የለቅሶ መፍትሄ

የለቅሶ መፍትሄ

አስታውሱ የጨቅላው ማልቀስ በራሱ የሚጎዳ አይደለም፤ ምናልባትም እንዲሁ ፈልጎ ይሆናል። የሚያለቅስን ህጻን ለማስቆም የሚከተሉት መፍትሄዋችን ይሞክሩ

  • የሚመጡት ወይም የሚመጠምጡት ነገር መስጠት፣
  • ጠቅልሎ ማቀፍ፣
  • የሆነ አይነት ጩሀት ማሰማት፣
  • የውሀ ድምጽ ማሰማት፣
  • ንጹህ አየር፣ ማንቀሳቀስ፣
  • መልዕክት መንገር፣
  • ሙሉ ልብሱን ማውለቅ፣
  • የሽንት ጨርቅ መቀየር፣
  • በሚያረጋጋ ሎሽን ማሸት።
  • ጓደኛን ወይም ዘመድን ለማማከር መጥራት፣ የምታምኑት ሰው እንዲረዳችሁ ማድረግ

ለራሳችሁ እንዲህ በሉት “ከጥቂት አመታት በኋላ የኔ ልጅ ማቆም እስኪያቅተው መሳቅ ይጀምራል!”

ምንም አድርጉ ምን፣ ብስጭታችሁን ህጻናችሁ ላይ አትግለጹ።  በፍጹም ጨቅላን የንዴት አትወዝውዙት ። የህጻን የአእምሮ ውስጥ ያሉት የደም ስሮች የውዝዋዜን ተጽዕኖ መቋቋም የማይችሉና ሊሰበሩ የሚችሉ ናቸው።

በተሎ የማይባበል አልቃሻ ህጻን በቤተሰቦቹ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ውጥረት ይፈጥራል። ይመስገነውና፣ ከፍ እያለ ሲሄድ፣ ራሱን ማረጋጋት የሚችል እና አብዛኛው ልቅሶውም የሚቀንስ ይሆናል። አረ ሣቁም የማይጠገብ ፍሰኃ ነው።