለት በዕለት ልብ ማለት፣ የእርግዝና ጊዜ ጥሩ ልምድ ነው። ከ28 ሳምንት ጀምሮ፣ የተወሰነ ጊዚያቶችን የጽንሱን እንቅስቃሴ በአትኩሮት ለመከታተል ጊዜዎን ቢመድቡ ጥሩ ነው።

በአብዛኛው ጽንስ የሚንቀሳቀሰው በጠዋት እና በማታ  አካባቢ ነው። ጽንሱ በሚነቃበት ጊዜ የጽንሱን እንቅስቃሴ ስሜት ሊለማመዱት ይችላሉ። እንቅስቃሴው ይበልጥ የሚሰማዎት በጎንዎ ሆነው ወይም ተቀምጠው ዘና ሲሉ ነው። የጽንሱ እንቅስቃሴ በቆሙበት ሰዓት፣ እየተራመዱ ወይም በሌላ ስራ ከተጠመዱ ብዙም አይሰማዎትም።

ወደ መጨረሻዎቹ የእርግዝና ወቅት የጽንሱ እንቅስቃሴ የተለየ ይሆናል። አነስ ያለ ምት ወይም እርግጫ እና በዛ ያለ መገለባበጥ ይሰማዎታል። ይሁን እንጂ፣ የጽንሱን እንቅስቃሴ በየቀኑ በተመሳሳይ ሰዓት የሚከታተሉ ከሆነ፣ 10 እንቅስቃሴዎችን ለማድመጥ ተመሳሳይ የሚሆን ጊዜ የሚወስድ ይሆናል።

ጤነኛ ጽንስ በሚነቃበት ጊዜ በሁለት ሰዓት ውስጥ ቢያንስ ለ 10 ጊዜ ይንቀሳቀሳል። ምናልባት ከተለመደው የየዕለት እንቅስቃሴ ያነሰ እንቅስቃሴ የሚሰማዎት ከሆነ አሳሳቢ ይሆናል። ጸጥ ወዳለ ቦታ በመቀመጥ በአትኩሮት የጽንሱን እንቅስቃሴ ለማድመጥ መሞከር።

በአንድ ቀን ውስጥ ጽንሱ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ካላሳየ ወይም መንፈራገጡ በቀናት ውስጥ እየቀነሰ የሚሄድ ከሆነ እና አነስተኛ እንቅስቃሴ ብቻ ከተሰማዎት፣ በአፋጣኝ ወደ እናቶች ጤና ጣቢይ ወይም ወደ ዶክተር መሄድ ግድ ይላል። በፍጹም እስከ ቀጣዩ ቀን አይጠብቁ!

የጽንሱን እንቅስቃሴ መስማት ካልቻሉ

ጁስ በመጠጣት ወይም ቀዝቃዛ ውሀ በመጠጣት ወይም ለጥቂት ደቂቃዎች በመራመድ፣ ቀጥሎም እንደገና መቆጠር መጀመር። እንዲህም ሆኖ የጽንሱ እንቅስቃሴ ካልተሰማዎት፣ በአፋጣኝ ወደ ጤና ጥበቃ መደወል ያስፈልጋል! በፍጹም እንዳትዘገዩ!