Skip to content (Press Enter)
- ምንጊዜም ቢሆን ህጻኑን በጀርባው ማስተኛት
- ህጻናትን ለማስተኛት ምቹው ቦታ የህጻናት አልጋ ነው፤ በአግዳሚ ወንበር፣ በሶፋ፣ በአልጋ ወይም በትራስ እንዲተኙ ማድረግ አንዳንድ ባለሙያዎች ይከለክላሉ፤
- ለህጻኑ ልትሰጡት የምትችሉት በጣም የተሻለው ነገር የእናት ጡት ወተት ነው፤ የእናት ጡት ወተት የተሻለው ነው!
- ህጻኑን ለሁለተኛ እጅ ጭስ (ለምሳሌ የሲጋራ ጭስ ባለበት አከባቢ) አታጋልጡት
- ለሌሎች እንክብካቤ ማድረግ እንዲችሉ እናቶች እና አባቶች ራሳቸውን መንከባከብ አለባቸው።
- የልጅዎን ገላ ከማጠብዎ አስቀድሞ፥ የልጅዎ እትብት እስከሚወድቅ ድረስ ይጠብቁ።
- ልጆች በእያንዳንዱ ቀን ክ 1 – 4 ሰዓታት ያህል ያለቅሳሉ፤ ማልቀስ ልጅን አይጎዳም፤ ግን የለቅሶውን ሁኔታ የማያቋርጥ ከሆነ ለሀኪሞ ያስታውቁ።
- ለጨቅላ ህፃን ልጅ ማልቀስ ብቸኛው የመግባቢያ መንገድ ነው። ልጆች ለተለያዩ ፍላጎቶቻቸው የተለያየ ልቅሶ ያለቅሳሉ፤ ወላጆች ይህን የህፃን ልጃቸውን አለቃቀስ ማጤንና ማወቅ አለባቸው።
- ልጆች ሲርባቸው፣ ሲረጥቡ፣ ሆዳቸው ሲነፋ፣ በጣም ሲሞቃቸው ወይም በጣም ሲበርዳቸው ያለቅሳሉ።
- ልጆች ሲተኙ፣ ወላጆችም ወድያው መተኛት አለባቸው፤ የቤቱ ስራ መቆየት ይችላል
- ወላጆች በቂ እንቅልፍ የማይተኙ እንደሆነ፥ ስሜታቸው ይለዋወጣል፤ የእንቅልፍ ማጣት በትንሹ መነጫነጭ፣ ቁጡነት፣ ድካም፣ ነገረኛነት ወዘተ ያስከትላል። ወላጆች እንቅልፍ ማጣት የሚያስከትለውን የስሜት መለዋወጥ ፈጽሞ ቸል ማለት የለባቸውም። ልብ ይበሉ! የእንቅልፍ ማጣት እጅግ መልካም የሆነ ሰውን ወደክፉ አረመኔነት ይለውጣል።
- ደረቅ ያሉ ምግቦችን ለልጆች መመገብ የሚመከረው ከ6 ወራት ዕድሜ በኋላ ነው።
- ለባሎች፥ እናቶች ጨቅላ ህፃን ልጅን ስለመንከባከብ ሁሉን ነገር ያውቃሉ ብላችሁ አትገምቱ።
- ልጅዎን ከትንባሆ ጭስ ይጠብቁ፤ ልጆችዎ አጠገብ ማጨስ በልጆች ላይ የጤና ችግር ያመጣል።
- እርስዎ እና ልጅዎ በአንድ ማንኪያ መመገብ የለባችሁም።
- ልጅዎን የሚነኩ ሁሉ – ወላጆችን ጨምሮ – እጃቸውን አስቀድመው መታጠብ አለባቸው፤ ጉንፋን፣ ሳል፣ ኢንፍዌንዛ ያለባቸው ሰዎች ልጅዎን ሊነኩ አይገባም።
- ሌሎች ትናንሽ ልጆችን ከጨቅላ ልጅዎ ጋር ለብቻቸው አይተዉ።
- ለልጅዎ ልዩ የሆነ የመኪና መቀመጫ ይጠቀሙ፤ ጨቅላ ልጅዎን በሚንቀሳቀስ መኪና ውስጥ በእጅዎ አይቀፉ።
- ጨቅላ ልጅዎን ቤት ውስጥ በአልጋ ላይ ወይም ልብስ መቀየሪያ ጠረጴዛ ላይ ትተው አይሂዱ፣ ለአፍታም ቢሆን!ልጅዎ ወድቆ/ቃ ሊጎዳብዎ/ልትጎዳብዎ ይችላል/ትችላለች።
- ልጅዎን ውሃ አከባቢ ላይ ብቻቸዉን አይልቀቁ፤ በመዋኛ ገንዳዎች፣ ሐይቆች፣ ኩሬዎች ወይም የመታጠቢያ ገንዳ አከባቢም ልጅዎን ብቻቸዉን አይልቀቁ።
- በመኝታ ጊዜ ልጅዎን አጥብቀው በማቀፍ የሚወዱትን መዝሙር ደግመው ደጋግመው ይዘምሩ፤ ተመሣሣይ መዝሙር መዘመር ልጅዎ እንዲሰክን እና ደህንነት እንዲሰማው ያደርጋል።
- ምክሮች ሁሉ ጨቅላዎችን በደምሳሳው የሚያጠቃልሉ ናቸው። እባክዎን ልጅዎ ልዩ መሆኑን እና የተለየ ፍላጎት ሊኖረው እንደሚችል ያስታውሱ። ጥያቄ ቢኖርዎት፥ የህጻናት ሐኪምዎን ይጠይቁ።
- በእያንዳንዱ ምሽት ልጅዎ የሚለቅስ ሲሆን እርስዎ ራስዎ ልክ እንደ ልጁ ማልቀስ እስኪዳዳዎ ድረስ ያሰለችዎታል። ተረጋግተው ይህም እንደሚያልፍ በማሰብ ልጅዎን ይንከባከቡ።